ⓘ Free online encyclopedia. Did you know?
                                               

አለቃ ገብረ ሐና

ከህይወት ታሪካቸው ስንጀምር አንዳንዶች የአባታቸው ስም ደስታ ተገኝ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ገብረ ማርያም ነው ይላሉ። ምናልባት አንዱ የአለም ሌላው ደግሞ የክርስትና ስማቸው ሊሆን ይችላል። የተወለዱት በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በድሮው የደብረታቦር አውራጃ ፎገራ ወረዳ፤ ናብጋ ጊዮርጊስ በተባለው ቦታ በ1814 ዓ.ም. ነው። የመጀመርያ ትምህርታቸውን በአካባቢው ከቀሰሙ በኋላ ወደ ጎጃ ...

                                               

አቡነ ሰላማ

አቡነ ሰላማ በአጼ ቴወድሮስ ዘመን የነበሩ ፓትሪያርክ ናቸው። የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን አጭር ታሪክ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጒድጓድ ተቅበዘበዙ።” ዕብ. 11፥38። በእርግጥ ዓለም ለእገሌ ይገባል ለእገሌ አይገባም የምትባል አይደለችም። ቅዱሳን መናንያን ግን በራሳቸው ፈቃደ ዓለምን አንፈልግሽም ስላሏት ዓለም አልተገባቸውም ተባሉ። እንደ ማንኛውም ሰው ...

                                               

አቡነ ተክለ ሃይማኖት

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው፤ በ፲፩፻፺፯ ዓ.ም ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው "አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡ ...

                                               

አባ ሳሙኤል ወልደ ካህን

አባ ሳሙኤል ወልደ ካህን የራስ ተፈሪ መኮንን እና የዘመዳቸው የራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴ አስተማሪ 1894-1904 ዓ.ም. ግድም ሁለታቸው በሐረር የኖሩ ልጆች በሆኑበት ጊዜ ነበሩ። ጃንሆይ በጻፉት መጽሐፍ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ምዕ. 1 መሠረት፣ አባታቸው ራስ መኮንን ፣ ልጆቹን በፈረንሳይኛ በቀን አንድ ሰአት እንዲያስተምሯቸው የጉዋዶሎፕ ሐኪም ዶ/ር ቢታልያን እንዳስቀጠሩ ይታወሳል። ...

                                               

ኣያና ብሩ

ኢንጂነር ኣያና ብሩ የአማርኛ የጽሕፈት መሣሪያንና በመሣሪያው የኣከታተቡን ዘዴ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው። ከኣድዋ ድል በኋላ ኢትዮጵያውያን የእንግሊዝኛውን የታይፕራይተር ወይም የጽሕፈት መሣሪያ ኣጠቃቀም ከተረዱ ወዲህ መሣሪያውን ለኣማርኛ ቀለሞች እንዲያገለግል ለ85 ዓመታት ግድም ቢታገሉም ሳይሳካ ቀርቷል። በመካከሉ ከተደረጉት የተለያዩ ሙከራዎች መካከል የኢንጂነር ኣያና ሥራ ኣንዱ ነ ...

                                               

ከንቲባ ገብሩ

ከንቲባ ገብሩ እውነተኛ ስማቸው ጎባው ደስታ ሲሆን የአቶ ደስታ ወልደ እስይ እና ወይዘሮ ትርንጎ ተክሌ ልጅ ነበሩ። የተወለዱትም ጎንደር ውስጥ አለፋ ጣቁሳ የሚባል ቦታ ሲሆን፣ ወላጆቻቸው መሳፍንቶች ስላልነበሩ ብዙ እንግልት ደርሶባቸው ካደጉ በሁዋላ በሚስዮን ወደ ውጭ ሄደው ተምረው ሲመለሱ ባሳዩት ችሎታ በራስ መኮንን የሐረር ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ። ቀጥሎም ከአድዋ ጦርነት በሁዋላ በዓ ...

                                               

ወይዘሮ የሺ እመቤት

ወይዘሮ የሺመቤት የልዑል ራስ መኮንን ባለቤት እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እናት ነበሩ። የሺመቤት አሊ ጋምጩ ማናቸው? ልዕልት የሺእመቤት እናታቸው ወ/ሮ ወለተጊዮርጊስ የምሩ ሲባሉ አባታቸው ደግሞ አሊ ጋምጩ ይባላሉ፡፡ የተወለዱት አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ዶሉ በሚባል ቦታ ነው፡፡የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ ከ20 አመት በፊት በወረኢሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የታሪ ...

