Back

ⓘ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር
                                     

ⓘ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር

ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ማለት በታሪክ ሊቃውንት ከተገመቱት የጥንት ዘመን አቅጣጠሮች መካከል አንዱ ነው።

ከ1000 ዓክልበ. ያሕል በኋላ ለሆነው ታሪክ፣ በተወሰነ አመት ይህ ድርጊት ሆነ ለማለት በጣም አጠያያቂ አይደለም። ከዚያ አስቀድሞ ግን መዝገቦች በካሳውያን ዘመን ጥቂት ስለ ነበሩ፣ ትንሽ ጨለማ ዘመን ተብሏል። በ "ኡልትራ አጭር አቆጣጠር" ዘንድ፣ በ1507 ዓክልበ. የሐቲ የኬጥያውያን ንጉስ 1 ሙርሲሊ ባቢሎንን ዘረፈ፤ ከዚያ ካሳውያን ከተማውን ይዘው ስሙን ካራንዱንያሽ አሉት።

                                     

1. የባቢሎን ውድቀት ዓመት መወሰን

የባቢሎን መጨረሻ ንጉሥ ሳምሱ-ዲታና ለ31 ዓመታት የነገሠ ቢታወቅም፣ የባቢሎን ካርንዱንያሽ መጀመርያ ካሳውያን ነገሥታት እስከ 1 ካዳሽማን-ኤንሊል ድረስ፣ 1383-1368 ግን ስንት አመታት እንደ ነገሡ በትክክል ስላልተገኘ፣ የባቢሎን ውድቀት አመት በትክክል ለመወሰን ለረጅም ጊዜ አልተቻለም ነበር። ዳሩ ግን በንጉሥ አሚ-ሳዱቃ ዘመን በ8ኛው ዓመት የዘሃራ ሁኔታና አቀማመጥ በደንብ ስለ ተመዘገበ፣ ይህ የታሪክ ሊቃውንት ዘመኑን ለመወሰን ረድቷል። ስለዚሁ የሥነ ፈለክ ቁጠራ፣ የአሚ-ሳዱቃ 8ኛው አመት ወይም በ1702፣ በ1646፣ በ1582፣ ወይም በ1550 ዓክልበ. እንደ ተከሠተ ታወቀ። ዛሬ የብዙ አገራት ታሪክ ሊቃውንት "መካከለኛ አቆጣጠር" የተባለውን ሲቀበሉ፣ የአሚሳዱቃ 8ኛው አመት በ1646 እና የባቢሎን ውድቀት በ1603 ዓክልበ. የሚወስኑት ናቸው። አለዚያ "አጭር አቆጣጠር" ተከትለው የአሚሳዱቃ 8ኛው አመት በ1582፣ የባቢሎንም ውድቀት በ1539 ዓክልበ. ያደርጉታል።

ባለፈው ቅርብ ጊዜ ግን በሥነ ቅርስ እርምጃ ሳቢያ የአሦር ነገሥታት ዘመናት ቁጥር ለማወቅ ስለ ተቻለ፣ የፈረንሳይ ሊቅ ዤራርድ ዠርቱ "ከሁሉ አጭሩ" ኡልትራ ወይም አብልጦ አጭር አቆጣጠር በትክክል እንደሚስማማው አስረድቷል። የአሚሳዱቃ 8ኛው አመት በ1550፣ የባቢሎንም ውድቀት በ1507 ዓክልበ. ሆነ ወይም ክ.በ. በ1499 እንደ ኤውሮጳውያን አቆጣጠር ለማለት እንችላለን ማለት ነው።

                                     
  • ሠርቶ የጉቲዩም ንጉሥ ሻርላግን የማረከበት ዓመት ነው ይህ ዓመት ምናልባት 2020 ዓክልበ. አካባቢ ነበር ኡልትራ አጭር አቆጣጠር በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር ደግሞ ከጉታውያን ከተዘረዘሩት ነገሥታት የ፪ኛው ስም ዛርላጋብ ወይም ሳርላጋብ
  • እርካብቱም የያምኻድ ንጉሥ ምናልባት ከ1587 እስከ 1575 ዓክልበ. አካባቢ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር በዋና ከተማው ሐላብ ነገሠ እርካብቱም በተለይ በአላላኽ ከተገኙት ጽላቶች ይታወቃል የአላላኽ ንጉሥ አሚታኩም ለእርካብቱም ተገዥ ሲሆን
  • እሽመ - ዳጋን ከ1850 እስከ 1833 ዓክልበ. ግድም ድረስ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ከኢሲን ሥርወ መንግሥት የሱመር ንጉሥ ነበር ማዕረጉ በይፋ የኡር የሱመርና የአካድ ንጉሥ ነበረ የሱመር ነገሥታት ዝርዝር እሽመ - ዳጋን ለ፳ ወይም
  • ሹ - ኢሊሹ ከ1872 እስከ 1862 ዓክልበ. ግድም ድረስ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ከኢሲን ሥርወ መንግሥት የሱመር ንጉሥ ነበር ማዕረጉ በይፋ የኡር የሱመርና የአካድ ንጉሥ ነበረ የሱመር ነገሥታት ዝርዝር ልዩ ልዩ ቅጂዎች ሹ - ኢሊሹ ለ፲
  • ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ 1661 ዓክልበ. - አሙር - እሽታር 1660 ዓክልበ. - ኢብኩ - እሽታር 1659 ዓክልበ. - 1658
  • የዘመኑን ቁጥር የሚገልጽ ሰነድ ግን እስካሁን አልተገኘም ስለዚህ ከ1383 ዓክልበ. በፊት በትንሽ ጨለማ ዘመን ባቢሎን ስንት አመት ያሕል በካሳውያን እንደ ተገዛ ለታሪክ ሊቃውንት አጠያያቂ ጉዳይ ሆኗል ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዩ
  • ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ 1671 ዓክልበ. - አያ 1670 ዓክልበ. - አዙቢያ 1669 ዓክልበ. - ኩርኩዳኒም የሻማሽ - ረዒ
  • አጭሩ ኡልትራ አጭር ወይም አብልጦ አጭር አቆጣጠር በትክክል እንደሚስማማው አስረድቷል የአሚሳዱቃ 8ኛው አመት በ1550 የባቢሎንም ውድቀት በ1507 ዓክልበ. ሆነ ወይም ክ.በ. በ1499 እንደ ኤውሮጳውያን አቆጣጠር ለማለት
  • ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ 1678 ዓክልበ. - አሁ - ዋቃር 1677 ዓክልበ. - ኪዙሩም 1676 ዓክልበ. - ዳዲያ 1675
  • ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ 1790 ዓክልበ. - አሹር - ኢዲን ሹሊ ልጅ 1789 ዓክልበ. - አሹር - ናዳ ፑዙር - አና ልጅ 1788

Users also searched:

...
...
...