Back

ⓘ ምህንድስና
                                               

መሀንዲስነት

ምህንድስና ማለት የሳይንስ እና የሂሳብ መርሆችን በመከተል እንዲሁም የማስተዋል እና የምርምር ችሎታን በመጠቀም በተመጣጣኝ ወጪ ለሰው ልጆች ጥቅም ሊውሉ የሚችሉ ግንባታዎችን መቀየስ፣ ተቋማትን መስራት፣ የመገልገያ ቁሳቁሶችን መፍጠር እና ይተለያዪ የቴክኒክ ችግሮችን መፍትሔ ማግኘትን ያጠቃልላል። ይህንን አይነት ስራ የሚሰራ ሰው መሐንዲስ ተብሎ ይጠራል። የምህንድስና ስራ የተለያዩ ዘርፎች ያሉት ሲሆን በተለምዶ ከሚታወቁት ዘርፎች ውስጥ ሲቭል፣ መካኒካል፣ ኤሌክትሪካል እና ኬሚካል ይጠቀሳሉ። የተክኖሎጂ ማደግ ተከትሎ በአሁኑ ወቅት የምህንድሲና ዘርፎች ሰፋ ያሉ ናቸው። አዲሶቹ የምህንድስና የትኩረት ዘርፎች ሁሉን አቀፍ እና ውሱን በሆነ የተግባር አቅጣጫ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ከምህንድስና አይነቶች መካከል፦ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኤሌክትሪክ ምህንድስና ኮምፒዩተር ምህንድስና ህንጻ ምህንድስና ይገኙቤታል።

                                               

የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና

የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ከጤና ጥበቃ ምህንስና ጋር ተጓዳኝ የሆነ የምህንድስና ዘርፍ ሲሆን፣ የጤና ጥበቃ ምህንድስና በአመዛኙ የንጹህ ውሃ መጠጥ አቅርቦትና የአካባቢ ቆሻሻ ፍሳሽ አወጋገድ ላይ ሲያተኩር፤ የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ሰፋ ባለ መልኩ የአካባቢ ብክለት የሚያስከትሉና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ጎጂ ኬሚካሎችን እና ቆሻሻዎችን መቆጣጠርና ማስወገድ ይጨምራል። የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና፤ የማህበረሰብ ጤና ምህንድስና እና የአካባቢ ጤና ምህንድስና በሚል አጠራርም ይታወቃል። የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና በኬሚካል ውህደቶች፣ በባዮሎጂካል ሂደቶች እንዲሁም በሙቀት ለውጥ አማካኝነት የሚፈጠሩ ቆሻሻዎችን የማጥራትና የማስወገድ፣ አየርንና ውሃን የማጣራት፣ እንዲሁም በአደጋ ወይም በቆሻሻ ክምችት የተበከለን የመሬት አካል ወደ ተፈጥሮዋዊ ይዘቱ የመመለስ ስራዎች የሚያከናወኑበት የምህንድስና ዘርፍ ነው። በአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ትኩረት ከሚደረግባቸው ዋና ነጥቦች ውስጥ የመርዝ ወይም የኬሚካል እንቅስቃሴ ወይም ጉዞ ከመሬት ላይና ከመሬት በታች፣ የው ...

                                               

