Back

ⓘ ሚያዝያ
                                               

አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ የስማቸው ትርጓሜ የክርስቶስ፣ የአብ ፣ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ማለት ነው ፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊታቸው ላይ እፍ ብሎ ጸጋውን፣ በረከቱን ስላሳደረባቸው በዚህ ስም ይጠራሉ ፡፡ የጻድቁ፣ የአባታቸው ስም መልአከ ምክሩ ሲሆን ፤ የእናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ ፡፡ የትውልድ ቦታቸው በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዳውንት ዐወን ዓባይ የተባለ አካባቢ ነው ፡፡ የተፀነሱት ሚያዝያ ፰፤ የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ ፰ ቀን ነው ፡፡

                                     

ⓘ ሚያዝያ

ሚያዝያ የወር ስም ሆኖ በመጋቢት ወር እና በግንቦት ወር መሀከል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ስምንተኛው የወር ስም ነው።

"ሚያዝያ" ከግዕዙ "አኅዘ" ከሚለው ግስ የተባዛ ነው።

በቅብጢ አቆጣጠር የዚህ ወር ስም ፓረሙደ ነው። ይህም በጥንታዊ ግብጽ አረመኔ ሃይማኖት ከጣኦት ስም "ፓ-ኤን-ረነኑተት" የረነኑተት ወር መጣ።

በጎርጎርዮስ አቆጣጠር የኤፕሪል መጨረሻና የመይ መጀመርያ ነው።