                                               

ዘውዱ ጌታቸው

ዘዉዱ ጌታቸው ፣ ኤች.አይ.ቪ|ኤድስን በሚመለከት ፀጥታና ዝምታ በሰፈነበት ወቅት ራሱ ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖር ይፋ በማዉጣት "ትውልድ ይዳን በእኛ ይብቃ"! ብሎ ኤች.አይ.ቪ|ኤድስን ለመዋጋት የተነሳ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነበረ። ዘውዱ ጌታቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በመስፍን ሀረር ትምህርት ቤት ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ተምሮ ካጠናቀቀ በኋላ በአዲ ...

                                               

የኢትዮጵያ መላክተኞች በብሪታኒያ

የታላቋ ብሪታኒያ መንግሥት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ጉዳዩን የሚያስፈጽምለት ወኪል እና የብሔራዊ ምሥጢራዊ ጉዳይ ባለሙያ ፤ በጊዜያዊነትም ኾነ በቋሚ ሹመት ወደኢትዮጵያ መላክ የጀመረው በ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው። ከዚያ በፊት በተለያዩ ጊዜያት መላክተኞችን የሰደደ ቢሆንም የነዚያ ተልዕኮ ግን ወደተለያዩት የክፍለ አገራት መሳፍንት እና ገዚዎች ነበር። የኢትዮጵያም ነገሥታት ከዓፄ ቴዎድሮስ ...

                                               

ዮናስ እሸቴ

መለጠፊያ:ፖለቲካ ዮናስ እሸቴ ሰኔ ፩፮ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. በአዲስ አበባ የተወለደ የኢትዮ-ፈረንሳይ የፖለቲካ ሰው እንዲሁም የፖለቲካና የኮምኒኬሽን አማካሪ ሲሆን በአሁኑ ሰአት የህዝባዊ አንድነት ንቅናቄ የፈረንሳይ ቀኝ ክንፍ ፓርቲ አባልና የፓርቲው የክልላዊ የወጣቶች ተጠሪ ነው።

                                               

ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን

ኪዳኔ ወልደመድኅን ዓርብ ሌሊት ሐምሌ ፪ ቀን ፲፱፻፯ ዓ.ም ቡልጋ በከሰም ወረዳ፤ የለጥ ቀበሌ፤ ልዩ ስሙ ቡሄ አምባ በሚባለው ሥፍራ ላይ ከናታቸው ከወይዘሮ አስካለ ደጀን እና ከአባታቸው ከቀኛዝማች ወልደመድኅን አዩደረስ ተወልደው ነሐሴ ፲ ቀን በጥምቀት ስም ኪዳነ ማርያም ተሰይመው የለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስቤተ ክርስቲያን ክርስትና ተነሱ። አባታችው ቀኛዝማች ወልደመድኅን ትውልድ ሃገራቸው ወበሪ ...

                                               

ጀምበሬ ሃይሉ

ቀኝ ጌታ ጀምበሬ ኃይሉ ደብረ ታቦር ውስጥ ተወለዱ። በልጅነታቸው በቤተ ክርስቲያን ትምሕርት ዳዊት፣ ጾመ ድጓ፣ ቅኔ፣ ዝማሬ እና አቋቋም ያጠኑት እኒህ ሰው አሁን የሚታወቁት በስዓሊነት ነው። በ፲፱፻፲፱ ዓ/ም ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ የወጣቱ ጀምበሬን አጎት ዓለቃ ዓለሙን ወሎ ውስጥ የምትገኘውን ተድባባ ማርያም የተባለች ቤተ ክርስቲያን በስዕል እንዲያስጌጡ ጠየቋቸው። በዚህ መሠረት ወጣቱ ጀም ...

                                               

ጣይቱ ብጡል

"ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ" በሚል ቅፅል ስም የታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብ ዳር ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፪ዓ/ም በጌምድር ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ። በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት በተወለዱ በ ፹ ቀናቸው ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፰፻፴፫ ዓ/ም በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሡ። በ ...

