Back

ⓘ ታሪክ                                               

የብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ አጭር የጀግንነት ታሪክ

ማጠቃለያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የማይረሣ የቅድስናና የጀግንነት ታሪክ ማስታወሻ። አርዕስት ፡ የብፁ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ አጭር የጀግንነት ታሪክ ። ምንጭ ፡ ድሬtube channel "All credits goes to Deretube Ethiopia channel" "00:23, 8 ሰፕቴምበር 2019 UTC" ክርስቶስሰምራ አማርኛ

                                               

ሉድ

ሉድ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት የሴም ልጅ የኖህም ልጅ ነበረ። ይህ ሉድ እና ምጽራይም የወለደው ሉዲም ግን ሁለት የተለያዩ ዘሮች ሆነው ይቆጥራል። የሉድ ተወላጆች በዮሴፉስና በሌሎች ጸሐፍት ዘንድ የትንሹ እስያ ሀገር ልድያ አካድኛ፦ ሉዱ ሆኑ። ከልድያም አስቀድሞ በዚያ ዙሪያ ሉዊያ የተባለ አገር ነበር። በ መጽሐፈ ኩፋሌ ድግሞ የሉድ ርስት የሉድ ተራሮች ከአራራት ወደ ምዕራብ፣ በትንሹ እስያ ናቸው። ከዚህ በላይ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ሄሮዶቶስ እንዳለ፣ ልድያ ከንጉሳቸው ከሉዶስ Λυδός ተሰየመች። የአቡሊድስ ዜና መዋዕል 226 ዓ.ም. ገደማ የሉድ ልጆች ላዞኔስ ወይም አላዞኒ ሓሊዞናውያን ሲለን፣ ስትራቦን ሐሊዞናውያን በሐሊስ ወንዝ ላይ ኖሩ በማለት አገኛቸው። ሆኖም በአቡሊድስ ዘንድ፣ "ልድያ" የተባለች አገር ከሉዲም ምጽራይም ወጣች። የእስላም ታሪክ ጸሃፊ ሙሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ 907 ዓ.ም. ገደማ በጻፈው ታሪክ የሉድ ሚስት የያፌት ልጅ ሻክባህ ስትሆን የፋርስና የጅዮርጅያ ዘሮች እንዲሁም ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ወለደ ...

                                               

ባራክ ኦባማ

                                               

ቲራስ

ቲራስ በኦሪት ዘፍጥረት 10 መሠረት የያፌት ታናሽ ወንድ ልጅ ነበረ። በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቲራስ ምንም ተጨማሪ መረጃ ባይጠቀስም፣ በ ኩፋሌ ዘንድ ምድር በተከፋፈለበት ወቅት የቲራስ ርስት በውቅያኖስ ውስጥ 4 ታላላቅ ደሴቶች ሆነ። የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ ዮሴፉስ 1ኛው ክፍለ ዘመን በጻፈው ታሪክ ዘንድ፣ ቲራስ የ "ጢራስያውያን" አባት ሆነ። እነዚህ በኋላ ስማቸው ጥራክያውያን እንደ ተባለ ይነግረናል። ጥራክውያንም በጥንታዊ ዘመን "ነበልባል ቀለም" ቀይ ወይም ወርቃማ ጸጉር ያለው ብሔር መሆናችውን ግሪኩ ጸሐፊ ዜኖፋኔስ 6ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. መሰክሯል። በጥንታዊ ዘመን "ቲራስ" የድኒስተር ወንዝ ስም ነበር። በዚህም ወንዝ አፍ የግሪክ ቅኝ አገር ቱራስ ይባል ነበር፤ በዙሪያውም ቲራጌታያውያን ይኖሩ ነበር። ከጥራክያውያንም ክፍሎች አንዱ ጌታያውያን ተብለው ይታወቁ ነበር ሄሮዶቱስ 4.93፣ 5.3 እና ሌሎች ጸሐፍት። በግሪኮች ዘንድ፣ የጥራክያውያን አባት ስም ጥራክስ ነበረ። በአንዳንድ ሊቃውንት ዘንድ፣ ይህ "ቲራስ ያፌት" በዘሮ ...

