Back

ⓘ ዴሞክራሲ
                                               

ሰአዳ መሐመድ ኢብራሂም - seada mohammed Ibrahim

ሰአዳ መሐመድ ኢብራሂም - seada mohammed Ibrahim የዚህ ታሪክ አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን እናወጣለን፡፡ በ tewedajemedia gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚ ...

ዴሞክራሲ
                                     

ⓘ ዴሞክራሲ

ዴሞክራሲ በተጠነሰሰበት ጥንታዊት ግሪክ ፣ ሰዎች ይኖሩ የነበረበት መሠረታዊ የፖለቲካ አሃድ ዩኒት ፣ ከተማዊ መንግስት ይባላል። ይህ በአሁን ዘመን ካለው አገር ወይንም ብሔራዊ መንግስት ይለያል። ከተማዊ መንግስታት፣ ለምሳሌ አቴና እንደ ከተማ አስተዳደርነቱ ፣ በቆዳ ስፋት አንስተኛ ስለነበር የዘመኑ ዲሞክራሲ በቀጥተኛ ተሳትፎ በስብሰባ ላይ የተመሰረተ ነበር። ነገር ግን ይህ ዓይነት አሰራር ከ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ለተነሱት በንፅፅር ግዙፍ ለሆኑት ብሔረ መንግስታት እማይቻል ስለነበር ማለት ከአገሪቱ ግዙፍ የቆዳ ስፋት አንጻር ሁሉን ዜጋ በየሳምንቱ ለስብሰባ መጥራት ስለማይቻል በእንግሊዝ አገር ፓርላማ የተባለ አዲስ ሥርዓት ተፈጠረ። ይህም ማለት ሕዝቡ ተወካዮቹን የፓርላማ ዓባላትን ይመርጣል፤ ተመራጮችም መንግሥትን ይመሠርታሉ። ይህ ዓይነት ሥርዓት ቀጥተኛ ያልሆነ ዴሞክራሲ በመባል ይታዎቃል። በአሁኑ ሰአት አብዛሃኛዎቹ የአለም ሃገራት የሚጠቀሙበት የመንግስት መዋቅር ነው።

                                     

1. ዜግነትና ዴሞክራሲ

አንድ ሥርዓት ዲሞክራሲያዊ፣ በሌላ አነጋገግር ከ ሕዝብ ወይም በ ሕዝብ የቆመ ነው ከተባለ፣ ሕዝብ ማለት እዚህ ላይ ምንድን ነው? አብዛኛውን ጊዜ ሕዝብ ማለት ዜጋ ማለትን ሲዎክል፣ እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ አብዛኞች ዲሞክራሲያዊ ሃገሮች ዜግነትን ትንሽ ለሆነ የህብረተሰብ ክፍል ሴቶችን፣ ድሆችን፣ ዘሮችን ያገለሉ ብቻ ያድሉ ነበር። እነዚህ ትንሽ ክፍሎች ብቻ እሚሳተፉበት ዴሞክራሲ በአሁኑ ዘመን ተቀባይነትን ያጣ ነው። ባሁኑ ዘመን፣ ዲሞክራሲ ማለት ብዙኃኑ ኅብረተሰብ መንግሥት የማዋቀር መብት አለው። የጥቂቶች መብት ደግሞ በህግ የተጠበቀ ነው።

                                     

2. ሥርዓተ ሕዝብ፣ ሥርዓተ ልሂቅ፣ ሥርዓተ ጥቂት

ፖለቲካዊ ዜግነት ሕጻናትን እንደማይጨምር አሁን ድረስ አብዛኞች ሃገራት የሚሰሩበት ነው። ይሁንና፣ በዚህ መንገድ አላግባብ ሌሎችም የሕዝብ አካላት እየተገለሉ ሄደው፣ ዴሞክራሲው ወደ ሌላ ዓይነት ሥርዓት ሊቀየር ይችላል። ለምሳሌ በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ የተከበሩ ሰዎች ብቻ እሚሳተፉበት ሥርዓት ሲፈጠር ሥርዓተ ልሂቅ ወይንም አሪስቶክራሲ ይባላል። በሆነ አጋጣሚ ዕድል አግኝተው ጥቂት ቡድኖች ብቻ በማህበረሰቡ ላይ በሚተላለፉ ውሳኔዎች ሲሳተፉ ሥርዓተ ጥቂት ወይንም ኦሊጋርኪ ይባላል። ይህን ሁኔታ ለማዎቅ አንድ ጊዜ አስቸጋሪ ይሆናል ምክንያቱም በሙሉ ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሥርዓት ሳይቀር፣ ጊዜ አግኝተው በፖለቲካው የሚሳተፉ ግለሰቦች ከአጠቃላይ ዜጋ ጥቂት ስለሆኑ። ይሁንና በዲሞክራሲ፣ የመሳተፍ መብቱ ለሁሉም ዜጋ ምንጊዜም ያለ ነው፣ ይጠቀሙበት አይጠቀሙበት።

