Back

ⓘ ኢትዮጵያ
                                               

ዴቪድ ቡክሰን

ዴቪድ ቡክሰን ከ1903 እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ የኖሩ ስነ እንስሳ ባለሙያ እና የብርታኒያ ቆንጽላ ሰራተኛ የነበሩ ሰው ናቸው። ስለ ኢትዮጵያ ጥንት አብያተክርስቲያናት፣ ሩሲያ ኪነ ህንጻ ጥበብ እና በምሥራቅ አውሮፓ ከእንጨት ስለተሰሩ አብያተክርስቲያናት በጻፉት መጽሐፍት ይታወቃሉ።

                                               

ገበጣ

ገበጣ ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ ጨዋታ ነው። እንደ ቼስ ና ዳማ በጠፍጣፋ ገበቴ ላይ ሁለት ሰወች የሚጫወቱት የጨዋታ አይነት ነው። በግብጦሽ ህግ መሰረት ገበቴው ላይ 18 ጉድጎዶች ሲኖሩ የተወሰኑ ጠጠሮችም በየጉድጘዱ ይቀመጣሉ። የጨዋታው አላማ እንግዲህ የባላጋራን ጠጠሮች መብላት ነው። የባላጋራ ጠጠሮች ዜሮ ሲቀሩ ያንጊዜ አሸነፍን ይባላል። ስዕሉ የሚያሳየው 3 ረድፍ ያለው ገበጣ ይሁን እንጂ ባለ ሁለት ረድፍ ብቻም አለ። ይህን ጨዋታ በኢንተርኔት መጫወት ይቻላል እዚህ ላይ

                                               

እስክስታ

እስክስታ ትኩረቱ የትከሻ እንቅስቃሴ የሆነ፣ ነገር ግን የእግር እንቅስቃሴንም የሚያካትት የውዝዋዜ አይነት ነው። እስክስታ የሚለው ቃል እስክስ ከሚለው እንደተመዘዘ ይታመናል። እስክስ ማለት አንድን ነገር ያለ መቆራረጥ ወይንም ፍስስ በሚል መልኩ መስራት እንደማለት ነው። ስለዚህም የትከሻ አካባቢ ንቅናቄ የውሃ አወራረድን ወይንም የፏፏቴ ጅረትን በመወከል ይከወናል። ከላይ ከተሰጠው ትርጓሜ አንጻር አብዛኛው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩ የውዝዋዜ አይነቶች በእስክስታ ስር ሊጠቃለሉ ይችላሉ። ልዩነታቸው እንግዲህ በየትኛው የሰውነት ክፍል ላይ ትኩረት እንደሚሰጡ ነው። የጉራጌ እስክስታ ለምሳሌ ከትከሻ ይልቅ ለእግር እንቅስቃሴ ትኩረት ይሰጣል፣ የ ሸዋ እስክስታ ምንጃር እስክስታ እንዲሁ ለእግር ትኩረት ሲሰጥ፣ የወሎ እስክስታ ሆታ ወደ ትከሻ ያደላል። የጎጃም እስክስታ እንቅጥቅጥ፣ ዝናብ፣ ድረባእና የጎንደር እስክስታ ዋንጫ ልቅለቃ፣ ደበኔ እስክስታ ወደ ላይ ሰውነት ክፍል እንቅስቃሴ እያደላ ይሄዳል። የትግራይ እስክስታ እስታሌላይ፣ አውረስ በመዘዋወር ...

                                               

በፍቃዱ አባይ ተክሉ/ Befekadu Abay teklu

በፍቃዱ አባይ ተክሉ/ Befekadu Abay teklu ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ እስካሁን መስፈርቱን የሚያሟሉ ባለታሪኮች ግለ-ታሪካቸውን እየጻፉ እየላኩልን ነው፡፡ እርስዎም tewedajemedia gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ6 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ...

                                               

ቴሌብር

ቴሌብር በኢትዮ ቴሌኮም ማለትም በኢትዮጵያ ብቸኛ የቴሌኮሙኒኬሽን እና የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ባለቤትነት የተጀመረው የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ነው። ቴሌብር ያለ ጥሬ ገንዘብ ግብይትን የሚያቀላጥፍ ስርዓት ነው። የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች በቴሌብር እገዛ ክፍያ መፈጸም ፣ ገንዘብ ማስተላለፍ እና የሞባይል የኋላ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። ይህም ደንበኞች በሁሉም አውታረመረቦች ላይ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሸቀጦች እና አገልግሎቶች እንዲከፍሉ፣ ለትምህርት ቤት ክፍያዎች ፣ ለፍጆታ ክፍያዎች እና ወዘተ በቀላሉ ክፍያ እንዲያደርጉ በእጅጉ ይረዳቸዋል። በተጨማሪም የሞባይል የአየር ሰዓት እና ጥቅልሎችን በቀላሉ እንድገዙም ያስችላቸዋል።

                                               

አለምሰገድ አበበ /Alemseged Abebe

አለምሰገድ አበበ /Alemseged Abebe ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በፊልም ፤ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እናስተዋውቃለን፡፡ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ5 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ ከሚድያ ዘርፍ ታሪኩ የሚቀርብለት ሰው አለምሰገድ አበበ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብቸኛው የጥናትና ምርምር ፕሮግራም አዘጋጅ አለምሰገድ አበበ ትውልድ ና ልጅነት ተወልዶ ያደገው በአሰላ ከተማ ሲሆን አዲስ ...

                                               

ደረጀ ሀይሌ ሺበሺ- Dereje haile shibeshi

ደረጀ ሀይሌ ሺበሺ- Dereje haile shibeshi ኮሜዲያ ደረጀ ሀይሌ የራሱን አሻራ ያኖረ ባለውለታ የዚህ ታሪክ አሰባሳቢ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ስእል ፤ በስነ-ጽሁፍ፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን እናወጣለን፡፡ በ tewedajemedia gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደ ...

                                               

ዳግማዊ ታሪኩ / dagmawi Tariku

ዳግማዊ ታሪኩ / dagmawi Tariku የዚህ ታሪክ አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን እናወጣለን፡፡ በ tewedajemedia gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስ ...

                                               

ብርሀኑ አየለ አክሊሉ-Birhanu Ayele Aklilu

ብርሀኑ አየለ አክሊሉ-Birhanu Ayele Aklilu የማስታወቂያ ሰው-ብርሀኑ አየለ የዚህ ታሪክ አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን እናወጣለን፡፡ በ tewedajemedia gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ...