                                               

ሞሳሕ

ሞሳሕ በኦሪት ዘፍጥረት ዘንድ የያፌት ልጅ የኖህም ልጅ ነበረ። በመጽሐፈ ኩፋሌ ደግሞ ስሙ "ሞስክፍ" ፣ "ሞሳኮ" ተጽፎ ይታያል። በአይሁድ ታሪክ ጸሐፊው ፍላቪዩስ ዮሴፉስ መሠረት 1ኛው ክፍለ ሸመን የጻፈ፣ ከሞሳሕ የተወለደው ሞሶኬኒ የተባለ ብሔር ነበር። "አሁን ቀጴዶቅያውያን ሲሆኑ የከተማቸው ስም ማዛካ የቀድሞ ስማቸው ትዝታ ነው" ብሎ ጻፈ። ይህም ብሔር ለጥንት ግሪካውያን ጸሐፍት ከ550 ዓክልበ. ጀምሮ "ሞስኮይ" ተብሎ ይታወቅ ነበር። ያንጊዜ የሞስኮይ ሕዝብ በአሁኑ ቱርክ፣ ጂዮርጂያና አርሜኒያ አገራት ውስጥ እንደ ኖረ ጻፉ። ከዚያ በፊት፣ ከአሦራውያን ጎረቤቶች መካከል ሲሆኑ ሙሽኪ በሚል ስያሜ ይታወቁ ነበር። እኚህ ሙሽኪ በአሦር ንጉሥ 2 ሳርጎን ዘመን 700 ዓክልበ. ግድም በኪልቅያ በደቡብ አናቶሊያ ሲገኙ የታባል መንግሥት ተባባሪዎች ነበሩ። ሙሽካውያን እና ታባላውያን በ1190 ግድም የኬጥያውያን መንግሥትን ወርረው ያፈረሱት ናቸው። ሌላ ስማቸው "ብሩጊ" ሲሆን ከመቄዶን አውሮጳ ወደ ትንሹ እስያ ተሻግረው ከ "ብሩጊ" ወደ "ፍሩጊ ...

                                               

አዘዞ

ስለ አዘዞ ከተማ የሚያመለክት ትንሽ ሃተታ አዘዞ የተባለችው ከተማ በሽማግሌዎችና ሊቃውንት አንደበት ሲነገር የነበረው አፈ ታሪክ የስሟ ትርጓሜ አንዲህ ነው፡፡ ይህች አዘዞ የተባለች ከተማ የጎንደር ነገስታት በሞቱ ጊዜ ይቀበሩባት ነበር፡፡ የን ግዜም ሲሞቱ የትዕዛዛቸውና የኑዛዜአቸው ቃል ከመቃብረ መንግስት መዝገብ ውስጥ እንዲገኝ እያሉ ከሞቱ በኋላ የሚሆነውን የኑዛዜአቸውንና የትዕዛዛቸውን ቃል ስለሚያስቀምጡበት ያዘዙበት ወይም የተናዘዙበት ቦታ በማለት ፈንታ ከዘመን ብዛት አዘዞ ተባለች እንጂ ጥን ስሟ አዝዞ ወይም ተናዝዞ ሞተ ማለት ነው፡፡ ምንጭ፡ አባ ጋስፖሪኒ ጉማ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፤ ከረጅሙ ባጭሩ የተውጣጣ፡፡

                                               