ኤሌክትሪክ ምህንድስና

ኤሌክትሪካል ምህንድስና ፣ ኤሌክትሪካል ኤንጂነሪንግ በመባል የሚታወቀዉ የምህንድስና ክፍል ስለ ኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስ ኤልክትሮ-መግነጢዝምነት የሚያወሳ የትምህርት የትግበራ ዘርፍ ነው። ይህ የምህንድስና ክፍል ተለይቶ የተጠራዉ እንደ ቴሌግራፍ ፤ ስልክ እና የኤልክትሪክ ኀይል ጥቅም ተገኝቶ ትግበር ላይ ከዋለ በኋላ ነዉ፤ ወደ ታሪኩ ስንመጣ ኤሌክትሪሲቲ ኮረንቲነት በሳይንሳዊ አስተሳሰብ መታሰብ ምንአልባትም ዊሊያም ጊልበርት ስታቲካሊ ቻርጅድ የሆኑ ቁሶች የሚለይ መሳሪያ በመፈልሰፉ ነው። ከ1830ዎቹ ጀምሮ የቴሌግራፍ ጥቅም ላይ መዋል ሙከራ ተደርጎም መሳካት ዐለምን ወደ ፈጣን ግኑኝነት እንዳስገባዉ ይታመናል። የሚከተሉትን በዘርፉ ልብ ይሏቸዋል፣ ባትሪ የኀይል ሙል፤ የኀይል ፍሰት ጥርቅም እና ማስተላለፊያው፤ ኤሌክትሮ መግነጢዝም፤ ተለዋዋጭ የማይለዋወጥ የኀይል ፍሰት፤ ትራንስፎርመር፤ ሞተር፤ ራዲዮ፤ መስመር አልባ ግንኙነት፤ ሞገድ፤ የጨረር ቱቦዎች፤ ቴሌቪዥን፤ ቫኪዉም ቱቦዎች፤ ትራንዚስተሮች፤ የተቀናጁ ሽቦዎች፤ ፕሮሰሰሮች፤ አስተላላፊዎች ...

                                               

ሲቪል ኢንጂነሪንግ

ሲቪል ምህንድስና ወይም ሲቪል ኢንጂነሪንግ አንዱ እና ታዋቂው የምህንድሥና ዘርፍ ነው። ሲቪል ምህንድስና ስለ ግንባታ አካላት አስፈላጊነት ቅድመ ጥናት የሚያደርግ እንዲሁም የግንባታ አካላቱ አስፈላጊነት ከታመነበት በኋላ፤ የንድፍ ስራና የግንባታ ሂደትን የሚከታተልና የሚያስፈጽም እንዲሁም የግንባታ አካላቱ አገልግሎት ላይ ከዋሉ በኋላ የአገልግሎት እድሜያቸው እስከሚያበቃ ድረስ የሚፈለግባቸውን አገልግሎት እየሰጡ እንዲቆዮ የጥገና ስራዎችን የሚያጠናና የሚተገብር የሙያ ዘርፍ ነው። ከግንባታ አካላት ውስጥ መንገዶች፣ ድልድዮች፣ ህንጻዎች፣ ግድቦች፣ የአየር ማረፊያ አስፋልት ንጣፎች፣ የውሃ ተፋሰስ መስመሮች፣ ለተለያዮ አገልግሎቶች የሚውሉ ትቦዎች፣ የባቡር ሃዲዶች፣ ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ሰው ሰራሽ ወንዞች እና ሌሎችም ይገኙበታል። ሲቪል ምህንድስና በጥንታዊነት ከወታደራዊ ምህንድስና ቀጥሎ ሁለተኛውን ደረጃ ሲይዝ፣ የሙያ ዘርፉ የግንባታ አካላቱ ላይ እንዲሁም የግንባታ ሂደቱ ላይ ተሞርኩዞ በተለያዮ የሙያ ዘርፎች ይከፋፈላል። የሙያ ዘር ...

                                               

የምርመራ ምህንድስና

የምርመራ ምህንድስና የግንባታ አካላት የሚፈለግባቸውን ጥቅም ሳይሰጡ ለአገልግሎት ከታቀደላቸው ጊዜ በፊት በመፍረስ አገልግሎት መስጠት ሲያቆሙ፣ እንዲሁም የመፍረስ አደጋው በሰው ወይም በንብረት ላይ አደጋ በሚያደርስበት ጊዜ የግንባታ አካሉን አወቃቀር ፣ የተሰራበትን ቁስ ፣ የግንባታውን ጥናት እንዲሁም መሰል ተዛማጅ ጉዳዮችን በመመርመር ተጠያቂ የሚሆነውን አካል ለማወቅና የፍርድ ሂደትን ለማገዝ የሚያገለግል የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ይህ የምህንድስና ዘርፍ ከምርመራ ውጤቶች በመነሳት የግንባታ ቁሶችን ወይም የግንባታ አካላት ጥራትን እንዲሁም የግንባታ አካላት አወቃቀርን የማሻሻል ስራዎን ለመስራት የሚያስችል የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ልዮ የሆነ የባለቤትነት ፍቃድ ያላቸውን የግንባታ ቁሶች ፣ አካላት ፣ ወይም የግንባታ ዘዴዎች የፍቃድ ባለቤቱን ይሁንታ ሳያገኙ በሚፈጸሙ ግንባታዎች ላይ የባለቤትነት ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚደረጉ ህጋዊ ሂደቶች ላይ ይህ የምህንድስና ዘርፍ ቁልፍ ቦታ አለው።