                                               

አለምሰገድ አበበ

አለምሰገድ አበበ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በፊልም ፤ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እናስተዋውቃለን፡፡ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ5 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ ከሚድያ ዘርፍ ታሪኩ የሚቀርብለት ሰው አለምሰገድ አበበ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብቸኛው የጥናትና ምርምር ፕሮግራም አዘጋጅ አለምሰገድ አበበ ትውልድ ና ልጅነት ተወልዶ ያደገው በአሰላ ከተማ ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1990 ...

ኢትዮጵያ
                                     

ⓘ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ወይም በይፋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።

አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ-ዓመት የሚያንስ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ-ነገሥታት እና ንግሥተ-ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ-ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ League of Nations አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ-አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።

የዛሬዋ ኢትዮጵያ የትልቅ የግዛት ለውጥ ውጤት ናት። ከሰሜን ግዛቱዋ በጣም የተቀነሰ ሲሆን በደቡብ በኩል ደግሞ ተስፋፍቷል። በ ፲፱፻፷፯ 1967 ዓ.ም.፣ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ፣ የእርስ በርስ ጦርነት በሀገሩ ተባባሰ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ በተለያዩ የመንግሥት አይነቶች ተዳድራለች። ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት African Union እና የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ መቀመጫ ናት። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከአፍሪካ ኃያል ሠራዊቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪቃ የእራሷ ጥንታዊ ፊደል ያላት ሀገርም ናት።

ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላት ሀገር ናት። ከአፍሪካ ትላልቅ ተራራዎች እንዲሁም ከዓለም ከባህር ጠለል በታች በጣም ጥልቅ ከሆኑ ቦታዎች አንዳንዶቹ ይገኙባታል። ሶፍ ዑመር ከአፍሪካ ዋሻዎች ትልቁ ሲሆን ፣ ዳሎል ከዓለም በጣም ሙቅ ቦታዎች አንዱ ነው። ወደ ሰማንኒያ የሚቆጠሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ከእነዚህም ኦሮሞና አምሀራ በብዛት ትልቆቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በኣክሱም ሓውልት፣ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በተሰሩ ቤተ-ክርስትያኖቹዋ እና በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶቹዋ ትታወቃለች። የቡና ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢትዮጵያ ሲሆን ሀገሪቱዋ በቡናና ማር አምራችነት በአፍሪካ ቅድሚያ ይዛለች።

ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስቱ ትላልቅ የአብርሃም ሀይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት አላት። ክርስትናን በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተቀብላለች። ከሕዝቡ አንድ ሁለተኛው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ነው። የመጀመሪያው የእስላም ሂጅራ ወደ ኢትዮጵያ ነው የተከናወነው። ነጋሽ በአፍሪካ የመጀመሪያው የእስላም መቀመጫ ናት። እስከ ፲፱፻፸ ዎቹ ድረስ ብዙ ቤተ-እስራኤሎች በኢትዮጵያ ይኖሩ ነበር። የራስ ተፈሪ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በትልቅ ክብር ነው የሚያያት።

ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ድህነት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ሰማኒያ አምስት ከመቶ በላይ የሚሆነው የአባይ ወንዝ ውሀ ከሀገሩ የሚመጣ ቢሆንም በ ፲፱፻፸ ዎቹ በተከሰቱ ድርቆች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ያንን ካሳለፈች በኋላ ሀገሪቱዋ አዲስ መንገድ በመፈለግ ላይ ትገኛለች።

ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ትርጉሙንና አመጣጡን ለመመርመር በ፲፱፻፹፩ 1987 እ.ኤ.አ. በወጣው ሰምና ወርቅ በተባለው የምርምር መጽሔት ፪ኛ ዓመት፣ ቁጥር ፬ አጥር ያለ ጽሑፍ አቅርበን፣ አንዳንድ ምሁራን፤" ኢትዮጵያ ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመጣ ቃል፣ ‘ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ’ ማለት ነው.” የሚሉት ትክክል እንዳልሆነ ለማሳየት፤ ናይጀርያ የሚባል አገርና፣ Nigeria ኒጀር Niger የሚባሉ አገርና ወንዝ በአፍሪካ እንዳሉ ጠቅሰን፣ ኔግራ፣ ኔግሮ፣ ኒገር፣ ኔግሪትዩድ ለሚሏቸው ቃላት ወደ ላቲን/እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመግባት ምክንያት ሆኑ እንጂ፣ ከላቲን ቋንቋ ተወስዶ ለአፍሪካ አገሮችና ወንዝ የተሰጠ ስም አይደለም በማለት፣ ኢትዮጵያ የሚለውም ቃል እንዲሁ ጥንታዊ ምንጩ ከግሪክ ሳይሆን ከአገራችን የወጣ ቃል መሆኑን ለመግለጽ ሞክረን ነበር።

አንድ-አንድ ቃላትን ስንመረምር በውስጣቸው የተደበቅ ምስጢር እናገኛለን። የተደበቀውን ምስጠር ለማግኘት ጥልቅ የታሪክና የቃላት ምርምርና ጥናት Philology / Etimology ማድረግ ያስፈልጋል። በብዙ ምርምርና ጥናትም ምስጢሩ የሚገለጥበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ በግዕዝ፣ በትግርኛና፣ አማርኛ ‘አነ’፣ ‘እኔ’ የሚሉ ቃላት ስናገኝ፣ በላቲን/በእንግሊዝኛ ደግሞ ‘አይ’ I - እንግሊዝኛ፣ ‘ኢዮ’ Io -ጣልያንኛ አሏቸው። በግዕዝ፣ ትግርኛና፣ አማርኛ ‘ዓይን’ ‘ዓይኒ’ ለሚሉ ቃላት ደግሞ፣ በእንግሊዝኛ አይ eye እናገኛለን። በአማርኛና ትግርኛ፤ ‘ያለቀለት ጉዳይ’ ለማለት ‘ሙት፣ የሞተ ነገር’፣ ስንል በእንግሊዝኛ ‘ሙት ኢሹ’ moot issue ይላሉ። በግዕዝና፣ ትግርኛ፣ ‘መርዓ’ ስንል፣ በእንግሊዝኛ marriage ‘መረጅ’ ይላሉ። ፈርኦን Pharaoh ከሚባል ጥንታዊ የግብፅ ንጉሥም ወደ ግዕዝ፣ ትግርኛና አማርኛ፣ እንዲሁም ወደ እንግሊዝኛ ቃላት፤ ‘ፈሪሃ’ ‘ፍርሓት’ ‘fear’ ፊር ለሚሏቸው ቃላት ምንጭ የሆነ ይመስላል። ንጉሡ ታላቅና የሚፈራ የነበረ ነው የሚመስል። እነዚህን ለምሳሌ አቀረብን እንጂ እንደዚህ ብዙ የቃላት መቀራረብ እናገኛለን።" ከማን ወሰደ? ታሪካዊ አመጣጡና አወራረዱስ እንዴት ነው?” የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ነው የቃላት ጥናትና ምርምር የሚያስፈልግ።