የሙፍቲ ዳውድ የህይወት ታሪክ

አል-ጀበርት የአርጎብኛ ቋንቋ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት/ Al Jebert Argobban languege School ሙፍቲ ዳውድ ሀበሾችን’ና ኢማም አል-ሻፊዒይን ያስተሳሰረ የአርጎባ_ዓሊም ▂▂▂▂▂{ውዱ ታሪካችንን ያንብቡት}▂▂▂▂▂ ታሪካችን በታላላቅ ኢስላማዊ ስብእናዎች ያሸበረቀ፤ በጠካራዎቹ ሙእሚኖች አስደናቂ ገድል የተሞላ ነዉ፡፡ ከነዚህ ልብን ከሚነኩ’ና ስለ ማንነታችን ቆም ብለን እንድናስብ ከሚጋብዙን ነገር ግን በእጅጉ ከተረሱ ታኮቻችን ዉስጥ አንዱን አነሆ!! ከ300 ኪታብ በላይ በእጃቸዉ የፃፉ የአርጎባ ዓሊም፤ለዚህም ገና የመን ዘቢድ ትምህርት ላይ እያሉ የሐበሻ ሙፍቲ ሸምሰል ሀበሻ ባሕሩ ራሕመቲ ኢማሙ አዕዞም ፊል ሀቂቀት ተብሎ የተመሰከረላቸዉን ታዋቂዉ ዓሊምና ምሁር የሐጂ ሙፍቲ ዳዉድን የሂይወት ታሪክ እንዲህ ልንተርከዉ ነዉ አብራችሁኝ ሁኑ፡፡ወቢላሂ ተዉፊቅ!!! ክፍል_አንድ ስማቸዉ ሙፍቲ # ዳዉድ_ቢን_አቡበክር አል-ጀበርቲ ይባላል፡፡ሙፍቲ ዳዉድ የተወለዱት በአሁኑ አከላለል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሔረሰብ ...

                                               

ማጎግ

ማጎግ በ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት ከያፌት ሰባት ልጆች ሁለተኛው ነው። ማጎግ ደግሞ በትንቢት ይጠቀሳል፤ በተለይ ትንቢተ ሕዝቅኤል 38፡2 ጎግ የሚባለው አለቃ ሲገልጽ የአገሩ ስም "ማጎግ" ይባላል፦ "በጎግ ላይና በማጎግ ምድር ላይ፣ በሞሳሕና በቶቤል ዋነኛ አለቃ ላይ" ይላል። በ ዮሐንስ ራዕይ 20፡8 "በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን፥ እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው" ሲል እዚህ ለመጀመርያው ጊዜ "ጎግና ማጎግ" አንድላይ ይሰየማሉ። "ጉግማንጉግ" የሚለው የአማርኛ ዘይቤ ከዚህ ጥቅስ ራዕይ 20፡8 የተወረደ ነው። የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ ዮሴፉስ 1ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. እንዳለው የማጎግ ልጆች የእስኩቴስ ሰዎች ነበሩ፤ ይህም ብሔር በጥንት ከጥቁር ባሕር ስሜን የተገኘ ሰፊ ሕዝብ ነበር። ግሪኮች እስኩቴስን "ማጎጊያ" ይሉት እንደ ነበር ጻፈ ። ኢሲዶር ዘሰቪላ 600 ዓ.ም. ግድም እንደ ጻፈው፣ ከዚህ በላይ አንዳንድ ሰዎች ማጎግ የጎታውያን ...

                                               

አራም (የሴም ልጅ)