                                               

ጸጋዬ ገብረ መድህን

ፀጋዬ ገብረመድኅን ቦዳ ተብላ በምትታውቅ አምቦ ካተማ አካባቢ በምትገኝ ተራራማ ቦታ ተወለዱ። በአምቦ ማአረገ ሕይወት ቀ.ኃ.ሥ. ትምህርት ቤት ከዚያም ጀነራል ዊንጌትና በአዲስ አበባ የንግድ ትምህርት ቤት በአገር ውስጥ ትምህርታችውን ከገፉ በኋላ በቺካጎ ብላክስቶን በህግ ትምህርት ተመርቀው በ1952 እንደ ወጡ በለንደን ከተማ የቴአትር ትምህርት በሮያል ኮርት ቴአትርና በፓሪስ ኮሜዲ ፍራንሴ ...

                                               

ፒተር ኡስቲኖቭ

ስር ፒተር አለክሳንደር ኡስቲኖቭ የነበረ የእንግሊዝ ተዋናይ፣ ጸሃፊና ተውኔት ደራሲ ነበር። በተለይ ደግሞ ፊልም ሰሪ፣ ቲያትር አዘጋጅ እና ኦፔራ መሪ፣ ፊልም አዘጋጅ፣ መድረክ ተላሚ፣ ፊልም ደራሲ፣ ቀልደኛ፣ ኮሜዲያን፣ ጋዜጣ አዘጋጅ፣ መጽሔት አዘጋጅ፣ ራዲዮ አስተላላፊና ቴሌቪዥን አቅራቢ ነበር። ሰር ፒተር ኡስቲኖቭ በእናቱ በኩል የራሽያ ነገስታት ዘር ሲሆን በአባቱ በኩል ደግሞ የራሺያ፣ ...

                                               

ሮማርዮ ሪከርድስ

ሮማርዮ ሪከርድስ ባለፉት 15 ዓመታት በሙዚቃ አሳታሚነት እንዲሁም አከፋፋይነት የካበተ ልምድ ያለው ሲሆን አሁን ደግሞ በፊልም ስራዎች በሙዚቃ ክሊፖች እንዲሁም አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሙሉ የፕሮዳክሽን ስራ ጀምራል፤፤ ሮማርዮ ሪከርድስ በኢትዮጵያ ሰፊ የስርጭት አድማሱን በማስፋት በአሁኑ ወቅት ተመራጭ የሙዚቃ አሳታሚ እና አከፋፋይ መሆኑ ተመስክሮለታል በቅርቡም ኦንላይን የሙዚቃ ገብያ ...

                                               

የኢትዮጵያ ሙዚቃ

ግርማዊ ጃንሆይ በአልጋ ወራሽነታቸው በ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. አውሮፓን ጎብኝተው ሲመለሱ አርባ የአርመን ተወላጆች በበጎ አድራጎት ለመርዳት ካስመጧቸው የመንፈስ ማነቃቂያና የሞራል መጠበቂያ እንዲሁም ለሀገሪቱ የሥልጣኔ እርምጃ ይጠቅማል በማለት የሙዚቃ ትምህርት ቤት አቋቋሙ። ከዚህ በኋላ በዚሁ ዓመተ ምሕረት ከወለጋ ጠቅላይ ግዛት ከሾጎሌ ፻፳ የሚሆኑ ወጣቶች መጥተው በሙዚቃ ትምህርት እንዲሰለጥኑ ...

                                               

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩ እና የሚጻፉ ቋንቋዎችን፣ እና የምልክት ቋንቋን ያጠቃልላል። በአገሩ ውስጥ ፺ የሚሆኑ ቋንቋዎች አሉ። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የስራ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵ ...

                                               

ጌዴኦኛ

ጌዴኦኛ ወይም ጌዴኡፋ በኢትዮጵያ ውስጥ በጌዴኦ ብሔረሰብ የሚነገር ኩሻዊ ቋንቋ ነው። የጌዴኦ ብሔረሰብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ሲሆን በብሔረሰቡ አባላት ጌዴኡፋ በመባል ይጠራል። ቋንቋው በተለይ ከሲዳምኛ፣ ከከምባትኛ፣ እና ከሀዲይኛ ቋንቋዎች ጋር የመመሳሰል ባህርይ አለው። በአሁኑ ሰዓት ጌዴኡፋ ከንግግር ቋንቋነት አልፎ የሥራ እና የትምህርት ቋንቋ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. የ ...