አንድ-አንድ ቃላትም ከቋንቋችን ፈልቀው ይወጡና ዓለምን ዞረው ተመልሰው ሲመጡ ብርቅ አድርገን እንቀበላቸዋለን። ለምሳሌ በኃይለሥላሴ ዘመን ያኔ ልዕልት ፀሓይ ሲባል ከነበረው ሆስፒታል ጎን አዲስ የሕንፃ ኮሌጅ ተከፍቶ፣ ‘የመሃንድስ ኮሌጅ’ በመባል ይታወቅ ነበር። መሃንድስ ማለት ምን ማለት ነው? መሃንድስ ማለት መሃናስ/መሃንዳሰ ከሚል የዓረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን፣ እርሱ ደግሞ ሃነፀ፣ ይሃንፅ፣ ማነፅ፣ ማሕፀን ሕፃን የሚታነፅበት ቦታ. ወዘተ ከሚሉ የግዕዝ፣ የትግርኛና፣ የአማርኛም ቃላት ይዛመዳል። እንግዲያውስ ማነፅ ከሚለው ቃል መሃንዳስ ሆኖ ተጣመመና፣ ከዚያም መሃንድስ ተብሎ፣ ዞሮ ተመልሶ ብርቅ ቃል ሆኖብን ለሕንፃ ኮሌጀ መጠሪያ ሆነ። አሁንም ቢሆን ኢንጂኔር ለማለት መሃንድስ ሲባል እንሰማለን።

ሌላም ቃል ፋጡማ/ፋጢማ የሚል ስም ስንመለከት፣ ከነብዩ ሙሓመድ ሴት ልጆች ለአንዷ የተሰጠ መጠሪያ ነበረ። በዓረብኛ አባባል ግን ጠ/ጸ የሚለው ሳይሆን ተ የሚለው ፊዴል ድምፅ ነው። ይህም ማለት፣ ቃሉ" ፈቲማ” ብለው ሲሉ፣ ትርጉሙም፡ ፍጽምት፣ Perfect ማለት ነው። ስለዚህ ፈቲማ ማለት፣ ፈጺማ ትግረኛ ፈጸመች አማርኛ ማለት ነው።

ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ሰምና ወርቅ በተባለው የምርምር መጽሔት 1987 እ.ኤ.አ. ያቀረብነው፣" ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ትርጉሙ ምን ማለት ነው? ኢትዮጲስ የሚባለው ንጉሥስ ለምን ይህ ስም ተሰጠው. ብለን በጠየቅንበት ጊዜ አጥጋቢ መልስ ባለማግኘታችን ቋንቋ ለሚመረምሩ liniguists እንዲያተኩሩበት በዚሁ እንተወዋለን” በማለት ምርምሩን ደመደምነው። ይሁንና ካለፉት ሃያ አምስት ዓመታት እስከ ዛሬ የቀረበ መልስ ስላላገኘንና፣ ጥያቄውም በአዕምሮአችን ሲብላላ ስለቆየ፣ የዚህ ጥያቄ መልስ ይህ ይመስላል ብለን የደረስንበትን ጭብጥ በዚህ የምርምር ጽሑፍ ለማቅረብ ተነሳን።

‘ፐ’ ‘ጰ’ ‘ጠ’ ‘ተ’

በመጀመሪያ Αιθιοπία ‘አይትዮፕያ’‘ኢትዮጵያ’ የሚሉ ቃላት ለመሆኑ የአገራችን ቃላት ናቸው ወይ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ለመሆኑ ከግዕዝ፣ ከአማርኛና፣ ከትግርኛ ቋንቋዎች" ጰ” ወይም" ፐ” የሚል ፊዴል ያላቸውን ቃላት ብንፈልግ ምን እናገኛለን?

በግዕዝፅ በትግርኛና በአማርኛ ፖሊስ ከሚል ቃል ሌላ ‘ፐ’ ፊዴል ያለበት ምን ቃል አለ? ምንም ያለ አይመስለንም። የአገራችን ሰውም ፓሊስ ከማለት ‘ቦሊስ’ ማለት ነው የሚቀናው፥ ኢትዮጵያ ከማለትም ይጦብያ ማለት ይቀልለዋል። ‘ፐ’ እና ‘ጰ’ የሚባሉ ፊዴላትም ወደ አገራችን የፊዴል ሰነድ የገቡት በቅርብ ጊዜ ከመሆኑም በላይ፥ የውጭ ቃላትን ለመጻፍ እንዲያመቹ ተብሎ መሆኑ ግልጽ ነው። በፊደላት ሰንጠረጅም ከሁሉ በታች፣ ወይም ከመጨረሻ ቦታ መስፈራቸው ኋላ የመጡ ለመሆናቸው ተጨማሪ ማስረጃ ነው።

Trapezium‘ጰ’ የሚል ፊዴል ያላቸውን ቃላት የአገራችን ቋንቋዎች ብንፈልግም፤ ጴጥሮስ፣ ጳውሎስ፣ ቆጵሮስ፣ ጠረጴዛ ወዘተ. እናገኛለን። ይሁንና እነዚህ ሁሉ የውጭ ቃላት፣ ከመካከለኛው ምስራቅና ከኤውሮጳ የገቡ እንጂ የአገራችን ቃላት አይደሉም። ‘ጠረጴዛ’ የሚል ቃልም ትራፔዞይድ trapezoid: a rectangular shaped object ከሚለው የላቲን/የእንግሊዝኛ ቋንቋ የተገኘ እንጂ በመሰረቱ የአማርኛ ቃል አይደለም። በጥንታዊ ግዕዝ ጽሑፍም ስንመለከት፤ ‘ክሊዎፓትራ፣ የፕቶሎሚ ልጅ’ ለማለት፤" አከልኡበጥራ፣ ወለተ በጥሊሞስ” ይላታል። ይህ የሚያሳየው" ፐ” የሚባል ፊዴል በጥንታዊ የአገራችን ቋንቋዎች ፈጽሞ እንዳልነበረ ነው። ክሊዎፓትራና አባቷ ፕቶሎሚ ግን ዘራቸው ግሪክ፣ ታላቁ እስክንድር ግብፅን አሸንፎ ከዚያው በኋላ ተክሏቸው የሄደ የግሪክ ገዢዎች ስለሆኑ፣ ስማቸው የግሪክ ስም ነው። ‘ፐ’ የሚል ፊዴልም አለበት።