                                               

ኮምፒዩተር ምህንድሥና

የኮምፒዩተር ምህንድስና የኤሌክትሪክና እና የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስናን ከኮምፒዩተር ሳይንስ ጋር አዋህዶ የሚያጠና የእውቀት ዘርፍ ነው ። የኮምፒውተር መሃንዲሶች ብዙ ጊዜ የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስናን፣ የሶፍትዌር እቅድና የተጨባጭ እና የማይጨበጥ የኮምፒውተር ክፍል ውህደት በማጠቃለል ያጠናሉ። እነዚህ መሃንዲሶች በብዙ አይነት የማንሰላሰል ስራ ላይ ይሳተፋሉ። ለምሳሌ በማይክሮፕሮሰሰር፣ በግል መንሰላስል እና በታላላቆቹ መንሰላስሎች ትልም ላይ ዋና ተዋንያን ናቸው። አልፎም ተርፎም በነዚህ ኮምፒወተሮች የሽቦወች ዑደት አቅድ አወጣጥ ሳይቀር ይሳተፋሉ። በዚህ ምክንያት የዚህ እውቀት ዘርፍ ተሳታፊወች አጠቃላይ የመንሰላስል ስርአት አካሄድን ብቻ ሳይሆን እንዴት መንሰላስሎች እርስ በርሳቸው እንደሚዋሃዱ ሁሉ ጥናት ያካሂዳሉ። የመንሰላስል መሃንዲስ አብዛኛው ስራው የሚመለከተው 1) ሶፍትዌርና ፊርምዌር ለታቃፊ ማይክሮኮንትሮለሮች መጻፍ 2) VLSI የተሰኙትን የኮምፒውተር አካል ቁራጮች እቅድ መንደፍ 3) አናሎግ የስሜት ህዋሳትን መተለም 4) በቀጥ ...

                                               

የአወቃቀር ምህንድስና (ስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ)

የአወቃቀር ምህንድስና የህንጻዎችን፣ የድልድዮችን፣ የማማዎችን፣ የመንገድ ማቋረጫ ድልድዮችን፣ የዋሻዎችን፣ በባህርና ላይ የሚገነቡ ለነዳጅ ወይም ለዘይት ማውጫ የሚያገለግሉ ሰው ሰራሽ መሬቶችን እና ማማዎችንና እንዲሁም እነኚህን የመሳሰሉ የግንባታ አካላትን በተመለከተ የአወቃቀር ንድፍና የአወቃቀር ትንታኔ ላይ የሚያተኩር የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። የአወቃቀር ትንታኔ structural analysis ጉልበቶች በግንባታ አካላት ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ መመዘን ላይ ትኩረት ያደርጋል። የአወቃቀር ምህንድስና በግንባታ አካላት ላይ የሚያርፉ ጉልበቶችን ለምሳሌ የራሱ የግንባታ አካሉ ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ የሚያርፉ ሌሎች ቋሚና ተቀሳቃሽ ክብደቶች፣ የንፋስ ግፊት ፣ የሙቀት ለውጥ፣ የውሃ ግፊት፣ የመሬት ጫና፣ የመሬት ርእደት፣ በረዶ እና የመሳሰሉትን የመለየትና፣ በእነኝህ ጉልበቶች አማካኝነት በግንባታ አካላቱ ውስጥ የሚከሰቱ ውስጣዊ ጫናዎችንና ጉልበቶችን internal stresses and forces የማስላትና የግንባታ አካላቱ እነኝ ...

