Back

ⓘ ቋንቋ
                                               

ቋንቋ

ቋንቋ የድምጽ፣ የምልክት ወይም የምስል ቅንብር ሆኖ ለማሰብ ወይም የታሰበን ሃሳብ ለሌላ ለማስተላለፍ የሚረዳ መሳሪያ ነው። በአጭሩ ቋንቋ የምልክቶች ስርዓትና እኒህን ምልክቶች ለማቀናበር የሚያስፈልጉ ህጎች ጥንቅር ነው። ቋንቋዎችን ለመፈረጅ እንዲሁም ለመክፈል የሚያስችሉ መስፈርቶችን ለማስቀመጥ ባለው ችግር ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በርግጠኝነት ስንት ቋንቋ በዓለም ላይ እንዳለ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። እንደ ተለያየ መስፈርት ግምት ከ3000 እስክ 7000 ቋንቋዎች በአለም ላይ እንዳሉ ስምምነት አለ። የሰው ልጅ ቋንቋ በተፈጥሮ የሚገኝ ሲሆን ህጻናት ቋንቋን በደመ ነፍስ ይማራሉ። በተፈጥሮ የሚገኙ የሰው ልጅ ቋንቋዎች ከድምጽና ከየሰውነት ክፍሎች ምልክት ይፈጠራሉ። በሺሆች የሚቆጠሩ የሰው ልጆች ቋንቋዎች ቢኖሩም የሁሉም የጋራ የሆኑ ቋሚ ጸባዮች አሏቸው። እኒህ ቋሚ ጸባዮች በሁሉም የተፈጥሮ ቋንቋውች ሠርጸው የሚገኙ እንጂ ላንዱ ሰርተው ላንዱ የማይሰሩ አይደሉም።

                                               

የኒካራጓ ምልክት ቋንቋ

የኒካራጓ ምልክት ቋንቋ በ1970ዎቹና በ1980ዎቹ በምዕራብ ኒካራጓ የመስማት መሳን ባለባቸው ተማሪዎች የተለማ የምልክት ቋንቋ ነው። የተለማው ከቆዩት እጅ ቋንቋዎች ሳይሆን በተማሪዎች እራሳቸው በድንገት ነበር። ስለዚህ ለቋንቋ ሊቃውንት "የመነጋገር ልደት" ወይም የመንስኤው ሁኔታ ለማጥናት ያስችላል። ከ1969 ዓ.ም. በፊት በመስማት የተሳናቸው ሰዎች ኅብረተሠብ አልነበራቸውም። ከቤተሠቦቻቸው ጋራ ለመነጋገር ይቻሉ ቀላል በሆነ እጅ ንቅናቄ ብቻ ነበር። በ1969 ዓ.ም. ግን ጆሯቸው ለማይስማ ተማሪዎች ልዩ ተምህርት ቤት በዋና ከተማ በማናጓ ስለ ተመሠረተላቸው 50 ተማሪዎች ወዲያው ትምህርታቸውን ጀመሩ። የሳንዲኒስታ አብዮት በሆነበት ወቅት 1971 ዓ.ም. መቶ ተማሪዎች ነበሩ። በ1972 ሁለተኛ ልዩ ትምህርት ቤት ተከፍቶ በ1975 ዓ.ም. የተማሪዎች ቁጥር 400 ደረሰ። በመጀመርያ ትምህርት ቤቶቹ የከንፈር ማንበብና የጣት ፊደል ብቻ ለማስተማር አስበው ይህ ዘዴ ግን አልተከናወንም። ዳሩ ግን ተማሪዎቹ በትርፍ ጊዜያቸው በቤተሠቦቻቸው የተጠቀሙ ...

