Back

ⓘ መስከረም
                                               

ለውረን ዳይጎል

ለውረን አሽሊ ዳይጎል የአሜሪካ ዘመናዊ የክርስቲያን ሙዚቃ ዘማሪና እና የዜማ ደራሲ ናቸው። ወደ ሴንትሪሲቲ ሙዚቃ ከተሰየሙ በኋላ ኻው ከን ኢት ብ የተባለውን የመጀመሪያ አልበማቸውን እ.ኤ.አ በ2015 አወጡ። መዝሙሩም በቢልቦርድ ከፍተኛ የክርስቲያን አልበሞች ገበታ ላይ ቁጥር 1 ሆኗል፣ በአር.አይ.ኤ.ኤ ፕላቲነም የምስክር ወረቀት ያስገኘ ሲሆን ክርስቲያናዊ ኤርፕለይ ቢልቦርድ ገበታ ላይ የመጀመሪያ የሆኑትን ሌሎች ነጠላ ዜማዎችንም አፍርቷል፤ እነርሱም ፌርስት፣ ትረስት ኢን ዩ እና ኦ ሎርድ ናቸው። የዳይጎል ሦስተኛው የስቱዲዮ አልበም የሆነው" ሉክ አፕ” በመስከረም ወር 2018 ተለቋል። ይህም" ዩ ሰይ” በሚለው ነጠላ ዜማ የፖፕ ክሮስ-ኦቨር ስኬት አመጣና በቢልቦርዱ 200 ዝርዝር ውስጥ ሦስተኛ ሊሆን ቻለ። በተጨማሪም ከ 20 ዓመት በላይ ሴቶች ምድብ በብዛት የተሸጠ የክርስቲያን አልበም የተባለ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ወደ 115 ሺህ የሚጠጋ ጊዜ በመሸጥ በብዛት የተሸጠ የክርስቲያን አልበም ለመሆንም በቅቷል። የአልበሙ መሪ ነጠላ ...

                                     

ⓘ መስከረም

መስከረም የወር ስም ሆኖ በጳጉሜ ወር እና በጥቅምት ወር መሀከል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ መጀመርያው የወር ስም ነው።

"መስከረም" ከግዕዙ "ከረመ" ከሚለው ግስ የተባዛ ነው። ሌላ ከቀረቡት ግመቶች መካከል መነሻው "መሰስ-ከረም" ክረምቱ መሰስ ብሎ ማለፉን፣ ወይም "መዘክረ-ዓም" የዓመት መታወሻ ይባላል። በቅብጢ አቆጣጠር የዚህ ወር ስም ጦውት ነው። ይህም በጥንታዊ ግብጽ አረመኔ ሃይማኖት ከጣኦት ስም "ጀሑቲ" መጣ።

በጎርጎርዮስ አቆጣጠር የሰፕቴምበር መጨረሻና የኦክቶበር መጀመርያ ነው።

                                     

1. በመስከረም ወር ነጻ የወጡ የአፍሪቃ አገራት

  • መስከረም ፲፬/14 ቀን ፲፱፻፷፮/1966 ዓ/ም የቀድሞዋ የፖርቱጋል ጊኒ ቢሳው
  • መስከረም ፳/20 ቀን ፲፱፻፶፱/1959 ዓ/ም የቀድሞዋ ቤችዋናላንድ ቦትስዋና
  • መስከረም ፳፩/21 ቀን ፲፱፻፶፫/1953 ዓ/ም ናይጄሪያ
  • መስከረም ፳፪/22 ቀን ፲፱፻፶፩/1951 ዓ/ም የቀድሞዋ የፈረንሳይ ምዕራብ አፍሪቃጊኒ
  • መስከረም ፳፬/24 ቀን ፲፱፻፶፱/1959 ዓ/ም የቀድሞዋ ባሱቶላንድ ሌሶቶ
  • መስከረም ፳፱/29 ቀን ፲፱፻፶፭/1955 ዓ/ም ኡጋንዳ