                                               

መሬት ነክ ምህንድስና (ጂኦቴክኒካል ምህንድስና)

መሬት ነክ ምህንድስና የግንባታ አካላትን የሚሸከሙ አለቶችና አፈሮችን የምህንድስና ጠባይ የሚያጠና የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ይህ ዘርፍ ከአፈር ሳይንስ፣ ከቁስ ሳይንስ ፣ ከሜካኒክስ እንዲሁም የፍሰት ሳይንስ እውቀቶችን በመጠቀም ደህንነታቸው የተጠበቀና የገንዘብ አቅምን ያገናዘቡ የግንባታ መሰረቶችን፣ የመጠበቂያ ግድግዳዎችን፣ ግድቦችን፣ ዋሻዎችን የመሳሰሉ የግንባታ አካላትን መንደፍና መገንባት ላይ ትኩረት ያደርጋል ። የከርሰ ምድር ውሃን በተለያዮ ምክንያቶች ከመበከል የመጠበቅ እንዲሁም የቆሻሻ ክምችትን በአግባቡ ለመቆለልና ክምችቱ የአፈርና የከርሰ ምድር ውሃን እንዳይበክል የማድረግ ስራዎችም በዚሁ የምህንድስና ዘርፍ የሚተገበሩ ናቸው። የአፈርን የምህንድስና ጸባይ የማወቅ ተግባር ለመሬት ነክ መሃንዲሶች ፈታኝ ነው። በሌሎች የሲቪል ምህንድስና ዘርፎች የግንባታ ቁሶች ጸባይ ለምሳሌ እንደ ብረት እና ኮንክሪት በሚገባ የሚታወቅ ሲሆን፤ በግንባታ አካባቢ የሚገኝን የአፈር ጸባይ ማወቅ ግን ከተለዋዋጭነቱና በናሙና በሚደረጉ ሙከራዎች መፈተ ...

                                               

የግንባታ ምህንድስና

የግንባታ ምህንድስና የግንባታ ሂደትን የማቀድ፣ የማስፈጸም፣ ለግንባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ ቁሳቁሶችን የማጓጓዝና የማቅረብ፣ እንዲሁም የግንባታ ቦታውን ለሚፈለገው የግንባታ አካል እንዲውል በግንባታው አካባቢ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ መሟላቱን የማረጋገጥ፣ የግንባታ ቦታው ለግንባታ ስራ ደህንነትና ምቹነት ያለው መሆኑን የማረጋገጥ እንዲሁም አግባብ የሆነ የግንባታ መሬት አጠቃቀምን የሚከታተልና የሚያስፈጽም የምህንድስና ዘርፍ ነው። የግንባታ ተቋራጮች በሌሎች የሲቪል ምህንድስና አገልግሎቶች ላይ ከተሰማሩ የአገልግሎት ተቋሞች አንጻር የተሰማሩበት መስክ ከፍተኛ የንግድ አደጋ ወይም መዋዠቅ ስለሚከሰትበት የግንባታ መሃንዲሶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን ንግድን በተመለከቱ ጉዳዮች ለምሳሌ ያህል የግንባታ ውሉን በመገምገም እና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በማርቀቅ፣ የግንባታ ግብአቶችን አቅርቦት ፍሰት በመቆጣጠር፣ እንዲሁም የግንባታ እቃዎች የገበያ ዋጋ መረጃን በመሰብሰብ ላይ ያውላሉ።

                                               

መሰላል

መሠላል ቀጥ ያለ ወይንም ያጋደለ መወጣጫ ነው። ሁለት አይነት ሲሆን እነርሱም ቋሚ መሠላል እና የገመድ መሰላል ናቸው። ቋሚ መሰላል የሚባለው ከእንጨት ወይም ከብረት አልያም ደግሞ ከሌሎች ነገሮች ሊሰራ የሚችል የመሰላል አይነት ነው። ይህም ሁለት ረዣዥም ቋሚ እና በእነዚህ ቋሚዎች ላይ የሚመቱ ወይንም የሚታሰሩ በርከት ያሉ አጫጭር መወጣጫዎች እንዲኖሩት ተደርጎ ይሰራል። ይህ አይነቱ መሰላል ሊወጣበት ወደተፈለገው ቦታ እንዲያጋድል ተደርጎ ይቀመጥ እና ጥቅም ላይ ይውላል። ሁለተኛው የመሰላል አይነት የገመድ መሰላል ሲሆን ይህ ደግሞ የሚሰራው ከገመድ ነው። ጥቅም ላይ ሲውል ግን ከላይ ብቻ ይንጠለጠላል።