ይህንን የፊዴላት ጥያቄ ያመጣነው ጥንታዊው የሁለቱ ነገሥታት ስም አጠራር ‘ኢትዮጲስ’ ወይም ‘ኢትዮፒስ’ ሊሆን እንደማይችል ለማስረዳት ነው። እንግዲያውስ ከዚህ የቃላት ምርምር የምናገኘው ነገር ካለ ይኽ ነው፤ በትክክለኛው ጥንታዊ አባባል ኢትዮጲስ፣ ኢይቶጲስ፣ ኢቶፒስ፣ አይቶፒስ. የሚሉ ስሞች ፈጽሞ የአገራችን ንገሥታት ስም ሊሆኑ እንደማይችሉ ነው።

ስለ ‘ጠ’ ፊዴል ካነሳን ደግሞ በግሪክ ቋንቋና በሌሎችም የኤውሮጳ ቋንቋዎች ‘ጠ’ የሚል ድምፅ የላቸውምና ‘ጠ’ የሚለውን በ ‘ተ’ እና ‘ፐ’ በሚሉ ፊዴላት ይተኳቸዋል። እንግዲያው ትክክለኛው አባባል ‘ይቶፒስ’ ሳይሆን" ይጦብስ” መሆን ይገባዋል እንላለን። ግሪኮች ‘ጠ’ ማለት ስላልቻሉ ነው Αιθιοπία ‘አይትዮፕያ’ ያሉት። እኛም ይኸው እስከ ዛሬ ኤውሮ‘ፓ’ ከማለት ኤውሮ‘ጳ’ እንደሚቀናን ማለት ነው።

የውጭ ታሪክ ጸሓፊዎች እነ ዮሴፍ ሃለቪ Josph Halevi፣ እኖ ሊትማን Enno Litman፣ ኤድዋርድ ግላሴር Edward Glaser፣ ኮንቲ ሮሲኒ Conti Rossini፣ ጂ. ሪክማንስ G. Rickmans የመሳሰሉትና ሌሎችም የውጭ አገር ሰዎች ያቀረቡት ጽሑፍ ይጦብያ ለማለት ስላልቻሉ ይቶፕያ፣ ኢቶፕያ፣ ሆኖ ወደ ቋንቋችን ሲተረጐም ‘ኢትዮጵያ’ ተብሎ ሊጸና ቻለ እንጂ ይህ ስም ትክክለኛ የአገራችን ይሁን የንጉሦቻችን ስም እንዳልሆነ ግልጽ ነው።

በአገራችን ታሪክ የምናገኘው ሓቅ ደግሞ፣" ይጦብያ”፣" ይጦብስ” የሚል ስም ለሕዝብና ለአገር ቀርቶ ለተራ ንጉሥም የማይሰጥ እንደ ነበረ ነው። ሕዝቡ ነገደ አግዓዝያን፣ አገሩ ብሔረ አግዓዚ፣ ቋንቋው ልሳነ ግዕዝ ነበር። ነገሥታቱም በየክፍለ-ሃገሩ ስም፤ የትግራይ ንጉሥ፣ የወሎ ንጉሥ፣ የጎጃም ንጉሥ፣ የሸዋ ንጉሥ. ወዘተ፣ ይባሉ ነበር።" ይጦብያ” ተብሎ የሚታወቀው ሁሉን የጠቀለለ ንጉሠ-ነገሥቱ ብቻ ነበር። ይህም የጥንቱን የይጦብስ ንጉሥን ጠቅላይ ስም ወራሽነት መያዙ ለማሳየት ሆን ብሎ የተደረገ ብልሓት ይመስላል።

ይጦብስ ማለትስ ምን ማለት ነው? በግዕዝ በትግርኛና በአማርኛም" መጥበስ” የሚል ቃል አለ። ቃሉም ሲራባ፤ ጠበሰ፣ ተጠበሰ፣ ይጠብስ፣ ትጠብስ፣ ጥቡስ፣. ወዘተ፣ እያለ ይራባል። እንግዲያውስ ይጦብስ ማለት ጥንታዊ ትርጉሙ፤ ይጠብሳል፣ ያቃጥላል፣ ኃይለኛ ንጉሥ ነው! ተብሎ ጠላቶችን ለማስፈራሪያ የወጣ ስም ይመስላል እንጂ ከግሪክ ቋንቋ ተወስዶ ለአገራችን ነገሥታት ‘ፊቱ የተጠበሰ፣ በፀሓይ የተቃጠለ’ ተብሎ የተሰጠ ስም ነው ማለት አይቻልም።

ይህንን የምንለው ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከግሪኮች የመጣ ነው ለሚሉት አጉል ምሁራን ስሕተታቸውን ለማሳየት ነው እንጂ፣ በየዘመናቱ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ልዩ-ልዩ ትርጉሞች እንደ ተሰጡት አይጠረጠርም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ማለት መልካም መዓዛ ያለው ዕጣን ነው የሚሉ አሉ። የለም፣ ታላቅና ጠቅላይ ማለት ነው የሚሉም አሉ። ከዘመናት ብዛትልዩ-ልዩ ትርጉሞች እንደተሰጡት አያጠራጥርም። የሚደንቀው ነገር ግን መሃነስ/መሃንደስ የሚል ቃል ዓለምን ዞሮ ወደኛ መሃንድስ ሆኖ ሲመለስ ህንፃ የሚለውን ትርጉሙን እንዳልሳተ፣ ‘ይጦብስ’ የሚለውም ቃል እንዲሁ የቃሉ አባባል ትንሽ ተወላግዶ በግሪኮች አነጋገር ‘ይቶፒስ’ ቢባልም የመቃጠልና የመጠበስ ትርጉሙን ሳይስት እንደ ተቀመጠ ለብዙ ዘመናት የቆየ ይመስላል።

እዚህ ላይ ‘ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?’ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ምናልባት በይጦብስ ዘመን የአገራችን ተጓዦች ወይም ነጋዴዎች ከግሪክ ሰዎች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ፤

እናንተ እነማንናችሁ?”ብለዋቸው ይሆናል።" የይጦብስ ሰዎች ነን”፣ብለው መልሰዋል።" ይጦብስ ማለትስ ምን ማለት ነው?” ብለው ሳይጠይቋቸው አልቀሩም።" የሚያሳርር፣ የሚያቃጥል፣ የሚጠብስ ኃይለኛ!” ማለት ነው ብለው አስረድተዋቸዋል።

ከዚያ ወድያ ግሪኮችጠቆር ያለውን ሰው ባዩ ቁጥር Αιθιοπίs" ይጦብስ” እያሉ መጥራት ጀምረው፣ ቃሉም ወደ ቋንቋቸው ከመግባቱም በላይ፣" ይጠብስ” የሚለውን ጥንታዊውን ትርጉም ሳይስት ለጥቁር አፍሪካዊ ሁሉ ‘ፊቱ የተጠበሰ፣ በፀሓይ የተቃጠለ’ Αιθιοπία ‘ኢትዮጵያ’ የሚል መጠሪያ ለመሆን የበቃ ነው የሚመስል።