አራም ሴም በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት መሠረት የኖህ ልጅ ሴም ከወለዱት ልጆች አንድ ሲሆን የዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴርና ሞሶሕ አባት ይባላል። በጥንቱ ታሪክ ጸሐፊዎች ዘንድ፣ ይህ አራም የስሜን መስጴጦምያና የሶርያ ሕዝብ የአራማውያን አባት ነበር። በኤብላ ጽላቶች ላይ 2300-2100 ዓክልበ. ግድም "አራሙ" እና "አርሚ" የሚሉ ስያሜዎች ይገኛሉ፤ "አርሚ" የሐላብ አሌፖ ስም ነበር። በ2034 ዓክልበ. ያሕል በአካድ ንጉሥ ናራም-ሲን በስሜን ተራሮች በተደረገው ዘመቻ "የአራም አለቃ ዱቡል" እንደማረከው ይመዘገባል። የአራም ሕዝብ ወይም አገር ደግሞ በማሪ ጽላቶች 1900 ዓክልበ. ግድም እና በኡጋሪት ጽላቶች 1300 ዓክልበ. ግድም ታይተዋል። ሆኖም እነዚህ ስያሜዎች ትርጉሞች ለሊቃውንት ክርክር ሆነዋል፤ የአራም ሕዝብ መኖሩ ከ1100 ዓክልበ. ጀምሮ በእርግጥ ይታወቃል። በ መጽሐፈ ኩፋሌ 9፡19 መሠረት፣ የኖህ ልጆች ምድሪቱን ሲያከፋፈሉ የአራም ልጆች የወረሱት ርስት ከኤፍራጥስና ከጤግሮስ ወንዞች መካከል ያለው አገር ሁሉ ያጠቅልል ነበር። ይ ...

                                               

መዝገበ ዕውቀት

መዝገበ ዕውቀት ማለት ወይም የዕውቀት ዘርፎች ሁሉ ወይም የአንድ ዕውቀት ዘርፍ የመረጃ ክምችት ነው። ከመዝገበ ቃላት የሚለይበት ጥቅሙ እያንዳንዱ መጣጥፍ ስለ አንድ ቃል ወይም ዘይቤ ብቻ ሳይሆን ጥልቀት ያለው መረጃ እሚሰጥ መሆኑ ነው። ስለዚህ የመዝገበ ዕውቀት መጣጥፍ ከመዝገበ ቃላት መጣጥፍ ይልቅ ረጅምና ዝርዝሩን የሚገልጽ ነው። ከሁሉ ጥንታዊው እስካሁንም የሚገኘው መዝገበ ዕውቀት የፕሊኒ መጽሐፍ ናቱራሊስ ሂስቶሪያ ወይም "የተፈጥሮ ታሪክ" ይባላል። በአሁኑ ዘመን በኢንተርኔት የሚነቡ ብዙ መዛግብተ ዕውቀት ሊገኙ ይቻላል። ዕውቀት የተሳተ መረጃ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ፣ መዝገበ ዕውቀት "መዝገበ ዕውነት" ከቶ አይሆንም። ለመሆኑ ግን በዞራስተር ጽሑፍ መሠረት "መዝገበ ዕውነት" ሃታ-ማራኒሽ የእግዚአብሔር 16ኛው ስያሜ ነው።

                                               

እሱባለው ይሁን

                                               

የደረጃዋ እመቤቴ ማርያም

ታሪክ
                                     

ⓘ ታሪክ

ታሪክ በትክክል እንደሚሰፈን ከተጻፉት መዝገቦች አንስቶ ይጀምራል። ከዚያ አስቀድሞ ምንም የተጻፉት መዝገቦች ሳይኖሩ የነበረው ወቅት ቅድመ-ታሪክ ይባላል።

በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከጥንታዊ ግብጽ ሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ለምሳሌ የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ እና የጊንጥ ዱላ ከዚህ ዘመን ናቸው። ስለዚህ ከ3125 ዓክልበ. በፊት ያለፈው ሁሉ የአለም "ቅድመ-ታሪክ" ነው።