                                               

ሚስማር

ሚስማር በተለይም እንጨት ነክ በሆነ የግንባታ ስራ ውስጥ ለቤት እና አጥር መስሪያነት የሚያገለግል ሹል ብረት ነው። ይህ ብረት ለማገር፣ ጠርብ፣ አውራጅ ወይንም ሌላ የመዋቅር አይነቶች ማያያዣነት ያገለግላል። ይህ መሳሪያ በመዶሻ ወይንም መርቴሎ እየተመታ መዋቅሮቹ ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል።

                                               

ማሽን

ማሽን ፡ አቅምን በመጠቀም ተግባር የሚከውን መሳሪያ ነው። ቀላል ማሽን ደግሞ በተራው የጉልበትን አቅጣጫ ወይም መጠን የሚቀይር እቃ ማለትነው። ኢንጅን የማሽን አይነት ሲሆን፣ ሙቀትን ወይም ሌላ አይነት አቅሞችን ወደ ተንቀሳቃሽ አቅም የሚቀይር መሳሪያ ነው። ብዙ ጊዜ ኢንጅኖች የበላይ ማሽኖች አካል ሁነው ይታያሉ፣ ለምሳሌ ተቀጣጣይ ኢንጅን የመኪና አካል እንደሆነ።

                                               

ሥነ-እንቅስቃሴ

ሥነ-እንቅስቃሴ የሚባለው የፊዚክስ ጥናት ቁስ ነገሮች የጉልበት ግፊት ወይም ስበት ሲደረግባቸው ወይንም ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ በከባቢያቸው ቁስ ላይ ምን አይነት ለውጥ ያመጣሉ ብሎ የሚያጠና የሳይንስ ዘርፍ ነው። ይህ የጥናት ዘርፍ ለስነ-ተፈጥሮ ትምህርት መሰርታዊ ከመሆኑ የተነሳ ከጥንት ዘመን ጀመሮ ሲጠና ኖሩዋል። በአሁኑ ጊዜ፣ ዘርፉ በዘመናት ሂድት ካካበተው የጎለመሰ ዕውቀት የተነሳ ብዙ የጥናት ዘርፎችን አካቶ ይዞ ይገኛል። ሆኖም ግን በእለት ተእለት በሚያጋጥሙን ቁሶች ዘንድ የሚካሄደውን የቁሶች ባህርይ በሚገባ የሚያስረዳው የሥነ-እንቅስቃሴ ዘርፍ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በነበረው እንግሊዛዊ ኢሳቅ ኒውተን በሚገባ ተጠቃሎ ቀርቦአል። ምንም እንኳ ኢሳቅ ኒውተን ህጎቹን በራሱ ባያገኛቸውም፣ እሱ ግን በሚገባ በመፈረጅና ጥቅማቸውንም ጥራዝ ነጠቅ ባልሆነ መልኩ እንዴት እንደሚሰሩ በማሳየት አስገንዝቦ አልፎአል። በተለምዶ የኒውተን ህግ ተብለው የሚታወቁት 3ቱ የስነ-እንቅስቃሴ ህጎች እንሆ፦

                                     