                                               

ማዖሪ ቋንቋ

ማዖሪ ቋንቋ ከኒው ዚላንድ መደበኛ ቋንቋዎች አንዱ ነው። የምሥራቅ ፖሊኔዚያ ደሴቶች ቋንቋ ቤተሠብ አባል ሲሆን የታሂቲ እና የሃዋይኢ እንዲሁም የሳሞዓ እና የቶንጋ ቋንቋዎች ዘመድ ነው። የተናጋሪዎቹ ቁጥር 100.000 የሚያሕል ነው።

                                               

ዓረብኛ

ዓረብኛ العربية ፡ የሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ቤተሠብ ፡ አባል ፡ ሆኖ ፡ የዕብራይስጥ ፡ የአረማያ ፡ እንዲሁም ፡ የአማርኛ ፡ ቅርብ ፡ ዘመድ ፡ ነው። ፪ ፻ ፶ 250 ፡ ሚሊዮን ፡ የሚያሕሉ ፡ ሰዎች ፡ እንደ ፡ እናት ፡ ቋንቋ ፡ ይናገሩታል። ከዚህም ፡ በላይ ፡ በጣም ፡ ብዙ ፡ ሰዎች ፡ እንደ ፡ ፪ ኛ ፡ ቋንቋ ፡ ተምረውታል። የሚጻፈው ፡ በዓረብኛ ፡ ፊደል ፡ ነው። በዓረብ ፡ አለም ፡ ውስጥ ፡ አያሌ ፡ ቀበሌኞች ፡ ይገኛሉ። ቋንቋው ፡ በእስልምና ፡ ታላቅ ፡ ሚና ፡ አጫውቷል። እስላሞች ፡ አላህ ፡ ለሙሐማድ ፡ ቁርዓንን ፡ ሲገልጽ ፡ በዓረብኛ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ ስለሚያምኑ ፡ እንደ ፡ ቅዱስ ፡ ቋንቋ ፡ ይቆጥሩታል። አብዛኛው ፡ ዓረብኛ ፡ ተናጋሪዎች ፡ ሙስሊሞች ፡ ናቸው። ዛሬ ፡ በምዕራብ ፡ ዓለም ፡ ደግሞ ፡ ብዙ ፡ ሰዎች ፡ አረብኛ ፡ እያጠኑ ፡ ነው። በታሪክ ፡ ከፍተኛ ፡ ሚና ፡ በማጫወቱ ፡ መጠን ፤ ብዙ ፡ የዓረብኛ ፡ ቃላት ፡ ወደ ፡ ሌሎች ፡ ቋንቋዎች ፡ ገብተዋል።

ግሪክ (ቋንቋ)
                                               

ግሪክ (ቋንቋ)

የግሪክ ቋንቋ ወይም ግሪክኛ ከህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች አንዱ ሲሆን የግሪክ እንዲሁም የቆጵሮስ መደበኛ ቋንቋ ነው። በጠቅላላ ከ15 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ይናገሩበታል። ቀደም ሲል ደግሞ በሜዲቴራኔያን ዙሪያ፣ በምዕራብ እስያና በስሜን አፍሪቃ በሰፊ ይጠቀም ነበር። ግሪክ የተጻፈበት በግሪክ አልፋቤት ነው። ዛሬ በዓለም ዙርያ አብዛኞቹ ፊደሎች በተለይም የላቲን አልፋቤትና የቂርሎስ አልፋቤት የተለሙ ከዚሁ ግሪክ ጽሕፈት ነበር። ግሪኮቹ ደግሞ ሀሣቡን የበደሩ ከፊንቄ አልፋቤት ምናልባት በ1100 ዓክልበ. ገዳማ ነበረ። ከዚያ በፊት 1500-1100 ዓክልበ. ግድም ከሥነ ቅርስ እንደ ታወቀ ግሪክኛ በፍጹም በሌላ ጽሕፈት "የሚውኬናይ ጽሕፈት" ይጻፍ ነበር። ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲስ ኪዳን መጀመርያ በግሪክ ተጽፏል።

