Back

ⓘ የግንባታ ምህንድስና
                                     

ⓘ የግንባታ ምህንድስና

የግንባታ ምህንድስና የግንባታ ሂደትን የማቀድ፣ የማስፈጸም፣ ለግንባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ ቁሳቁሶችን የማጓጓዝና የማቅረብ፣ እንዲሁም የግንባታ ቦታውን ለሚፈለገው የግንባታ አካል እንዲውል በግንባታው አካባቢ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ መሟላቱን የማረጋገጥ፣ የግንባታ ቦታው ለግንባታ ስራ ደህንነትና ምቹነት ያለው መሆኑን የማረጋገጥ እንዲሁም አግባብ የሆነ የግንባታ መሬት አጠቃቀምን የሚከታተልና የሚያስፈጽም የምህንድስና ዘርፍ ነው። የግንባታ ተቋራጮች በሌሎች የሲቪል ምህንድስና አገልግሎቶች ላይ ከተሰማሩ የአገልግሎት ተቋሞች አንጻር የተሰማሩበት መስክ ከፍተኛ የንግድ አደጋ ወይም መዋዠቅ ስለሚከሰትበት የግንባታ መሃንዲሶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን ንግድን በተመለከቱ ጉዳዮች ለምሳሌ ያህል የግንባታ ውሉን በመገምገም እና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በማርቀቅ፣ የግንባታ ግብአቶችን አቅርቦት ፍሰት በመቆጣጠር፣ እንዲሁም የግንባታ እቃዎች የገበያ ዋጋ መረጃን በመሰብሰብ ላይ ያውላሉ።

                                     
  • ሌሎች በአፈር ወይም በድንጋይ የተሰሩ ወይም የተደገፉ የግንባታ አካላትን ጥናት ንድፍ እና ግንባታ የምናከናውንበት የሙያ ዘርፍ ነው የጂኦቴክኒክ ምህንድስና የከርስ ምድር ምህንድስና geological engineering ዘርፍንም ያካተተ
  • ሲሚንቶ የግንባታ ግብአት ሲሆን መዋቅሮችን ለመስራት እና እርስ በርስ ለማያያዝ ይጠቅማል ይህ ቁስ ተሰርቶ ከደረቀ በኋላ የመጠንከር ባህሪ አለው
  • ሚስማር በተለይም እንጨት ነክ በሆነ የግንባታ ስራ ውስጥ ለቤት እና አጥር መስሪያነት የሚያገለግል ሹል ብረት ነው ይህ ብረት ለማገር ጠርብ አውራጅ ወይንም ሌላ የመዋቅር አይነቶች ማያያዣነት ያገለግላል ይህ መሳሪያ በመዶሻ ወይንም መርቴሎ
  • ፌሮ ብረት ወይም የማጠናከሪያ ብረት ከካርቦን ብረት የሚሰራ ጠንካራ የግንባታ መሣሪያ ሲሆን የሚጠቅመውም በሲሚንቶ ቅልቅል ውስጥ እንደማጠናከሪያነት ነው ይህ ብረት የተሠራው መዋቅር ጭመቃዊ ጥንካሬ እንዲኖረው ያደርገዋል
  • ይህ መዋቅር ከእንጨት የሚሰራ ከሆነ በሚስማር ወይንም ሌላ ማያያዣ ገመድ ሊሆን ይችላል እየተያያዘ እንዲቆም ይደረጋል ነገር ግን መዋቅሩ እንደ ቆርቆሮ ጎማ ግንብ እንዲሁም ሽቦ የመሰሉ የተለያዩ የግንባታ ግብአቶች ሊሰራ ይችላል

Users also searched:

...
...
...