                                               

ሆሣዕና በዓል

የሆሣዕና በዓል ሆሣዕና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን ሲሆን በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊ ...

                                               

ምሻምሾ

ምሻምሾ በኢትዮጵያ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ ነው። በ1902 ዓ.ም በታተመው የትብብር ሥራቸው፣ አለቃ ታየ ሚሻ ሚሾ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅላት ለማስታዎስ በስቅለት ቀን፣ በዓመት ኣንድ ጊዜ እንደሚካሄድ ያሰፍራሉ። እንደርሳቸው አባባል፣ ሚሻ ሚሾ እሚለው ሃረግ የመጣ ውሾ ዉሾ ከሚል ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ ከተሰነዘረ ስደብ ትውስታ ነው።

                                               

አሸንድየ

አሸንድየ በኢትዮጵያ የሚከበር በዓል ነው። በዚህ በዓል፣ ህጻናት አሸንዳ ከተባለ፣ የነጭ ሽንኩርት ቅጠል እሚመስል ረጅም ሳር የተለያዩ አይነት ጌጦችን በማበጀት፣ እንዲሁም ቀበቶና ቀሚስ በመስራት፣ በየቤቱ በመሄድ አሸንድየ አሸንድ አበባ እርግፍ እንደ ወለባ እያሉ በመዝፈን የሚጨፍሩበት የጨዋታና በዓል አይነት ነው። አለቃ ታየ በ1902 ዓ.ም. በታተመ የትብብር መጽሐፋቸው፣ አሸንድየ በዓልን ...

                                               

ደብረ ታቦር (ዓመት በዓል)

የዚህ በዓል መሠረት የክርስቲያን እምነት ሲሆን፣ ደብረ ታቦር በግዕዝ የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደፀሐይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራ ...

                                               

ፋሲካ

ፋሲካ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል የተነሳበትን የትንሳዔ ቀን ማሰብያ ዕለት ነው። ስሙ ፋሲካ የመጣው ከአረማይክ /ፓስኻ/፣ ግሪክኛ /ፓስቃ/፣ ዕብራይስጥ /ፐሳኽ/ ሲሆን፤ የአይሁድ ፋሲካ በዓል ዕብራውያን በሙሴ መሪነት ከግብፅ ፈርዖን ግዛት በተዓምራትና በመቅሠፍቶች የወጡበትን ጊዜ ለማክበር ነበር። ይህ ታሪክ በተለይ በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘጸአት ይገለጻል። በተለይ በዘጸአት 12፡23 ...

                                               

ቀጥቃጭ

የኢትዮጵያን ባህላዊ የብረትና ነሓስ እቃዎች እንዴት እንደሚሰሩ የሚያውቅና በተግባርም የሚተረጉም ምሁር ቀጥቃጭ ይባላል። ግን ያን የሚያደርጉና ይህን የመሰለ የጅ ጥበብ ያላቸው እነኚህ ባለሙያዎች በህብረተሰቡ ዘንድ የተናቁና የተገፉ ናቸው ይህ ደግሞ ከጥንት ጀምሮ የመጣ ነው የሚገርመው ነገር አሁንም ድረስ እነዚህ ወርቅ እጅ ያላቸው ማህበረሰቦችን በተለያየ መንገድ በተለያየ ስያሜ ይጠሯቸዋል ...

                                               

አረቄ

የኢትዮጵያ አረቄ አዘገጃጀት በአጭሩ. 1ኛ በበቂ ሁኔታ ደርቆ የተፈጨ እኩል ይዘት ያላቸው በቆሎ እና ብቅል ማዘጋጀት ለምሳሌ አንድ ቁና ብቅል እና አንድ ቁና በቆሎ. 2ኛ ብቅሉን በእንስራ አድርጎ በላዩ ላይ ውሃ መሙላት።. 3ኛ በመቀጠልም የተፈጨው በቆሎ በዋድያት /በዝርግ እቃ/ አድርጎ በውሀ ከተንፈረፈረ በኋላ በማግስቱ በብረት ምጣድ ማንኮር።. 4ኛ በመቀጠልም በተዘጀው ብቅል ላይ በሶስ ...