                                     

1.1. ታሪክ ቅድመ ታሪክ

ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የሰው ልጅ ከነበረባችው ቦታዎች አንዷ መሆኗ ትታወቃለች። የሰው ፍልሰት ጥናቶች ፣ የቅሪተ አካል ጥናቶችና ሌሎች የሳይንሳዊ ዘዴዎች ይህን ያረጋግጣሉ። ድንቅነሽ የምትባለው በአፋር ክልል ውስጥ የተገኘችው አጽም በአለም በዕድሜ ሁለተኛ ጥንታዊ ናት። ከ 3.2 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ እንደኖረች ይገመታል። ሌሎችም ታዋቂ አጽሞች በኢትዮጵያ ተገኝተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ደሴት በመሆን የቆየች ታላቅ ሀገር ናት።

                                     

1.2. ታሪክ የመጀመሪያዎቹ መንግስታት

በ ፰፻ 800 ዓመተ-ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ። በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ 400 ዓመተ-ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር።

የአክሱማውያን ስፈን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠንካራ መንግሥታዊ ማኅበረሰብ ነበር። በፋርስ ፣ ሮማ እና ቻይና ይገኙ ከነበሩ ታላላቅ መንግሥታት በወደረኛነት የሚቆጠር ትልቅ ኅይል ነበር። በ4ኛው ምእተ-ዓመት አክሱም ወደ ክርስትና ተለወጠ። በ፮ ኛው ምእት ዓመት የአክሱማውያን ግዛታዊ ቁጥጥር የዛሬዋን የመን ግዛት ይጨምር ነበር። ግን በ፮ ኛው እና በ ፰ ኛው አምኣት የአክሱም ሥልጣኔ በእስልምና መነሣት እና መስፋፋት ተዳክሞ ለውድቀት በቃ ። ተከታዩ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ልክ በድንገት እንደተነሳ በድንገት ሲያበቃ ፣ ይኵኖ አምላክ ሥልጣን በ ፲፪፻፷፪ 1262 ዓ. ም. ጨበጡ ፤ እንዲያም ሲል የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትን መለሱ። ከዚያም ለብዙ ዘመናት የሰለሞናዊው መንግስት ከጠለ።

                                     

1.3. ታሪክ ከአውሮፓ ጋር የታደሰ ግንኙነት

በ ፲ ፭ ኛው ምዕተ-ዓመት መጀመሪያ ኢትዮጵያ ከአክሱም ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአውሮፓ ጋር ግንኙነት ጀመረች። ከእንግሊዝ ንጉሥ ሄነሪ አራተኛ Henry IV ወደ የአቢሲኒያ ንጉሠ-ነገሥት የተላከ ደብዳቤ እስከ ዛሬ ድረስ አለ። በ1428 እ.ኤ.አ. አፄ ይስሐቅ ወደ የአራጎን ንጉሥ አልፎንዞ አምስተኛ Alfonso V ሁለት መልክተኞች ልከው ነበር። ግን የመጀመራያው ያልተቋረጠ ግንኙነት በአፄ ልብነ ድንግል ስር ከፖርቱጋል ጋር ከ1508 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ነው የተካሄደው።

ኢትዮጵያ በአህመድ ግራኝ ስትጠቃ ፣ ፖርቱጋል አራት መቶ ወታደሮችና የጦር መሳሪያ በመላክ ኢትዮጵያን ረድታለች። አፄ ሱስንዮስ በፖርቱጋልና እስፓንያ ተጽዕኖ እና ተጨማሪ እርዳታ ከመፈለጋቸው የተነሳ ወደ የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ተለወጡ ፤ የኢትዮጵያ ይፋ ሀይማኖትንም አደረገቱት። ይህ ውሳኔ ወደ ግዙፍ ተቃውሞና ጦርነት አመራ። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞቱ በኋላ ፣ የአፄ ሱስንዮስ ልጅ አፄ ፋሲለደስ በ 1632 እ.ኤ.አ. ኢትዮጵያ ወደ አርቶዶክስ ክርስትና መመለሷን አወጁ። አውሮፓውያኖቹንም ከኢትዮጵያ አስወጡ።

                                     

1.4. ታሪክ ዘመነ መሳፍንት

ከ ፲፯፻፶፭ 1755 እስከ ፲፰፻፶፭ 1855 እ. ኤ. አ. ኢትዮጵያ እንደገና ከአለም ጉዳዮች ተገላ ነበር። ይህ ጊዜ "ዘመነ-መሳፍንት" ይባላል ምክኒያቱም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥቶች በራስ ሚካኬል ስሁል ፣ ራስ ወልደ ሥላሴ ፣ ራስ ጉግሳ እና በመሳሰሉት ቁጥጥር ስር ነበሩ። ራስ ጉግሳ በ፲፯ ኛው ክፍለ ዘመን ጎንደርን በመምራታቸው የቤተ-መንግሥቱን ቋንቋ ከአማርኛ ወደ ኦሮምኛ ለውጠው ነበር።

የኢትዮጵያ ግለልኘነት ያበቃው ከእንግሊዝ ጋር ግንኙነት ስትጀምር ነው። ኢትዮጵያ እንደገና የተዋሀደችው እንዲሁም የዘውዱ ስልጣን የተጠናከረው በ ፲፰፻፶፭ 1855 እ. ኤ. አ. በአፄ ቴዎድሮስ ምክኒያት ነው። የሰሜን አሮሞዎችና ትግሬዎች አመፅና የግብፆች ተደጋጋሚ ድንበር መጣስ የአፄ ቴዎድሮስ ስልጣን እንዲዳከም አደረጉት። በመጨረሻም ከእንግሊዝ ጋር በነበረው ጦርነት እስረኛ አልሆንም ብለው አፄ ቴዎድሮስ እራሳቸውን አጠፉ። በ ፲፰፻፷፰ 1868 እ. ኤ. አ. ኢትዮጵያና ግብፅ ጉራ በሚባለው ቦታ ተዋጉ። በአፄ ዮሐንስ አራተኛ የተመሩት የሰሜን ኢትዮጵያ ኃይሎች ድል ተቀናጁ።