ⓘ ምህንድስና

  • ምህንድስና ማለት የሳይንስ እና የሂሳብ መርሆችን በመከተል እንዲሁም የማስተዋል እና የምርምር ችሎታን በመጠቀም በተመጣጣኝ ወጪ ለሰው ልጆች ጥቅም ሊውሉ የሚችሉ ግንባታዎችን መቀየስ ተቋማትን መስራት የመገልገያ ቁሳቁሶችን መፍጠር እና ይተለያዪ
  • በትራንስፖርት ምህንድስና ውስጥ ሰፊ ድርሻ ይይዛሉ የትራንስፖርት ምህንድስና በውስጡ የትራንስፖርት ንድፍ ስራ transportaion design የትራንስፖርት ግንባታ እቅድ transportation planning የትራፊክ ምህንድስና traffic
  • የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ከጤና ጥበቃ ምህንስና ጋር ተጓዳኝ የሆነ የምህንድስና ዘርፍ ሲሆን የጤና ጥበቃ ምህንድስና በአመዛኙ የንጹህ ውሃ መጠጥ አቅርቦትና የአካባቢ ቆሻሻ ፍሳሽ አወጋገድ ላይ ሲያተኩር የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ሰፋ ባለ መልኩ
  • ኤሌክትሪካል ምህንድስና ኤሌክትሪካል ኤንጂነሪንግ በመባል የሚታወቀዉ የምህንድስና ክፍል ስለ ኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስ ኤልክትሮ - መግነጢዝምነት የሚያወሳ የትምህርት የትግበራ ዘርፍ ነው ይህ የምህንድስና ክፍል ተለይቶ የተጠራዉ እንደ ቴሌግራፍ
  • የመሬት ርዕደት ምህንድስና መሬት ርዕደት በሚያይልባቸው አካባቢዎች የሚሰሩ የግንባታ አካላት የመሬት ርዕደትን ተቋቁመው እንዲዘልቁ ለማድረግ የግንባታ አካላቱን አወቃቀር በተለየ መልኩ ትኩረት በመስጠት የሚያጠናና መፍትሄ የሚሰጥ የምህንድስና
  • ሲቪል ምህንድስና ወይም ሲቪል ኢንጂነሪንግ አንዱ እና ታዋቂው የምህንድሥና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ነው ሲቪል ምህንድስና ስለ ግንባታ አካላት አስፈላጊነት ቅድመ ጥናት የሚያደርግ እንዲሁም የግንባታ አካላቱ አስፈላጊነት ከታመነበት በኋላ የንድፍ
  • የምርመራ ምህንድስና የግንባታ አካላት የሚፈለግባቸውን ጥቅም ሳይሰጡ ለአገልግሎት ከታቀደላቸው ጊዜ በፊት በመፍረስ አገልግሎት መስጠት ሲያቆሙ እንዲሁም የመፍረስ አደጋው በሰው ወይም በንብረት ላይ አደጋ በሚያደርስበት ጊዜ የግንባታ አካሉን
  • የኮምፒዩተር መንሰላስል ምህንድስና የኤሌክትሪክና እና የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስናን ከኮምፒዩተር ሳይንስ ጋር አዋህዶ የሚያጠና የእውቀት ዘርፍ ነው የኮምፒውተር መሃንዲሶች ብዙ ጊዜ የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስናን የሶፍትዌር እቅድና የተጨባጭ
  • የአወቃቀር ምህንድስና የህንጻዎችን የድልድዮችን የማማዎችን የመንገድ ማቋረጫ ድልድዮችን የዋሻዎችን በባህርና ላይ የሚገነቡ ለነዳጅ ወይም ለዘይት ማውጫ የሚያገለግሉ ሰው ሰራሽ መሬቶችን እና ማማዎችንና እንዲሁም እነኚህን የመሳሰሉ የግንባታ
ትራንስፖርት ምህንድስና
                                               

ትራንስፖርት ምህንድስና

የትራንስፖርት ምህንድስና ሰዎችንና ቁሳቁስን ከቦታ ወደ ቦታ በደህንነት ፣ በተቀላጠፈና ምቹ በሆነ መንገድ ማጓጓዝ ላይ ትኩረት ያደርጋል። ይህንን አላማማ ለማሳካትም የመኪና፣ የባቡር፣ የውሃና የአየር ማረፊያ መንገዶች እንዲሁም የወደቦች ንድፍ፣ ግንባታና ጥገና ስራዎች በትራንስፖርት ምህንድስና ውስጥ ሰፊ ድርሻ ይይዛሉ። የትራንስፖርት ምህንድስና በውስጡ የትራንስፖርት ንድፍ ስራ ፣ የትራንስፖርት ግንባታ እቅድ ፣ የትራፊክ ምህንድስና ፣ የከተማ ልማት ምህንድስና፣ የመንገድ ንጣፍ ምህንድስና የመሳሰሉ ንኡስ የሙያ ዘርፎችን የያዘ ነው።

                                               