                                               

ስልጤ

ስልጤ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።የስልጤ ብሔረሰብ በሀገራችን ከሚገኙ በርካታ ብሔሮች: ብሔረሰቦችና ህዝቦች አንዱ ነው: ብሔረሰቡ በአዲስ አበባ-ሆሳዕና መንገድ በ172 ኪ.ሜ ርቀት ከመንገዱ ግራና ቀኝ 60 ኪ.ሜ ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን በስፋት ይኖራል የዞኑ ጠቅላላ ስፋት 3ሺkm² ነው እኤአ 2004 በተደረገ ቆጠራ በዞኑ የሚኖረው 850ሺ በዞኑ መስደደር ቢቻ የነበረ ...

                                               

ቤተ እስራኤል

ቤተ እስራኤል በኢትዮጵያ ሲኖሩ የነበሩ የዘር ሃረጋቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸው የአብርሃም የያዕቆብ የይስሃቅ የዘር ሃረግ ሲሆን በኢትዮጵያ ለብዙ ዘመናት ሲኖሩ ቆየተው ከ1984 እ.ኤ.አ. ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ወደ እስራኤል ሃገር በመመለስ ላይ ይገኛሉ። የመጀመሪዎቹ ቤተ እስራኤላዊያን ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት 500 አመት በፊት፤ የመጀመሪያው የሰለሞን ቤተ መቅደስ ከፈረሠ በሗላ፣ ...

                                               

አርጎባ

አርጎባ ኢትዮጵያ በደቡብ እስከ ባሌ በምስራቅ እስከ ሐርር፣ አፋር ሰሜን ሸዋ ትግራይ ክፍል ድረስ የሚኖሩ አርጎብኛ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችን የሚገልጽ ቃል ነው። አርጎባ በአፋር ዞን 3 የአርጎባ ልዩ ወረዳ፣ አዋሽ ሠባት ኪሎ፣ ወረርና የመሳሰሉት፣ በአማራ ሰሜንሸዋ (ምንጃር - መልካጅሎ፣ ጮባ፣ በረኸት፣ አሳግርት፣ ሸዋ ሮቢት፣ አጣዬ፣ ጣርማበርና የመሳሰሉት፣ በደቡብ ወሎዞን እና ኦሮሚያ ልዩ ...

                                               

ወላይታ

ወላይታ በቀድሞ ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ባሁኑ ደቡብ ክልል የሚገኝ ና የራሱ የሆነ ቋንቋና ባህል ያለው ሕዝብ ሲሆን ከሲዳማ፡ ከከምባታ፡ ከሃዲያና ተመሳሳይ ቋንቋ ከሚናገሩ ከኩሎ ኮንታ ከጎፋና ጋሞ ሕዝብ ጋር ይዋሰናል። ወላይታ ህዝቡ በጣም የተደባለቀ ሲሆን በከተማ አከባቢ ልቆ የሚገኝ ኃይማኖት ኦርቶዶክስ ይሁን እንጂ በጠቅላላ አውራጃው ፕሮቴስታንትና እስልምና እምነት እየተስፋፋ ነው። የወላይ ...

                                               

ዛይሴ

ዛይሴ ወይም ዘይሴ በኢትዮጵያ ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሚገኝ ብሔረሰብ ነው። የዛይሴ ብሔረሰብ በጋሞ ጎፋ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ኤልጎ፣ወዘቃ እና ዛይሴ ደንብሌ በሚባሉ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖር ሲሆን፣እነዚህ ቀበሌዎች ከጋሞጎፋ ዞን ርዕሰ ከተማ አርባ ምንጭ በ22 ኪ.ሜ. ርቀት ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ከአርባ ምንጭ ወደ ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ኾንሶና ዲራሼ ልዩ ወ ...

                                               

የሲዳማ ባሕላዊ ሐይማኖት

የሲዳማ ባህላዊ ሐይማኖት ሲዳማ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል አንዱ ሲሆን፡ ቀድሞ የሲዳሞ ክፍለ አገር ይባል በነበረው እና በአሁኑ ጊዜ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት አካል በሆነው ሲዳማ ዞን ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ነው። ህዝቡ ከሲዳማ ዞን ውጪ በአጎራባቹ የኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች ውስጥ ይኖራል። የህዝብ ብዛቱም ከአራት ሚሊዮን በላይ እንደሆነ የተለያዩ ...

