Back

ⓘ መልክዐ ምድር
                                               

መሬት

መሬት በሥርዓተ ፀሐይ ውስጥ ከፀሐይ ባላት ርቀት ሶስተኛ በግዝፈት ደግሞ ከፕላኔቶች ሁሉ አምስተኛ ግዙፍ የሆነች ፈለክ ናት። በግዝፈት እና በይዘት ቋጥኛዊ ይዘት ካላቸው ወይንም በእንግሊዝኛው ተሬስትሪያል ፈለኮች ከሚባሉት የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች። በተለምዶ ዓለም ወይም ምድር እየተባለች ትጠራለች። በሳይንሳዊ የተለምዶ ስም ደግሞ "ሰማያዊዋ ፕላኔት" እየተባለች ትጠራለች። ይህች ፕላኔት የሰው ልጅን ጨምሮ ለብዙ ሚሊዮን ዝርያዎች መኖሪያ ናት። ከምድር ብዛት አትክልት ሁሉ እየበቀሉ ሲሆን ለሰው ልጅና ለእንስሳ ያስፈለጉት እህል፣ ፍራፍሬ፣ መድኃኒቶችና ሌሎችም ሁሉ ታስገኛለች። ይህም የታወቀች ብቸኛዋ ህይወት ያለው ነገር መኖሪያ ያደርጋታል። ስለዚህ ነው በተለያዩ እምነቶች ዘንድ ምድራዊት እማማችን የተባለች። "አብርሃማዊ" በተባሉት ሃይማኖቶች በተለይ ክርስትና፣ እስልምናና አይሁድና ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚሉ፣ መጀመርያ ፪ ሰዎች አዳምና ሕይዋን ከኤደን ገነት ወጥተው የሰው ልጅ ታሪክ ከ6 ሺህ አመታት በላይ ብዙ አይሆንም። ከዚያ አስቀ ...

                                               

ሰዓት ክልል

የ ሰዓት ክልል ማለት ሰዓቶቻቸው እንዲስማሙ ያለበት አገሮች ሁሉ የወሰኑበት ክልል ነው። በብዛት የጎረቤት ሰዓት ክልሎች ጊዜ ልክ በ1 ሰዓት ስለሚለያዩ የክልሉን ሰዓት ከግሬኒች አማካኝ ጊዜ ባለው ልዩነት ይቆጠራል።

                                               

ቅጥ

ቅጥ: ባንድ ነገር ወይም ኅዋ ውስጥ የታቀፉትን ነጥቦች በበቂ ሁኔታ ለመግለፅ የሚያስፈልጉን መለኪያወች ብዛት ቅጥ ይባላል። ለምሳሌ አንድ መስመር ላይ ያለን ነጥብ አንድ ቁጥር ብቻ ያስፈልጋል፣ ይሄውም ከመስመሩ መጀምሪያ ያለው ርቀት ነው። በዚህ ምክንያት መስመር አንድ ቅጥ አለው እንላለን። የተንጣለለ ሜዳን ገጽታ ወይም ደግሞ የበርሜልን ገጽታ ወይም የደብሉልቡል ኳስን ገጽታ ወይም ሌላ ገጽታን ብንወስድ፣ በዚያ ገጽታ ላይ ያለን ነጥብ አቀማመጥ ለመወሰን ሁለት መለኪያወች ያስፈልጉናል። በዚህ ምክንያት ማንኛውም ገጽታ ሁለት ቅጥ አለው ይባላል። ከኳሱ ገጽታ ዘልቀን ገብተን ወይም በባሊ ካለ ውሃ ውስጥ ገብተን ወይም ካንድ ሙሉ ነገር ውስጥ ዘልቀን ገብተን የምናገኘውን ነጥብ ዐቀማመጥ ለመወሰን ሶስት መለኪያወች ያስፈልጉናል። በዚህ ምክንያት ማንኛውም ምላዓት ያለው ቁስ ሶስት ቅጥ አለው ይባላል። ነጥብ ግን እንደትርጓሜዋ ምንም ቅጥ የላትም ምክንያቱም ርዝመትም ሆነ ስፋትም ሆነ ይዘት የላትምና።

                                               

ዋሻ

ዋሻ ተፈጥሯዊ የሆነ እና በመሬት መቦርቦር የተፈጠረ ክፍተት ነው። ይህ ክፍተት ዋሻ ለመባል ቢያንስ ሰው የሚያስገባ መጠን ሊኖረው ይገባል። ሥነ-ዋሻ የሚባለው የሳይንስ ዘርፍ በዋነኛነት እንደ ዋሻ ያሉ ክፍተቶች እና አካባቢያቸውን ያጠናል።

                                     