የመሬት ርዕደት ምህንድስና

የመሬት ርዕደት ምህንድስና መሬት ርዕደት በሚያይልባቸው አካባቢዎች የሚሰሩ የግንባታ አካላት፤ የመሬት ርዕደትን ተቋቁመው እንዲዘልቁ ለማድረግ የግንባታ አካላቱን አወቃቀር በተለየ መልኩ ትኩረት በመስጠት የሚያጠናና መፍትሄ የሚሰጥ የምህንድስና ዘርፍ ነው። ይህ የምህንድስና ዘርፍ የአወቃቀር ምህንድስና ዘርፍ አካል ነው። የመሬት ርዕደት ምህንድስና ዋነኛ አላማው በመሬትና በግንባታ አካሉ እንዲሁም በግንባታ አካላቱ መካካል በመሬት ርዕደት ጊዜ የሚኖረውን መስተጋብር መረዳትና የግንባታ አካሉ የመሬት ርዕደት ሂደቱን አልፎ አገልግሎት እንዲሰጥ አወቃቀሩን፣ የግንባታ ቁስ አመራረጡን እንዲሁም መሰል የግንባታ መፍትሄዎችን በየሀገራቱ ጥቅም ላይ ከዋሉ የግንባታ መስፈርቶች ጋር በሚስማማ መልኩ መተግበር ነው።

የወደብ (የባህር ዳርቻ) ምህንድስና
                                               

የወደብ (የባህር ዳርቻ) ምህንድስና

የወደብ ምህንድስና የወደብ አካባቢን የማልማትና የማስተዳደር ስራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፣ ወደብን ለመጓጓዣ ስራ ከማዋል በተጨማሪ፣ በወደብ አካባቢ የሚከሰቱ የውሃ መጥለቅለቅ አደጋዎችን፣ የአፈር መሸርሸርና እና የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎችን የመከላከል ስራ የሚያከናውን የምህንድስና ዘርፍ ነው።

መጠነ ዙሪያ
                                               

መጠነ ዙሪያ

መጠነ ዙሪያ አንድን ስፋት የሚያካልል ርዝመት ነው። ይህ እንደ ክብ ወይም አራት ማዕዘን ላሉ ባለ ሁለት ቅጥ ስፋቶች፤ መጠነ ዙሪያ ማለት የድንበራቸው ርዝመት ሲሆን፣ እንደ ኳስ ላሉ ባለ ሶስት ቅጥ አካላት ደግሞ፤ የውጭ ገፅ አንድ ዙር ርዝመት ይሆናል።

ቀበቶ (ማሽን)
                                               

ቀበቶ (ማሽን)

ቀበቶ ከተጣጣፊ ቁስ የተሰራ አንድ ዙር የሚሰራ፣ ሁለት የሚሽከረከሩ መዘውሮችን የሚያገናኝ የማሽን ዓይነት ነው። ቀበቶወች ለእንቅስቃሴ ምንጭ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ፣ ወይም ድግሞ ኃይል ለማስተላለፍ ወይም አንጻራዊ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ይረዳሉ። በቀበቶ ሁለትበከራወች በአንድ አቅጣጫ እንዲሽከረከሩ ማድረግ ይቻላል ወይም ከተፈለገ ቀበቶውን በማቋረጥ በተቃራኒ አቅጣጫ እንዲሽከረከሩ ማድረግ ይቻላል። በታላቅ የገበያ ቦታወች ላይ የሚሰራበት አመላላሽ ቀበቶ የዚህ ማሽን አንዱ ተግባራዊ መገለጫ ነው።

አጣብቂ
                                               

አጣብቂ

አጣብቂ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ቁሶችን አንድ ላይ ሜካኒካል በሆነ ሁኔታ የሚያያይዝ ማሽን ነው። በኬሚካል የሚያጣብቁን ፣ እንደ ማስቲሽ ያሉትን አይጠቀልልም። አንድ የአጣብቂ አይነቶችን ለምሳሌ ብንወስድ፡ ስቴፕለር ቁልፍ ዚፕ ብሎን አውታር ስፒል ቬልክሮ ምስማር ይገኙበታል።

                                               