                                               

ጅሩ

ጅሩ የሚባለው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች የሚኖሩበት በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኝ አካባቢ ሲሆን በዚሁ ዞን ሁልት ወረዳዎች እና አራት አነስተኛ ከተሞች አሉት። እነሱም እንሳሮና ዋዩ እና ሞረትና ጅሩ ወረዳ ይባላሉ። እንሳሮ እና ዋዩ ወረዳ ዋና ከተማው ደነባ ይባላል። ደነባ ከአዲስ አበባ በ175 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ስትገኝ ከደብረ ብርሃን 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በዚሁ ወረ ...

                                               

ጌዴኦ

ጌዴኦ በኢትዮጵያ ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ የሚገኝ ብሔር ነው። የጌዴኦ ብሔረሰብ በዋናነት በጌዴኦ ዞን ውስጥ ባሉ ስድስት ወረዳዎች በስፋት የሚኖር ሲሆን ከዞኑ ውጪም በሲዳማ ዞን፣ በኦሮሚያ ክልል በቦረና እና በጉጂ ዞኖች በሚገኙ አጎራባች አካባቢዎች ወይንም ወረዳዎች በብዛት እንደሚገኙ ይገመታል። የጌዴኦ ብሔረሰብ በዋናነት በሚገኝባቸው የከተማና የገጠር አካባቢዎች ሌ ...

                                               

ሐረር

ሐረር ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ በአምስት መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተማ ናት። በዘመኑ የአስተዳደር መዋቅር የሃረሪ ክልል ዋና ከተማ ናት። በ1.885 ሜትር ከፍታ ላይ፣ የወይና ደጋ የአይር ጠባይ በተላበሰ ቦታ ላይ አርፋለች። በምድር መጋጠሚያ ውቅር 9°19′ ሰሜን ኬክሮስ እና 42°07′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ናት። በ1987 ዓመተ ምህረቱ የህዝብ ቆጠራ መ ...

                                               

መርሻ ናሁሰናይ

አቶ መርሻ ናሁ ሰናይ ከዓጼ ምኒልክ ዘመነ ሥልጣን እስከ ዓጼ ኃይለሥላሴ ድረስ ለሀገራቸው ከፍተኛ ምሣሌያዊ አገልግሎት ያበረከቱ ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ከ1890ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1902 እ.ኤ.አ በሐረር የታሪካዊው ጄልዴሳ እና የአካባቢው አስተዳዳሪ ሆነው አገልግለዋል። የድሬዳዋ ከተማ እንዲቆረቆር ቁልፍ ሚና ከመጫወታቸውም በላይ ከ1902 እስከ 1906 እ.ኤ.አ የድሬዳዋና አካባቢዋ የመጀመሪ ...

                                               

መባዓ ጽዮን

መባዓ ጽዮን በሌላ ስማቸው ተክለ ማርያም በዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን የነበሩ ጻድቅ ሰው ሲሆኑ በተወለዱ በ፸፬ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ተለይተዋል። ገድላቸው እንደሚጠቅሰው በሸዋ ግዛት አንዳገብጣን ይባል እነበር ቦታ ከአባታቸው ሀብተ ጽዮንና እናታቸው ጽዮን ትኩና በስለት ተወለዱ። ቀጥሎም ከአባታቸውና ከተለያዩ ቀሳውስት ትምህርት በመቅሰም አድገው እራሳቸውን በጾምና ጸሎት በማነጽ ቅድስናን አግ ...

                                               

ሙሴ ቀስተኛ

ሙሴ ቀስተኛ ጣልያንኛ፡ Sebastiano Castagna) ይሄ ሰው በአድዋ ጦርነት የጣልያን መንግሥት አገራችንን ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛትነት ለመግዛት ከገቡት ወታደሮች አንዱ ሲሆን፣ ለወረራ የመጣው የጠላት ኃይል በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ እና በሠራዊታቸው ቆራጥነት አድዋ ላይ ድል ሲሆን ተማርኮ የቀረና እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ የኖር ኢጣልያዊ ነው። ሙሴ ቀስተኛ በ፲፰፻፷ ዓ/ም በ ...