በ ፲፰፻፹፱ 1889 እና በ ፲፰፻፺ 1890 ዎቹ እ.ኤ.አ. መጀመሪያ ፣ የሸዋ ንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ከዚያም ዳግማዊ አፄምኒልክ በራስ ጎበና እርዳታ አማካኝነት ሀገሯን ወደ ደቡብና ምሥራቅ ማስፋፋት ጀመሩ። ከአህመድ ግራኝ ወረራ በኋላ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር ያልነበሩ ፣ ሌሎች ደግሞ በማንኛው ጊዜ በኢትዮጵይ ቁጥጥር ስር ያልነበሩ ቦታዎች በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አገዛዝ ጊዜ በኢትዮጵያ ስር ሆኑ። ከዚህ ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ ድንበር ብዙ አልተለወጠም። ከ ፲፰፻፹፰ 1888 እስከ ፲፰፻፺፪ 1892 እ. ኤ. አ. ድረስ የነበረው የሰፋ ድርቅ ከኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ሶስተኛ የሚገመተውን ቀጥፎአል።                                     

1.5. ታሪክ የአውሮፓ ሽሚያ ለአፍሪካ

በ ፲፰፻፹ 1880 ዎቹ እ. ኤ. አ. የአውሮፓ መንግሥቶች በበርሊን ጉባኤ ተስማምተው አፍሪካን በቅኝ ገዢነት መከፋፈል ጀመሩ። በኢትዮጵያ እና ጣልያን መካከል የነበሩ የዚያ ዘመን ውዝግቦች ወደ አድዋ ጦርነት በ ፲፰፻፹፰ 1888 ዓ. ም. አመሩ። በጦርነቱ የጣልያን ትልቅ ዘመናዊ ጦር በኢትዮጵያ ጦር ትልቅ ሽንፈት የደረሰበት መሆኑ ዓለምን አስደነቀ።

                                     

1.6. ታሪክ የግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን

በ ፳ ኛው ምእት ሁለተኛው ሩብ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኢትዮጵያን ከልጅ ኢያሱ በኋላ መምራት ጀመሩ። ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ ሕብረት መቋቋም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

የኢትዮጵያ ነጻነት በጣልያን ወረራ ከ ፲፱፻፴፮ 1936 እስከ ፲፱፻፵፩ 1941 እ. ኤ. አ. ድረስ ቢጠቃም በጀግኖችዋ መከታ ተጠብቋል። በአዚህ ጥቃት ጊዜ ዓፄ ኃይለሥላሴ በ ፲፱፻፴፭ 1935 እ. ኤ. አ. በሊግ ኦፍ ኔሽንስ League of Nations ፊት የሚታወስ ንግግር በአማርኛ አደረጉ። ይህ ንግግር በዓለም ታዋቂ አደረጋቸው። እንዲሁም በ ፲፱፻፴፭ 1935 እ.ኤ.አ. በ ታይም Time መጽሄት "የዓመቱ ሰው" አስባላቸው። ጣልያን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ መሳተፍ ስትጀምር ፣ እንግሊዝ ከኢትዮጵያዊ ተዋጊዎች ጋር ኢትዮጵያን ነጻ አወጣች። ግን እስከ ፲፱፻፵፫ 1943 እ. ኤ. አ. ድረስ አንዳንድ ጣልያኖች በደፈጣ ያለ ስኬት ይዋጉ ነበር። በ ፲፱፻፵፪ 1942 እ. ኤ. አ. ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባርነት እንደ ተከለከለ አወጁ።

ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ጀግና ሆነው ቢታዩም ፣ የ ፲፱፻፸፫ 1973 እ.ኤ.አ. ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ፣ የምግብ ዕጥረትና የድንበር ጦርነቶች ተቃውሞ አስነሱ። ከዚያም በ ፲፱፻፸፬ 1974 እ. ኤ. አ. በሶቪየት ሕብረት የተደገፈውና በመንግስቱ ኃይለ ማርያም የተመራው ደርግ ማለት ኮሚቴ ማለት ነው ዓፄ ኃይለ ሥላሴን ከስልጣን አስወረደ።

                                     

1.7. ታሪክ ኮምዩኒዝም

የተለያዩ መፈንቅለ መንግሥቶች ፣ የሰፋ ድርቀትና ስደተኞች የደርግ ሥርዓት ትልቅ ችግሮች ነበሩ። በ ፲፱፻፸፯ 1977 እ. ኤ. አ. ሶማሊያ ኦጋዴንን በመውረሯ የኦጋዴን ጦርነት ተነሳ። በሶቪየት ሕብረት ፣ ኩባ ፣ ደቡብ የመን ፣ ምስራቅ ጀርመንና ሰሜን ኮሪያ የመሳሪያ እርዳታ እንዲሁም ወደ ፲፭ ሺህ በሚቆጠሩ የኩባ ወታደሮች ድጋፍ አማካኝነት ደርግ ኦጋዴንን እንደገና መቆጣጠር ቻለ።

በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በቀይ ሽብር ፣ የግዴታ ስደት ፣ ወይም ረሀብ ሞተዋል። መንግስቱ ቀይ ሽብር ያካሄደው በተቀዋሚዎች በተፈጸመው ነጭ ሽብር መልስ እንደሆነ ጠቅሷል። በ ፳፻፮ 2006 እ. ኤ. አ. መንግስቱ ኃይለ ማርያም በሌሉበት የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል።

በ ፲፱፻፹ 1980 ዎቹ መጀመሪያ የተከሰቱ ድርቀቶች ምክኒያት ስምንት ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ሲራብ ፣ አንድ ሚሊዮን ደግሞ ሞተዋል። ተቃውሞ በትግራይና ኤርትራ ክልሎች ተስፋፋ። በ ፲፱፻፹፱ 1989 እ. ኤ. አ. ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከሌሎች እንቅስቃሴዎች ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን መሠረተ። የሶቪየት ሕብረትም ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ መቀነስ ጀመረች። የኢኮኖሚ ችግሮች ተከሰቱ ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ተዳከመ።

በሜይ ፲፱፻፺፩ 1991 እ. ኤ. አ. የኢ. ህ. አ. ዴ. ግ. ጦር ወደ አዲስ አበባ አመራ። የመንግስት ኃይሎች ምንም አይነት የውጭ እርዳታ ስላላገኙ ፣ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.ን ጥቃቶች መቋቋም አልቻሉም። መንግስቱ ኃይለ ማርያም ወደ ዚምባብዌ ሄደው እስከ ዛሬ ድረስ በዛችው ሀገር ይኖራሉ። ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ፹ ፯ አባላት ያሉት የሽግግር መንግሥት መሠረተ። በጁን ፲፱፻፺፪ 1992 እ. ኤ. አ. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፣ እንዲሁም በማርች ፲፱፻፺፫ 1993 እ. ኤ. አ. የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት የሽግግር መንግሥቱን ለቀው ወጡ። በ ፲፱፻፺፬ 1994 እ. ኤ. አ. ሁለት የሕግ አውጪ ምክር ቤቶችንና የፍትሕ ስርዓትን የሚደነግግ አዲስ ሕገ መንግሥት ተፃፈ። የመጀመሪያው ምርጫ በሜይ ፲፱፻፺፭ 1995 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። አቶ መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።                                     