አጥር

አጥር በግንባታ ስራ ውስጥ በቤት ወይም በሌላ ንብረት ዙሪያ እንደ በጠበቂያ ወይንም የድንበር ወሰንነት የሚያገለግል መዋቅር ነው። ይህ መዋቅር ከእንጨት የሚሰራ ከሆነ በሚስማር ወይንም ሌላ ማያያዣ እየተያያዘ እንዲቆም ይደረጋል። ነገር ግን መዋቅሩ እንደ ቆርቆሮ፣ ጎማ፣ ግንብ እንዲሁም ሽቦ የመሰሉ የተለያዩ የግንባታ ግብአቶች ሊሰራ ይችላል።

ኩችኔታ
                                               

ኩችኔታ

Catalogs, CAD files and more Bearings information from Bosch Rexroth How Bearings Work - Animations and functioning How Bearings Work - - Animations on www.mechanismen.be Early Bearing Failure Detection - Case study

                                               

የግምባታ መሬት ሳይንስ በምህንድስና

ደግሞ ይዩ፦ ላይ አፈር በተፈጥሮ አፈር ሶስት ቁሦች አሉት፡ ማለትም ፈሣሽ ፣ ጠጣር አፈር እንዲሁም አየር ናቸው። የአፈር ጥንካሬ በነኝህ ሦስት ቁሶች መጠንና የርስ በርስ ግንኙነት ይወሰናል። የአፈር ጠጣር ክፍል ከተለያዩ ቁሦች የተሰራ ነው፣ ከነኝህ ውስጥ የሸክላ አፈር ክሌይ ፣ አሸዋ፣ የተፈጥሮ ብስባሽ፤ እንዲሁም ከተለያዩ ማእድኖች ይገኙበታል። እነኝህን የአፈር አይነቶች ለምህንድሥና አላማ በሁለት ይከፈላሉ፣ እርስ በርስ ተጣባቂ አፈሮች ለምሣሌ የሽክላ አፈር፣ እርስ በርስ የማይጣበቁ አፈሮች ለምሣሌ አሸዋ በተፈጥሮ በመሬት ውስጥ የርስ በርስ ተጣባቂ አፈሮች መጠን ዝቅተኛ ቢሆንም የአፈርን ባህርይ በከፍተኛ ደረጃ ይወስናሉ። አፈር በመጠን እንደሚከተለው ይከፋፈላል፤ የሽክላ አፈር ክሌይ (

ድልድይ
                                               

ድልድይ

ድልድይ በመንገድ ላይ የሚያጋጥሙ እንደ ውሃ፣ ሸለቆ እንዲሁም ሌላ መንገድ ያሉ መሰናክሎችን ለማሻገር የሚሰራ የመንገድ አካል ነው። የድልድዩ ቅርፅ እንደ ድልድዩ ጥቅም፣ የማሰሪያ በጀት፣ የሚሰራበት አካባቢ እንዲሁም እንደተጠቀምንበት መስሪያ ይለያያል። አንድን መሠናክል ለማለፍ የሚሠራ የድልድይ አይነት በድልድዩ ጥቅም፣ ድልድዩ በሚሰራበት ቦታ ባለው የመሬት አቀማመጥ፣ ለመሥሪያነት በምንጠቀምበት ቁስ እና ድልድዩን ለመሥራት በተመደበው በጀት ላይ ይወሰናል።

ጥርስ (ማሽን)
                                               

ጥርስ (ማሽን)

ጥርስ ተሽከርካሪ ማሽኝ ሲሆን እላዩ ላይ በተቀረጹ ጥርሶች የሌላን አካል ጥርስ በመንከስ ጠምዛዥ ጉልበትን ከአንድ አካል ወደ ሌላ የሚያስተላልፍ ነው። ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ጥርሶች ተባብረው ሲሰሩ አስተላላፊ ይሰኛሉ። ጥርሶች የአንድን ሃይል ምንጭ አቅጣጫ፣ መጠንና ፍጥነት ቀይረው ማስተላለፍ ይችላሉ። ስለሆነም ለመኪና ማርሽነት ግልጋሎት ይሰጣሉ። በጥርስ ቁጥሮች ልክ ትክክለኛ የፍጥነት ውድር መቀመር ስለሚቻል ጥርሶች ለሰዓት ስራ ያገለግላሉ።

Users also searched:

...
...
...