                                               

ማርኮ ፖሎ

ማርኮ ፖሎ ጥንታዊው የጣሊያን ተጓዥ እና ነጋዴ ነበር። ታዋቂነትም ያተረፈው በተለይ ወደቻይና እና ሞንጎሊያ ከተጓዙት አውሮጳውያን ቀደምትነት ስለነበረው ነው። በዚህ ምክንያት ከሱ በኋላ ዘግይተው የተነሱት እነ ክርስቶፎር ኮሎምበስ ሳይቀር ለሱ ከፍተኛ ግምት እና አድንቆት እንደነበራቸው ታሪክ ይዘክራል። ት 1 17 አመት ሲሞላው ከጣሊያን ቬኒስ ከተማ በመነሳት፣ መጀመሪያ በጀልባ ከዚያም በእ ...

                                               

ሪቻርድ ፓንክኸርስት

ዶክተር ሪቻርድ ፐንክኸርስት ዲሴምበር 3፣ 1927 እ.ኤ.አ. ከእንግሊዛዊቷ እናታቸው ሲልቪያ ፓንክኸርስትና ጣሊያናዊ አባታቸው ሲልቮ ኮሮ ተወለዱ። በባንክሮፍትስ ስኩል ኢን ውድፎርድ ቀዳሚ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የኢኮኖሚካዊ ታሪክ ዶክትሬት አግኙ ።

                                               

ሲልቪያ ፓንክኸርስት

እመት ሲልቪያ ፓንክኸርስት ሚያዝያ ፳፰ ቀን ፲፰፻፸፬ ማንቼስተር በምትባለው የእንግሊዝ ከተማ ተወለዱ። እናታቸው ለሴቶች መብት እና የፖለቲካ ድምጽ ታጋይ የነበሩት ኤመሊን ፓንክኸርስ ሲሆኑ አባታቸው ዶክቶር ሪቻርድ ፓንክኸርስት ይባሉ ነበር። እመት ሲልቪያ የታወቁት የታሪክ ምሁር የፕሮፌሶር ሪቻርድ ፓንክኸርስት እናት ናቸው። ግፈኛው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ መጀመሪያ ይሄው የ ...

                                               

ስሜን መንግሥት

Kingdom of Semien/የቤተ እስራኤሎች ስርወ መንግስት የሰሜን መንግስት በሚል ስያሜ የሚታወቀው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የአይሁድ እምነት ተከታይ ቤተ እስራኤላዊያን ፤አቋቁመውት የነበረው ስርወ መንግስት ነው። ይህ የቤተ እስራኤላዊያን ስርወ መንግስት ከ4ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን የነበር መሆኑን ታሪክ ያሳያል።323_1640 በ4ተኛው ክፍለ ዘመን፣ኢት ...

                                               

ሽመና

ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸው በርካታ ባህላዊ አና ታሪካዊ እሴቶች መካከል የሕዝቦች ባህላዊ አለባበስ አንዱ ነው። ይህ ባህላዊ አለባበስ ደግሞ በአመዛኙ የሽመና ሥራ ውጤት ነው። የሽመና ሥራ በሀገራችን መቼና እንዴት እንደተጀመረ በትክክል የሚገልጽ የጽሑፍ መረጃ ባይኖርም ከሺ ዓመታት በላይ ዕድሜ እንዳለው አንዳንድ ጽሑፎች ይጠቁማሉ። በሀገራችን የሺ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው የሽመና ሥራ ...

                                               

ባቲ ድል ወምበሬ

ባቲ ድል ወምበሬ የአዳል ገዢ እንዲሁም የዘይላ አስተዳዳሪ የነበረው ኢማም ማህፉዝ ልጅ የነበረች ሲሆን አባቷ ከሞተ በኋላ ግራኝ አህመድን አግብታ በባሏ ዘመቻ ሁሉ ተሳታፊ የነበረች ሴት ናት። ግራኝ ከተገደለ በኋላ የእህቱ ልጅ የነበረውን ኑር ኢብን ሙጃሂድ በማግባት የባሏን ሞት የተበቀለች የአዳል መሪ ናት። ባቲ የሚለው ቃል ማዕረጓን ሲያሳይ፣ "ድል ወምበሬ" የሚለው ስያሜ ደግሞ በአማርኛ ...

