Back

ⓘ ደብተራ
                                     

ⓘ ደብተራ

ደብተራ ማለት ድንኳን ማለት ነው አንድም ካህንን አገልጋይ መዘመር አንድም በእውቀቱ ከፍ ያለ ሊቅ ማለት ነው።

●የደብተራ ትርጓሜ በመዛግበተ ቃላት ወጥበባት ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላቸው፡-

‹‹ደብተራ – ድንኳን፡፡ ደበተረ – ደብተር ዘረጋ፣ ጻፈ፣ ከተበ ፡፡ ተደበተረ – ተዘረጋ፡፡ ደብተራ – የድንኳን ስም፡፡ ደብተራ – ዜማ. ቅኔ፣ ሳታት ሰዓታት የሚያውቅ፣ በደብተራ በድንኳን ውስጥ የሚመራ፣ የሚቀኝ፣ የሚዘምር፣ መንፈሳዊ አገልጋይ፣ ካህን፣ አወዳሽ ሳታት ቋሚ፡፡ ደብቴ – ከፊለ ስም ወይም ቁልምጫ፣ የደብተራ ወገን፣ የኔ ደብተራ ማለት ነው፡፡›› ይሉናል፡፡

● #ግእዙም፡-

‹‹ደብተረ› ማለትን በአወራረዱ ሕግ በተንበለ ቤት አስገብቶ ሲያበቃ ‹‹ተከለ›› ሲል ይተረጕምና ለድንኳን ይሰጠዋል፡፡

ግእዝ ድንኳን ለሚለው ቃል ከደብተራ በተጨማሪ ኀይመትና ደበና ማለትን ይጠቀማል፡፡ ደበና የንጉሥ ድንኳን የሚጠራበት ስም ነው፡፡ ደበናንሳ ባለእጅ የሚለው ቃል ከዚህ ስም ጋራ ስለመያያዝ አለመያያዙ አላውቅም! ●የፕ/ር ሥርግው አማርኛ የቤ/ክ መዝገበ ቃላት፡- ‹‹ደብተራ የቃሉ ቀጥተኛ ትርጕም ድንኳን ማለት ነው፡፡ ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅኔ ማኅሌት የያሬድን ዜማ የሚዘምር፣ የሚመረግድ እንዲሁም ቅኔን የሚቀኝ ደብተራ ይባላል፡፡›› ብሎናል፡፡

                                     
  • ይገባል ለወልድም ምስጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድርጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው ማለት ነው ከሰማይ እንደተመለሰ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣዕመ
  • ወደካቶሊክነት የተቀየረውና ከአንቷን ዳባዲ ጋር በዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን ስለሆነው ሁሉ ደብዳቤ ይለዋወጥ የነበረው የዋድላው ሰው ደብተራ አሰጋኽኝ ጥር 1858 ዓ.ም. ለአንቷን ዳባዲ በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ በማለት ይህን ሁኔታ ገልጦት ነበር አለቃ ገብረ
  • ደብዳቤዎቻቸው በአማርኛ ይጻፉ ነበር ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል የደብተራ ዘነብ መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ ም ደብተራ ዘነብ የጻፉት የቴዎድሮስ ታሪክ የኢዘንበርግ የዓለም ታሪክ 1842 እና የአማርኛ የጂኦግራፊ መጽሐፍ 1842
  • ጠላ ስጡ የማይገባ ሱሪ የማይበቅል ዘሪ የማይጠረጥር ቤቱን አያጥር የማይጣሉ መላእክት የማይታረቁ አጋንንት የማይጽፍ ደብተራ ክንፍ የሌለው አሞራ የማይፈርስ ምሽግ የለም የማይፈወስ ድዉይ የማይመለስ ጊጉይ የሜዳ ንስንሱን የቤት ጉስጉሱን የሜዳ

Users also searched:

...
...
...