ቻይንኛ
                                               

ቻይንኛ

ቻይና፣ ታንግ የቻይና ቋንቋ፣ የቻይና ቋንቋ መሆኑን ወይም የቻይና ቋንቋዎች የቻይና ቋንቋ ቋንቋዎች አንዱ ነው፡፡አንዲት ቋንቋ ቢታየው በዓለም ቋንቋ በጣም የተጠቃሚ ቋንቋ ነው፤ አሁን የዓለም ሕዝብ አምስተኛው ቋንቋ ነው።ብዙ ቅርንጫፎች አሉት፡፡ከዚህም በላይ ቻይናውያን እንደ ሻንካይ ተጋራሚ አካባቢ የዓለምአቀፍ አቀራቢ ቋንቋ ነው፡፡

ሲ (የኮምፒዩተር ፍርገማ ቋንቋ)
                                               

ሲ (የኮምፒዩተር ፍርገማ ቋንቋ)

ሲ የኮምፑተር ፍርገማ ቋንቋ ለሲፊ አላማ የሚውል የተደራጀ ትዕዛዝ ተኮር የኮምፒውትር ፍርገማ ቋንቋ ሲሆን ለዪኒክስ የሲስተም አሰሪ ተብሎ በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ በደኒስ ሪቺ ተሰርቶ ቀረበ። ከዚያ ወዲህ በአብዛኛው የኮምፒዩተር የሲስተም አሰሪ ተስፋፍቶ በአለም በስፋት ከሚያገለግሉ የፍርገማ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ሲ ሌሎች ታዋቂ የፍርገማ ቋንቋዎች ገጽታ ላይ ታላቅ ሚና ተጫውቶዋል። በተለይም ሲ++ ለሲ ማሻሻያ ተብሎ የታቀደ ቋንቋ ነው። የተመጠነና ብቃት ያለው ኮድ ለማውጣት የተመቻቸ ቋንቋ ሆኖ ሲታወቅ፣ የሲስተም አሰሪ ሶፍትዌሮችን ለመስራት የተለመደ ቋንቋ ሆኖ ሳለ ሌሎች ሶፍትዌሮችንም ለመጻፍ በስፋት ያገለግላል።

የስራ ቋንቋ
                                               

የስራ ቋንቋ

የስራ ቋንቋ በአንድ ሀገር ውስጥ ብሔራዊ ቋንቋ ነው። ይህም ማለት በሀገሪቱ ፍርድ ቤት፣ ፓርላማ እና የአስተዳደር ቦታዎች ለመግባቢያነት የሚያገለግል ማለት ነው። ቋንቋው በሀገሪቱ ውስጥ ብዙ ተናጋሪ ባይኖረውም እንኳን የስራ ቋንቋ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ለምሳሌ በኒውዚላንድ ማዖሪ የተባለው ቋንቋ በሀገሪቱ ከ5 በመቶ ያልበለጠ ተናጋሪ ቢኖረውም የሀገሪቱ የስራ ቋንቋ ተደርጎ ይጠቀሙበታል።

                                               

ምሳሌ

ምሳሌ ማለት በአንድ ቋንቋ ወይም ባሕል ውስጥ የሚጠበቅ የጥበብ ቃል ወይም ዘይቤ ነው። ብዙ ምሳሌዎች ከቋንቋ ወደ ቋንቋ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ወይም ከሃይማኖቶች የሚተላለፉ ናቸው። ለምሳሌ በብሉይ ኪዳን መጽሐፈ ምሳሌ ውስጥ ያሉት የንጉሥ ሠለሞን ምሳሌዎች በበርካታ ክርስቲያን ባህሎች ታውቀዋል። እንዲሁም በተረፉት መጻሕፍት የተወሰዱ ምሳሌዎች አሉ። አማርኛ ምሳሌ የብዙ አማርኛ ምሳሌ ትርጉም በ ይገኛል። እንግሊዝኛ ምሳሌ "Early to bed, early to rise, makes a man healthy, wealthy and wise" ቤንጃሚን ፍራንክሊን፤ ቶሎ ለመኝታ፣ ቶለ ለመነሣት፣ ሰውን ጤንኛ፣ ባለጸጋና ጥበበኛ ያደርገዋል።