                                               

አልፍሬድ ኢልግ

ቢትወደድ አልፍሬድ ኢልግ በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ኑሮውን ኢትዮጵያ ውስጥ የመሠረተ፤ የስዊትዘርላንድ ዜጋ ነበር። ኢልግ በምሕንድስና ሙያው ባቡር እና የቧንቧ ውሐ ለአገራችን ካስተዋወቃቸው ብዙ ዘመናዊ የሥልጣኔ መስመሮች ሁለቱ ሲሆኑ በንጉሠ ነገሥቱ ፊት ታላቅ ታማኝነትን በማፍራቱ የዘውድ አማካሪ እና የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ እስከመምራትም የበቃ ሰው ነበር። ቢትወደድ ኢልግ በዘ ...

                                               

አርባ ልጆች

አርባ ልጆች የተባሉት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የቱርክ መንግስት አርመናውያን ላይ ጭፍጨፋ ባካሄደበት ወቅት ወላጆቻቸውን በማጣት እና ከጭፍጨፋው ለማምለጥ ተሰደው በእየሩሳሌም የአርመን ገዳም ውስጥ ሲኖሩ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ አምጥተው ያሳደጉዋቸው 40 አርመናውያን ልጆች ናቸው። በልጆቹ የሙዚቃ ችሎታ የተደመሙት አፄ ኃይለሥላሴ በእየሩሳሌም የአርመን ፓትርያርክ ...

                                               

አባ ጎርጎርዮስ

አባ ጎርጎሪዮስ እስክንድር ከመካነ ሥላሴ ወሎ የመጡ ቄስና የመኳንንት ዘር ነበሩ። ከጀርመናዊው ሉዶልፍ እዮብ ጋር በመሆን በአማርኛና በግዕዝ ብዙ መዝገበ እውቀቶችን የጻፉ ናቸው ። በመርከብ መሳፈር ኤቲኒሬሪ=itineraryስሕተት ምክኒያት ከኢትዮጵያ ወደ ሕንድ ከዛም ወደ አውሮፓ የገቡት አባ ጎርጎርዮስ እስክንድር በ፲፮፶፪ ዓ.ም. ሉዶልፍና እሱን ይደጉመው የነበረው የሳክስ ጎታ እና አምስ ...

                                               

አብዲሳ አጋ

ኮሎኔል አብዲሳ አጋ የተወለደው በ፲፱፻፲፪ ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል፣ ወለጋ ዞን ነበር። በ፲፪ ዓመቱ አባቱ በንዴት ወንድማቸውን አበበን በመግደላቸው ሲታሰሩ አብዲሳ አባቱን ለማስፈታት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርግም ሳይሳካ በሞት ተቀጥተዋል። በኋላም በ፲፬ ዓመቱ የኢትዮጵያን ጦር በመቀላቀል ሀገሩን ማገልገሉን ሀ ብሎ ጀመረ።

                                               

አው ባድር

ኣው-ባዲር፣ አው-ባድር፣ አባዲር፦ ፦ በ ፲፫ ኛው ክ/ዘመን ውስጥ የተፃፈውና ስለ ሐረር ጥንታዊ አፈታሪካዊ ታሪክ የሚዘክረው ፋዝ መዲናት ሐረር የተባለው ያልታተመ መጽሐፍ እንደሚገልጸው አባድር እጅግ ከተከበሩት የሐረር ሼኽዎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ናቸው። በዚሁ መጽሓፍ አገላለጽ መሠረት፡ አባድር ከሌሎች በርካታ ሼኾች ጋር በመሆን ከሂጃዝ በ፮፻፩፪ ሂጅሪያ ተነስተው ሐረር ከገቡ በኋላ በአ ...

                                               

አይቲዮፒያ (የግሪክ ቃል)

አይቲዮፒያ የሚለው ቃል መጀመርያ በጥንታዊ ምንጮች የመልክዓ ምድር ስያሜ ሆኖ ሲታይ፣ የላየኛ አባይ ወንዝ አውራጃ እንዲሁም ከሳህራ በረሃ በስተደቡብ ላለው አገር በሙሉ ያመለከት ነበር። ይህ ስም በግሪክ በሆሜር ጽሁፎች በ ኢልያዳ ና ኦዲሲ ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። በተለይ ከግሪክ ታሪክ ምሁር ሄሮዶቱስ ጀምሮ "አይቲዮፒያ" ሲጻፍ ትርጉሙ ከግብጽ ወደ ደቡብ ለተገኘው የአፍሪካ ክፍል ሁሉ እንደ ሆ ...