1.8. ታሪክ በቅርብ ጊዜ

በየተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ኢትዮጵያና ኤርትራ በፌደሬሽን ተዋህደው ነበር። በ ፲፱፻፺፫ 1993 እ.ኤ.አ. በተካሄደውና የተባበሩት መንግሥታት በታዘበው ሕዝበ ድምፅ ፣

በወቅቱ ስልጣንን በጠመንጃ አፈሙዝ የያዙትና የኤርትራን መገንጠል በሚፈልጉት በህውአትና ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አማካይነት ለኤርትራ ህዝብ ‹ባርነት› ወይንስ ‹ነፃነት› ተብሎ እንዲመርጡ ተገደው ማንም ባርነትን የሚመርጥ የለምና ነፃነትን መረጡ ተባሎ በረሃ ገብተው ሲታገሉለት የነበረውን አላማ ስልጣናቸውን በመጠቀም አስፈፅመው ከ ፺፱ ከመቶ በላይ የሚሆነው የኤርትራ ሕዝብና በውጭ ሀገር የነበሩ ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ መገንጠልን መርጠዋል። በሜይ ፳፬ ፣ ፲፱፻፺፫ 1993 እ. ኤ. አ. ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነፃነቷን አወጀች።

በሜይ ፲፱፻፺፰ 1998 እ. ኤ. አ. የድንበር ውዝግብ እስከ ጁን ፳፻ 2000 እ. ኤ. አ. ወደ ቀጠለው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አምርቶአል። ይህ ጦርነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን ጎድቶአል። በሜይ ፲፭ ፣ ፳፻፭ 2005 እ.ኤ.አ. አጠቃላይ ምርጫ ቢካሄድም ተቃዋሚዎች ማጭበርበር እንደነበረ ወንጅለዋል። በአጠቃላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከ ፪፻ 200 በላይ የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸንፈዋል። ግን አንዳንድ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባሎች ከምርጫው በኋላ ከነበረው ረብሻ ጋር በተያያዘ ታስረው ነበር። በአሁኑ ጊዜ ያለው የፖለቲካ ስርአት በብሄር ላይ የተመሰረተ ፌደራላዊ ስርአት ነው፡፡

                                     

2. መልክዓ-ምድር

ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ከ 3-14 ዲግሪ ሰሜን እና ከ 33-48 ዲግሪ ምሥራቅ የምትገኝ አገር ስትሆን የቆዳ ስፋቱዋም 1.127.127 ካሬ ኪ.ሜ. ነው። በሰሜን ከኤርትራ ፣ በምዕራብ ከሱዳንና ደቡብ ሱዳን ፣ በደቡብ ከኬኒያ ፣ እንዲሁም በምሥራቅ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ ጋር ትዋሰናለች። የኢትዮጵያ አብዛኛው ግዛት በተራሮች እና አንባዎች የተሞላ ሲሆን ፣ ታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እነዚህኑ ከፍተኛ ቦታዎች ከሰሜን ምሥራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ በመጋደም ለሁለት ይከፍላቸዋል። በስምጥ ሸለቆው ዙሪያም በረሃማ የሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎች ይገኛሉ። ይሄን መሰሉ የመልክዓ-ምድር ልዩነት አገሪቷ የተለያዩ የአየር ንብረት ፣ የአፈር ፣ የዕፅዋት እና የሕዝብ አሰፋፈር ገጽታዎች እንዲኖሯት አስችሏታል። በከፍታና በመልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዓይነት የአየር-፡ ንብረት ክልሎች ይገኛሉ። እነሱም፦

 • ደጋ – ከፍታቸው ከባሕር ጠለል 2400 ሜትር የሚጀምር እና የሙቀት መጠናቸው ከ 16 ዲግሪ ሴ. ግ. የማይበልጥ
 • ቆላ – ከባህር ጠለል በታች ጀምሮ እስከ 1500 ሜትር ከፍታ ያላቸው ፣ የሙቀት መጠናቸውም ከ 30 ዲግሪ ሴ. ግ. እስከ 50 ዲግሪ ሴ. ግ. የሚደርስ አካባቢዎች ናቸው።
 • ወይናደጋ – ከፍታቸው ከባሐር ጠለል ከ 1500 እስከ 2400 ሜትር ፣ ሙቀታቸውም ከ 16 ዲግሪ ሴ. ግ. እስከ 30 ዲግሪ ሴ. ግ. የሚደርስ ፣ እና

ዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ሲሆን ፣ ከሱ ቀደም ብሎ አልፎ የሚጥል የበልግ ዝናብ በየካቲት እና በመጋቢት ይከሰታል። የተቀሩት ወራት በአብዛኛው ደረቅ ናቸው።

ሲዳማ ተጨማሪ ክልል ናት== አስተዳደራዊ ክልሎች ==

ከ ፲፱፻፺፮ 1996 እ.ኤ.አ. በፊት ኢትዮጵያ በ ፲፬ ክልሎች ተከፍላ ነበር። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጽያ ውስጥ ፱ አስተዳደራዊ ክልሎች ይገኛሉ። አወቃቀራቸውም በህገ-መንግስቱ በተደነገገው መሰረት "በህዝብ አሰፋፈር ፤ ቋንቋ ማንነት እና ፈቃድ ላይ" ተመስርቶ ሲሆን ክልሎቹም፦

 • የአማራ ክልል
 • የትግራይ ክልል
 • የሶማሌ ክልል
 • የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል
 • የቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል
 • የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
 • የሀረሪ ሕዝብ ክልል ሲሆኑ በተጨማሪም
 • የኦሮሚያ ክልል
 • ድሬዳዋ እራሳቸውን የቻሉ የአስተዳደር አካባቢዎች ሆነው ተዋቅረዋል።
 • የአፋር ክልል
 • አዲስ አበባ እና
                                     

3. ሕዝብ

ኢትዮጵያ ከ ፹ 80 በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች የሚገኙባት "የብሄረሰቦች ሙዚየም" ልትሰኝ የቻለች ሀገር ነች። ትልልቆቹ ብሄረሰቦች ፣ የአማራ ፣ እና የኦሮሞ የትግራይ እንደሁም የሶማሌ ሲሆኑ እነዚሁ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የሀገሪቷ ሕዝብ ቁጥር ከ 3/4 ኛ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ። በሃይማኖት በኩልም ሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖቶች ክርስትና እና እስልምና በስፋት የሚስተዋልባት አገር ናት። የክርስትና እምነት ተከታዮች ከ 55%-60 % ፣ እስልምና ከ35% እሰከ 40% እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ 5%-8% የሚሆነውን ይይዛሉ።