ⓘ መልክዐ ምድር

  • ጂዎግራፊ የመልክዓ ምድር ወይም ጂዎግራፊ የመሬት አቀማመጥ ወይም ገጽታ የሚያመልከት ጥናት ነው ቃሉ ጂዎግራፊ ከግሪክ γεωγραφία ጌዮግራፊያ ምድር መጻፍ መጣ መልክዐ ምድር ጂዎግራፊ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ካርታወች በየዘመኑ
  • የኢትዮጵያ መልክዐ ምድር ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
  • በዚህ አቅራቢያ ውስጥ አያሌ መንግሥታት ይገኛሉ እነርሱም ኩወይት አገር ባህሬን ቃታር የተባበሩት የዓረብ ግዛቶች ኦማን የመን ሳዑዲ አረቢያ ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
  • ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
  • ኦማን በአረቢያ ልሳነ ምድር የተገኘ አገር ሲሆን ዋና ከተማው መስከት ነው ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
  • ባሕሬን በአረቢያ ልሳነ ምድር የሚገኝ አገር ነው ዋና ከተማው ማናማ ነው ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
  • ምስራቅ ሐረርጌ ዞን በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ 12 ዞኖች አንዱ ነው አለማያ ባቢሌ ፉኛን ቢራ ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
  • ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
  • Category: Geology የሚገኛኙ ተጨማሪ ፋይሎች አሉ ይህ ሳይንስ ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
  • የጣልያን ታሪክ ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ
መሬት ጥናት (ጂዮሎጂ)
                                               

መሬት ጥናት (ጂዮሎጂ)

የመሬት ጥናት ወይም ጂዮሎጂ ስሙ እንደሚያመለክተው የመሬትን አሠራር፣ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎችን እና ታሪክ ያጠናል። ይህ ጥናት የመሬትን ውስጣዊ አሰራር አንድንገነዘብ በጣም ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል። ይህ ሙያ የተፈጥሮ ሐብቶችም የሚገኙበትን ቦታ እንድናውቅ ይረዳናል።

መግነጢሳዊ ስሜን ዋልታ
                                               

መግነጢሳዊ ስሜን ዋልታ

መግነጢሳዊ ስሜን ዋልታ ማለት የመሬት መግነጢሳዊ ኃይል መስክ በቀጥታ ወደ ታች የሚስብበት ሥፍራ ነው። በስሜን ዋልታ አካባቢ ይዞራል። ጠድከልን ስለሚስብ የስሜን አቅጣቻ ለማጠቆም አገልግሏል። ተዘዋዋሪ እንደ ሆነ ሁሉ ለብዙ ክፍለዘመናት በስሜኑ ካናዳ ይገኝ ነበር። ዳሩ ግን በቅርቡ ባለፉት ዓመታት ካናዳን ትቶ በፍጥነት ወደ ሳይቤሪያ እየተጓዘ ነው። ይህ በምድሪቱ መሃል ያሉት ፈሳሽ ብረታብረቶች አቀማመጣቸውን እየተቀየሩ ስለ ሆነ ነው ይባላል። እንዲሁም መግነጢሳዊ ደቡብ ዋልታ ባለፉት ቅርብ አመታት ከአንታርክቲካ ወጥታ ትንሽ ወደ አውስትራሊያ ቀርባለች።

ሴይንት ህሊና፣ አሰንሽንና ትሪስተን ደ ኩና
                                               

ሴይንት ህሊና፣ አሰንሽንና ትሪስተን ደ ኩና

ሴይንት ህሊና፣ አሰንሽንና ትሪስተን ደ ኩና በአትላንቲክ ውቅያኖስ የሚገኝ የእንግሊዝ ቅኝ አገር ነው። ሴይንት ህሊና ደሴት፣ አሰንሽን ደሴት እና ትሪስተን ደ ኩና ያጠቅልላል። ከነሐሴ 26 ቀን 2001 ዓ.ም. በፊት፣ አሰንሸን ደሴት እና ትሪስተን ደ ኩና በሴይንት ህሊና ጥገኝነት ሥር ኖረው ነበር፤ በዚያ ቀን ግን ሦስቱ ግዛቶች በሕግ እኩል ተደርገው የጠቅላላ ግዛቱ ይፋዊ ስም ከ "ሴይንት ህሊናና ጥገኞቿ" ወደ "ሴይንት ህሊና፣ አሰንሽንና ትሪስተን ደ ኩና" ተቀየረ።