                                     

3. ዴሞክራሲ ለምን ተፈለገ?

እንደ ፈላስፋው ጆን ስቱዋርት ሚል ሦስት ምክንያቶች ይጠቀሳሉ፦

ሥልታዊ ምክንያት

ሕግ አርቃቂዎች የአንድን ሕብረተሰብ ጥቅም፣ መብት እና አስተሳሰብ በሚያረቁት ሕግ ውስጥ ግምት እንዲያስገቡ ከሌሎች የፖለቲካ ሥር ዓቶች በላይ ዴሞክራሲ ያስገድዳቸዋል። በዚህ ምክንያት ሰዎች በዚህ ሥርዓት ውስጥ የመጎዳታቸው ዕድል አንስተኛ ነው። ተመራማሪ ዓማርትያ ሴን ዋቢ ሲሰጥ "በማናቸው ዲሞክራሲያዊና ሉዓላዊ መንግስታት ከፍተኛ ርሃብ ተከስቶ አያቅም" ይላል።

ሥነ ዕውቀታዊ ምክንያት

ዴሞክራሲ አብዛኛውን ሕዝብ በውሳኔ አስጣጥ ላይ ስለሚያካፍል፣ ከሌሎች የፓለቲካ ሥርዓቶች በበለጠ ሥለ ሕዝቡ ጉዳይ ያዎቀ ሆኖ ይገኛል። በውሳኔ አሰጣጥ የሚካፈለው ሕዝብ መብዛት በሌላ ጎን ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ እሚደረገውን ስራ ያግዛል፣ ተሳታፊዎችም ስለ ጉዳዮች የበለጠ የተተቸና የተብራራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይረዳል።

የዜጎችን ባሕርይ የማሻሻል ምክንያት

በዴሞክራሲ ሥርዓት ያሉ ሰዎች በውሳኔዎች ላይ ስለሚሳተፉ፤ ከሌሎች ሥርዓት ሰዎች በተለየ እራሳቸውን ችለው እንዲያስቡ፣ በሃሳባቸው ምክንያታዊ እንዲሆኑ እና የሌሎችን መብቶች ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ስለሚገደዱ በሥነ ምግባር እንዲሻሻሉ ይሆናሉ።

ከሚያስከትለው ጥቅም ውጭ ሌሎች ሥነ ምግባራዊ ጥቅሞች ይጠቀሳሉ። ለምሳሌ ሓርነት እና ዕኩልነት፣ እኩልነት፣ የሕግ የበላይነት፣ የመናገር መብት፣ ፍትህ ይጠቀሳሉ

                                     

4. በዴሞክራሲ ላይ የተነሱ ትችቶች

ፕላቶ የሥርዓተ ልሂቃን ዓይነት መንግስት ደጋፊ ስለነበር ዲሞክራሲን ከዚህ አቋሙ ተነስቶ ለመንቀፍ ሞክሯል። በእርሱ አስተሳሰብ በዲሞክራሲ ሥር ዓት ወደ ሥልጣን ላይ መውጣት እሚችሉት የምርጫ ሥር ዓቱን በማጭበርበር ወይንም በብልጥ ንግግር እና ስራ ሰውን በማታለል የተካኑ ሰዎች ይሆናሉ። ምርጫን እሚያሸንፉ ሰዎች ደግሞ የግዴታ መንግስታዊ ኣስተዳደር ላይ ብቁ ሆነው ስለማይገኙ፣ ዴሞክራሲ መንግስትን ለንደዚህ ያለ ግሽበት ይዳርጋል ይላል።