                                     

4. ቋንቋዎች

ዋና መጣጥፍ፦ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች

በኢትዮጵያ ውስጥ ከ ፹ በላይ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ ፹ በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ናት። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የስራ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩት ቋንቋዎች አፍሮ-ኤስያዊ እና ናይሎ ሳህራዊ በሚባሉ ሁለት ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። በአፍሮ-ኤስያዊ የቋንቋ ቤተሰብ ውስጥም ኩሻዊ፣ ኦሞአዊ እና ሴማዊ የሚባሉ ንዑስ ክፍሎች አሉ።

ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ አፋን ኦሮሞ ፣ ሶማልኛ ፣ አፋርኛ ፣ ሲዳምኛ ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ ከ አባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ ፣ ኩናማኛ ፣ ጉሙዝኛ ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው። እንደ ወላይትኛ ፣ ፣ ጎፍኛ ፣ ከፋኛ ፣ ሃመርኛ የመሳሰሉት የ ኦሞአዊ ቋንቋ ዘሮች ሲሆኑ አማርኛ ፣ ትግርኛ ፣ ጉራጊኛ ፣ ስልጢኛ ፣ ሀደሪኛ፣ አርጎብኛ፣ ጎፍኛ እና መሰል ቋንቋዎች ከ ሴማዊ ቋንቋዎች ይመደባሉ። ዘጋቢ በአወል ሙሀመድ ደራ

                                     

5. ፊደል

የሴሚቲክ ምንጭ ያላቸው እንደ ትግርኛና አማርኛ ያሉት ቋንቋዎች የራሱ የሆነ የተለየ የፊደል ስርአት ያላቸው ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን ከአፍሪቃ ብቸኛዋ ባለ ጥንት ፊደል ሀገር ያደርጋታል። እነኚህ የሴሚቲክ ምንጭ ያላችው ቋንቋዎች ግዕዝ የተባለ በአሁኑ ወቅት ከቤተክርስትያን ውጭ ለዕለት ተዕለት ግልጋሎት ላይ የማይውል ግንድ ዘር አላቸው።

በኣሁኑ ጊዜ ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የቢለን፣ ቤንች፣ ምኢን፣ ሙርሲ፣ ሱሪ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኣውንጂ፣ ኦሮሚፋ፣ ዓማርኛ፣ ዲዚ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ ቋንቋዎች የሚጋሯቸውን ቀለሞችና ሌሎች ያጠቃልላል። በፊደሉ ከሚጠቀሙ ቋንቋዎች መካከል ሓረሪ ኣንዱ ነው። መጽሓፍ ቅዱስ ሙሉዉን ወይም በከፊል ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ ቤቶች ከታተሙባቸው ቋንቋዎች መካከል ሃዲያ፣ ሲዳሞ፣ ከምባታ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ይገኙበታል። ደግሞ ኣበራ ሞላ ይዩ።

በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይቀርብ የነበረው የግዕዝ ፊደል በ፲፱፻፹ ገደማ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ኣጠቃቀሙ ወደ ኮምፕዩተር ዞሯል። ከእዚያም ወዲህ ፊደሉ የዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ ስለገባ እያንዳንዱ ቀለም የእራሱ ስፍራ ኣለው። en:Ethiopic_Unicode_block) ይህ የኣማርኛ ውክፔድያ ድረገጽም የቀረበው በእዚሁ ፊደል ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ፊደሉን በእጅ ስልክ መጠቀም ተችሏል። ለፊደሉ ኣጠቃቀም ኣስፈላጊ ሆነው የተፈጠሩ ኣዳዲስ የቴክኖሎጂ ዘዴዎችም የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት መታወቂያ ወይንም ፓተንት ማግኘት ጀምረዋል።

                                     
 • መንግሥተ ኢትዮጵያ ወይም አቢሲኒያ በዛሬዎቹ ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚገኝ መንግሥት ነበር በትልቅነቱ ጊዜ ሰሜን ሶማሊያ ጅቡቲ ደቡብ ግብፅ ምሥራቃዊ ሱዳን የመንና ምዕራባዊ ሳውዲ አረቢያን ያጠቃልል ነበር ኢትዮቢያየኢትዮ ግዛትያ ግዛት
 • ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ በደርግ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ነበር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ በኅብረተሰባዊነት አብቢ ለምልሚ ቃል ኪዳን ገብተዋል ጀግኖች ልጆችሽ ወንዞች ተራሮችሽ ድንግል መሬትሽ ለኢትዮጵያ
 • ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ መንግስት የበላይ ጠባቂነት የሚንቀሳቀስ የሀገሪቱ ብቸኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው ዜና ስፖርት ሙዚቃ እና የመሳሰሉትን ስርጭቶች ለተመልካቾች ያቀርባል ስርጭቱንም
 • በመቍጠር ሲጀምር ይመስለኛል ኣዲሱ ካለንደር ላይ ሰባት ዓመታት ግድም የጨመረበት የዓመታቱም ቍጥር ከግብጽ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የቀረበ ነው ጨረቃ መሬትን ስትዞርና መሬት ፀሓይን ስትዞር የሚወስዱት 532 ዓመታት 19 X 28 ተደጋጋሚ ናቸው
 • የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲ ነው
 • ብር ETB ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ የምትጠቀምበት ሕጋዊ ገንዘብ ነው 1 ብር ለ100 ሳንቲም እኩል ነው በ1933 ታትሞ የነበረው የኢትዮጵያ 2 ብር በ1932 ታትሞ የነበርው የኢትዮጵያ 100 ብር በ1961 ታትሞ የነበረው የኢትዮጵያ
 • ጳጉሜ የወር ስም ሆኖ በነሐሴ እና በመስከረም ወራት መኻል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ የመጨረሻው እና አሥራ ሦስተኛው ፲፫ ኛው የወር ስም ነው ጳጉሜ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዘመነ ዮሐንስ ሥግር ዓመት
 • የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲ ነው
 • የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር በጠላት ወረራ ዘመን የተመሠረተ ድርጅት ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ያሉት አዛውንት አባላቱ በዚያው የአምሥት ዓመት ትግል ዘመናት መኳንንቱ የጦር መሪዎቻቸውና ንጉሠ ነገሥቱም ጭምር እነዚያን
 • የኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ይገኛል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አባል ሲሆን ዋና ስታዲየሙ አዲስ አበባ ስታዲየም ነው ይህ ስለ ስፖርት ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
 • የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲ ነው
 • የደቡብ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች አንድነት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲ ነው

Users also searched:

እንግሊዘኛ ቋንቋ ለመቻል,

...
...
...