ስሜን ዋልታ
                                               

ስሜን ዋልታ

ስሜን ዋልታ ማለት የመሬት እንዝርት የምትዞርበት ከሁሉም ስሜን የሆነው ያው ነጥብ ነው። በአርክቲክ ውቅያኖስ መሃል ይገኛል። ለዚህም ቅርብ የሆነው መግነጢሳዊ ስሜን ዋልታ ሌላ ነጥብ ነው። ይህ ጠድከል ምንጊዜም የሚያጠቆም፣ በቀስ ተዘዋዋሪ የሆነ ሥፍራ ነው። በተጨማሪ ሦስተኛ ምድረ መግነጢሳዊ ስሜን ዋልታ ደግሞ አለ።

ኒው ጊኒ
                                               

ኒው ጊኒ

ኒው ጊኒ በኦሺያኒያ የተገኘ ታላቅ ደሴት ነው። አሁን በኢንዶኔዥያና በፓፑዋ ኒው ጊኒ ይካፈላል። ደሴቱ የሸንኮራ ኣገዳ እንዲሁም የሙዝ መነሻ እንደ ሆነ ይታመናል። ከዚህም በላይ በአትክልትም ሆነ በእንስሳት በኩል ብዙ ብርቅዬ ዝርዮች አሉ።

ከፍታ (ቶፖግራፊ)
                                               

ከፍታ (ቶፖግራፊ)

ከፍታ በቶፖግራፊ ወይም መልክዐ ምድር ማለት አንድ ሥፍራ ከባሕር ጠለል በላይ በስንት ሜትር እንደሚርቅ የሚገልጽ ተውላጠ ቁጥር ነው። ጫፍ summit ማለት አጠገብ ካሉት ስፍራዎች ሁሉ በላይ ከፍተኛው የሆነ ጫፍ ነው። በትምህርተ ሂሳብ ረገድ የከፍታው ጫፍ እንደዚህ ይቀመራል። በተራ አባባል ከፍታ ማለት ብዙ ለየት ያለው የተራራ ጫፍ ማለት ነው። በምድር ገጽታ ከ1 ኪሎሜትር አቅራቢያ ከፍ ያለው ጫፍ ሲሆን ኢንደዚህ ይባላል።

የምድር መጋጠሚያ ውቅር
                                               

የምድር መጋጠሚያ ውቅር

የምድር መጋጠሚያ ውቅር በምድሪቱ ያለባት እያንዳንዱ ሥፍራ በሦስት መጋጠሚያ ተውላጠ ቁጥሮች እንዲወሰን ያስችላል። እነርሱም፦ 1) ኬክሮስ ፤ 2) ኬንትሮስ እና 3) ከፍታ ናቸው። እነዚህ በምድሪቱ ዙረት ዋልታ ተስረው በጂዎሜትሪ እንደ ፈልክ ያለውን ማንኛውንም ቅርጽ መለካት ይመስላል።

ያሬን
                                               

ያሬን

ያሬን የናውሩ ሠፈር ነው። የናውሩ ማዘጋጃ ቤት እዚያ ስለሚገኝ ብዙ ጊዜ እንደ ደሴቲቱ ዋና ከተማ ቢቆጠርም በይፋ ግን አገሪቱ ምንም ዋና ከተማ የላትም። በሠፈሩ የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር በ1995 ዓ.ም. 1.100 ሆኖ ይገመታል።

ደቡብ ዋልታ
                                               

ደቡብ ዋልታ

ደቡብ ዋልታ ማለት የመሬት እንዝርት የምትዞርበት ከሁሉም ደቡብ የሆነው ያው ነጥብ ነው። በአንታርክቲካ አህጉሩ መሃል ይገኛል። ለዚህም ቅርብ የሆነው መግነጢሳዊ ደቡብ ዋልታ ሌላ ነጥብ ነው። ይህ ጠድከል ምንጊዜም የሚያጠቆም፣ በቀስ ተዘዋዋሪ የሆነ ሥፍራ ነው። በተጨማሪ ሦስተኛ ምድረ መግነጢሳዊ ደቡብ ዋልታ ደግሞ አለ።

ጌዎግራፊያ፡ማለቱ፡የምድር፡ትምህርት። 1833
                                               

ጌዎግራፊያ፡ማለቱ፡የምድር፡ትምህርት። 1833

ምናልባትም የመጀመሪያው የአማርኛ ጅዎግራፊ መጽሐፍ ሊባል የሚችለው ይህ መጽሐፍ በቄሱ ቻርለስ ዊሊየም ኢዘንበርግ በእንግሊዝ አገር በ1833 ዓ.ም ታተመ። ስለአውሮጳ ከተሞች፣ ስለ አገሮች፣ አህጉሮች፣ፈለኮችና ከዋክብት የሚያትተው ይህ መጽሐፍ 268 ገጾችን ያዝላል። ከታች የሚታዩትን ገጾች በመጫን ቀጥታ ማንበብ ወይም ዳውንሎድ አድርገው ቀስ ብለው ማንበብ ይችላሉ።

Users also searched:

...
...
...