የእንግሊዙ ቶማስ ሆብስ በአንጻሩ የዘውድ ሥርዓትን በመደገፍ፤ የዴሞክራሲ ሥርዓት መንግስት እንዳይረጋጋ እሚያረጉ ተቃውሞዎችን ያበረታታል በማለት ይነቅፋል።

                                     
  • Nouvelle ቤኒን በቀይ ቀለም ዋና ከተማ ፖርቶ ኖቮ ኮቶኑ ብሔራዊ ቋንቋዎች ፈረንሳይኛ መንግሥት ፕሬዝዳንት የብዙ ፓርቲ ዴሞክራሲ ፓትሪስ ታሎን ዋና ቀናት ሐምሌ ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. August 1, 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነት ከፈረንሳይ
  • ከተማ ዌሊንግተን ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ ማዎሪ የምልክት ቋንቋ መንግሥት ንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር የፓርላማ ዴሞክራሲ እና ሕገ መንግሥታዊ ንጉሳዊ መንግሥት ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ፪ኛ ጆን ኪይ የመሬት ስፋት አጠቃላይ ካሬ ኪ.ሜ
  • Nauru Bwiema ዋና ከተማ ያሬን ብሔራዊ ቋንቋዎች ናውሩኛ እንግሊዝኛ መንግሥት ፕሬዝዳንት ፓርለሜንታዊ ሪፐብሊክ ዴሞክራሲ ባሮን ዋካ የመሬት ስፋት አጠቃላይ ካሬ ኪ.ሜ. 21 193ኛ የሕዝብ ብዛት የ2011 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
  • አፒያ ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ ሳሞዓኝ መንግሥት ዖ ለ ዓኦ ኦ ለ ማሎ ጠቅላይ ሚኒስትር የአንድነት ፓርለሜንታዊ ዴሞክራሲ ቫኣለቶኣ ጹኣላኡቪ ፪ ጡኢላአፓ ዓኢኦኖ ጻኢለለ ማሊአለጋኦኢ የመሬት ስፋት አጠቃላይ ካሬ ኪ.ሜ. 2, 842 167ኛ
  • Atua ዋና ከተማ ፉናፉቲ ብሔራዊ ቋንቋዎች ቱቫሉኛ እንግሊዝኛ መንግሥት ንግሥት አገረ ገዥ ጠቅላይ ሚኒስትር የፓርላማ ዴሞክራሲ እና ሕገ መንግሥታዊ ንጉሳዊ መንግሥት ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ፪ኛ ኢኣኮባ ኢታለሌ አነለ ሶፖጋ የመሬት ስፋት አጠቃላይ
  • ከተማ ፓሊኪር ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ መንግሥት ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት ፌዴራላዊ ፓርለሜንታዊ ሪፐብሊክ ዴሞክራሲ ፒተር ክርስቲያን ዮሲዎ ጆርጅ የመሬት ስፋት አጠቃላይ ካሬ ኪ.ሜ. 702 177ኛ የሕዝብ ብዛት የ2015
  • televised ይታያል ስለ Badawi plight ጨምሮ ቢያንስ 2016 በቀዳሚ መሆኑን ገልጸዋል ሰብዓዊ መብቶች እና ዴሞክራሲ ወደ Raoul Wallenberg ማዕከል ሰብዓዊ መብቶች ግብረ እንደ Badawi አለም አቀፍ የህግ ምክር. ከድርጅቱ
  • የሚሰጡዋቸውን ሊደርስባቸው የአሜሪካ በህዳሴው ቅድሚያ የሚሰጡዋቸውን አስተሳሰብ አሁን scorned grassroots ዴሞክራሲ SNCC ስለጀመሩ ቅድሚያ በመስጠት ስለጀመሩ ቅድሚያ የሚሰጡዋቸውን ላይ, establishing ጥልቅ - አሁን አካባቢ
  • የሚሰጡዋቸውን ሊደርስባቸው የአሜሪካ በህዳሴው ቅድሚያ የሚሰጡዋቸውን አስተሳሰብ አሁን scorned grassroots ዴሞክራሲ SNCC ስለጀመሩ ቅድሚያ በመስጠት ስለጀመሩ ቅድሚያ የሚሰጡዋቸውን ላይ, establishing ጥልቅ - አሁን አካባቢ

Users also searched:

...
...
...