Back

ⓘ አንጎል
                                               

ተዋህዶ

በዚህ እምነት ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በነበረበት ጊዜ አንደ እና አንድ ብቻ ተፈጥሮ /ባሕርይ ነበረው ። ይህም ተፈጥሮ /ባሕርይ ሥጋ የሌለበት መለኮት ነበር የሚል ነው ። ሥጋ እንኳ ቢኖረው ፣ ባሕር ውስጥ ሟሙቶ እንደሚጠፋ አንድ ማንኪያ ጨው ፣ የክርስቶስ ሥጋም እንዲሁ በመለኮቱ ባሕር ሟሙቶ ጠፍቷል ይላሉ ።

                                               

ሰፍነግ

ሰፍነጎች ከዕፅዋት ወገን የሚመደቡ ቢመስሉም አርስቶትልና ትልቁ ፕሊኒ በትክክል ከእንስሳት ክፍል መድበዋቸዋል። ሊቃውንት በመላው ዓለም በሚገኙ ውቅያኖሶችና ሐይቆች ቢያንስ 15.000 የሚያክሉ የሰፍነግ ዝርያዎች ይገኛሉ ብለው ይገምታሉ። እነዚህ ሁሉ ሰፍነጎች በቅርጽም ሆነ በቀለም እጅግ የተለያዩ ናቸው። ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ቀጭን ጣት፣ ጉርድ በርሜል፣ የተዘረጋ ምንጣፍ፣ የሚያምር ማራገቢያና የጠራ ብርሌ የመሰለ መልክ ያላቸው ሰፍነጎች አሉ። አንዳንዶች ከስንዴ ቅንጣት ያነሱ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ከሰው የሚበልጥ ቁመት አላቸው። አንዳንድ ሰፍነጎች በመቶ የሚቆጠር ዕድሜ ሊኖራቸው እንደሚችል የሳይንስ ሊቃውንት ያምናሉ። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ" ሰፍነጎች በቅርጻቸው፣ በአሠራራቸውም ሆነ በእድገታቸው ከሌሎች እንስሳት የተለዩ ናቸው” ይላል። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? ሰፍነጎች እንደ ሌሎቹ እንስሳት የውስጥ አካል የላቸውም። ታዲያ ልብ፣ አንጎልም ሆነ የነርቭ አውታር ሳይኖራቸው እንዴት በሕይወት መኖር ይችላሉ? በሰፍነግ አካል ውስጥ፣ ...

አንጎል
                                     

ⓘ አንጎል

አንጎል የማዕከላዊ ስርዓተ ነርቭ ክፍል ሲሆን የሚገኘውም በራስ ቅል አጥንት ውስጥ ነው። በራስ ቅል መሸፈኑ በምንም ዓይነት የመታየት የመነካት የመሸተት አልያም የመቀመስ እድል እንዳይኖረው አድርጎታል። ይህ መዋቅር የሚገኘው በዋናነት የጀርባ አጥንት ያላቸው እንስሳት ላይ ሲሆን በአብዛሀኛዎቹ የጀርባ አጥንት የሌላቸው እንስሳት ላይም ይገኛል። በአንዳንድ እንደ ኮከብ ዓሳ ያሉ የዓሳ ዝርያዎች ላይ ይህ አካል የሌለ ሲሆን እንደ ስፖንጅ ዓይነት እንስሳቶች ደግሞ ጭራሹንም የስርዓተ ነርቭ መዋቅር የላቸውም።

ከሳይንስ አንጻር አእምሮና አንጎል ይገናኛሉ ተብለው ሲታመን ለዚህ እንደ ዋና ማስረጃ ሆኖ የሚቀርበው በተጨባጩ የአንጎል ክፍሎች ላይ የሚደርስ ጉዳት በአእምሮ አስተሳሰብ ላይ የሚያመጣው ለውጥ ነው። ሌላው ተጠቃሽ መረጃ አንድ መድሃኒቶች በአእምሮ ላይ የሚያመጡት ለውጦች ናቸው።