በሌላ አገር ግን የጽሑፍ መዝገቦች እንዲሁም የታሪክ መጋረጃ መከፈቱ እንደ ግብጽ ጥንታዊ አይሆንም። ለምሳሌ ከሜክሲኮ ስሜን የኖሩት ስሜን አሜሪካ ኗሪዎች እንደ ብዙ አሕጉር ሰዎች ለረጅም ዘመን የጽሑፍ አካል ባጠቃላይ ያልነበራቸው ሆነው ቀሩ። ከዚሁ የመዝገቦች ጉድለት የተነሣ ከ1500 ዓም በፊት ያለው ጊዜ ሁሉ የስሜን አሜሪካ ቅድመ-ታሪክ ሊባል ይችላል። ከ1500 ዓም በፊት የተቀረጹት አንዳንድ ጽሑፎች በተለይም የፊንቄ ቋንቋ በሰፊ በአሜሪካዎች ቢገኙም ሁላቸው በፈረንጅ ሊቃውንት አጠያያቂ ተብለዋል። ሆኖም ስለነዚህ የፊንቄ ቅርሶች ወዘተ. በአሜሪካ ተገኝተው የሚገልጹ መጻሕፍት ሊገኙ ይቻላል።

ከግብጽ ጥንታዊ መንግሥት ዘመን ቀጥሎ ጥንታዊ የሆኑት የኩኔይፎርም ጽሑፍ መዝገቦች ከመስጴጦምያ ከ2500 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ሊታዩ ይቻላል። የአንዳንድ ሌላ አገር መዝገቦች ለምሳሌ የቻይና መዝገቦች በልማድ ተጠብቀው ደግሞ ከዚህ ዘመን ያህል ጀምሮ ይዘግባሉ፤ ነገር ግን በቻይና በሥነ ቅርስ ረገድ ከ1200 ዓክልበ. በፊት የተቀረጸው ጽሑፍ ቢኖር አልተረፈም ወይም አልተገኘም። ከ1600 ዓክልበ. በፊት የነበረውንም የሥያ ሥርወ መንግስት የምናውቀው በኋላ በተዘገቡት ጽሑፎች ብቻ ሲሆን የዚያ ዘመን ታሪክ "አፈ ታሪክ" ሊባል ይችላል።

 • የኢትዮጵያ ታሪክ
 • የእስያ ታሪክ
 • የፈጠራዎች ታሪክ
 • ድንጋይ ዘመን
 • የመረጃ ኅብረተሠብ
 • ታሪካዊ አቆጣጠር በየክፍለዘመኑ
 • ናስ ዘመን
 • የዓለም ታሪክ
 • የብርሃናት ክፍለ ዘመን
 • መካከለኛ ዘመን
 • የአውሮጳ ታሪክ
 • የአፍሪቃ ታሪክ
 • የታሪካዊ ዓመት በዓላት መቁጠርያ
 • የኢንዱስትሪ አብዮት
 • የብረት ዘመን
 • ዘመነ ህዳሴ
                                               

የሕጻናት መጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት

ሕጻናት የአዋቂዎችን ጥንቃቄ የተሞላ እንክብካቤ ይሻሉ። በለጋነታቸው ከቤተሰባቸውና ከቅርብ አሳዳጊዎቻቸው ተገቢውን እንክብካቤ ሊያገኙ ባይችሉ፣ ሕይወታቸው በአሳዛኝ ሁኔታ የመደምደም እድሉ ከፍተኛ ነው። ይህ እንክብካቤ በብዙ ረገድ ሊገለጥ ቢችልም፣ ንፁሕ ጭንቅላታቸው በማይረባ እውቀት ከመጠቅጠቁ በፊት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህዎችን እንዲጨብጡ ማገዝ ከየትኛውም እንክብካቤ የላቀ ድርሻ ይኖረዋል። ስለዚህ ልጅዎን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በማስተማር ያሳድጉ። ይህን ውሳኔ ወስነው ከሆነ፣ ለልጅዎ/ለሕጻናት የሚሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምሕርት በሚከተለው ዌብ ሳይት ላይ ያገኛሉ።

Free and no ads
no need to download or install

Pino - logical board game which is based on tactics and strategy. In general this is a remix of chess, checkers and corners. The game develops imagination, concentration, teaches how to solve tasks, plan their own actions and of course to think logically. It does not matter how much pieces you have, the main thing is how they are placement!

online intellectual game →