Back

ⓘ ዐውደ ምንባብ ያልተገለጸ
                                               

ማትያስ ከተማ

ማትያስ ከተማ የእኔ ሽበት የተባለ የግጥም ምጽሐፍ የጻፈ ሲሆን በድረ ገጾች ላይ በሚጽፋቸው ግጥሞች ይታወቃል። ግጥሞቹን የሚጽፋቸው ወለላዬ በሚል የብዕር ስም ነው። ከታች የተዘረዘሩት ግጥሞቹ ከብዙ ጥቂቶቹ ሲሆኑ የሮብዕ ግጥሞች በሚል ለሁለት ዓመት ያህል አጫጭር ግጥሞች ለአንባብያን በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ላይ አስነብቧል አጫጭር ልብ ወለድ ጽሁፎቹንም ያቀርባል። ነዋሪነቱ በስዊድን ነው። እኔን ስቀሏት የኔ ሽበት ከወለላዬ በድል እንግባ! ከወለላዬ የኛ ሰው ሊቁ. ወለላዬ ዳሪና ቀባሪ ስው አይደለም አለኝ እኛም እንዳንሰቅለው ይድረስ ለአቶ መለስ ወለላዬ የፈና ጅራ የፈና ጅርቱ ከወለላዬ የዛ ሰውዬ ድምጽ እኛም ቃል ገብተናል! ወለላዬ እኔና አንቺ.ቁ. 1 እና 2 ስደት ተወኝ ወለላዬ ድምፃችን ይሰማ! ወለላዬ ካሣን አትቀስቅሱት!! ወለላዬ የት ይሆን መድረሻው? ወለላዬ ቅ ደግሞ ደፈረሰ ሰልፍ ልውጣ በአንድነትህ ፅና ወለላዬ - በድምፅ የሙዚቃ አባዜ ወለላዬ እኔም አለኝ ሕልም ከወለላዬ "እኔ ላንቺ ብዬ …" ወለላዬ ተኩስ አቁም ይደረግ! ከ ...

                                               

አንተነህ መንግስቴ

ውልደት አንተነህ መንግስቴ በ መጋቢት 13 1978 ዓም በ ጎጃም ክፍለ ሀገር ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በቀድሞው ሞጣ አውራጃ በ ቀራንዮ ከተማ ነው የተወለደው። ትምህርት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቀራንዮ ተምሯል፤ የሁለተኛና የመሰናዶ ትምህርቱን ደግሞ በሞጣ ነው የተማረው። በ18 ዓመቱ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባውን ውጤት በማምጣት ባህርዳር ተዩኒቨርሲቲን ተቀላቅሏል። በጋዜጠኝነትና በኮሙኒኬሽን በ1999 ዓም በማዕረግ ተመርቋል። ስራ አንተነህ ከዩኒቨርሲቲ እንደተመረቀ ለ4 ወራት ያህል ስራ ፈልጎ በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ማስታወቂያ ጽ/ቤት የፕሬስና ኢንፎርሜሽን ዴስክ ኃላፊ በመሆን ለ6 ወራት ሰርቷል። በግንቦት 2000 ዓም የአማራ ብዙሃን መገናኛ ደርጅትን ተቀላቅሎ ጋዜጠኛ ሆኗል። በድርጅቱ ለሁለት ዓመት ከሰራ በኋላ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን በ2002 ሰኔ ወር ተቀላቅሎ ለ11 ወራት አገልግሏል። ከዚያም ወደ ክልል በመመለስ በጋዜጠኝነት ዘርፉ በመስራት ላይ ይገኛል። አንተነህ ህልሙ ረቂቅ እሳቤው ምጡቅ ነው። ዛሬ በጋዜጠኝነት እየሰ ...

                                               

ምወዳትን ተረት እነሆ

በጣም ቀዝቃዛ በሆነ አንድ የክረምት ወቅት አንዲት ወፍ በጎጆዋ ተኝታ ነበር፡፡ ይሁንና ጎጆዋ ውስጥ ሆና ቅዝቃዜውን መቋቋም ስላልቻለች፤የዝናብም ጠፈጠፍ ከቅርንጫፎች ላይ ወደ ጎጆዋ እየሰረገ ስላስቸገራት ከጎጆዋ ወጥታ መብረር ጀመረች፡፡ተቀምጬ ሞቴን ከምጠባበቅ እድሌን ልሞክር ብላ ከጎጆዋ ወጥታ ስትበር ቅዝቃዜውም እየባሰ ዝናቡም እያየለ ሄደ፡፡ ከጥቂት ቆይታም በኋላ ቆፈን ክንፎቿን አላላውስ ብሏት መብረር ስላቃታት ከብቶች ሳር ከሚግጡበት መስክ ላይ ወደቀች፡፡ በመስኩም ላይ ከነበሩ ከብቶች አንዲቱ ላም ባጠገቧ 1 ስታልፍ አዛባዋን ጣለችባት፡፡ የአዛባውም ትኩስነት ለሰውነቷ ሙቀት ሠጣት፡፡ደሟ ሲሞቅ አካሏም ሲፍታታ ይታወቀት ጀመር፡፡ ከሞት ስጋት ተርፋ እንዲህም ህይወት ተስፋ ስለሰጠቻት ደስ ተሰኘች፡፡ ከደስታዋም ብዛት 3በአዛባው እንደተሸፈነች መዘመር ጀመረች፡፡ በአካባቢውም ርቦት ተኝቶ የነበረ የዱር ድመት የወፏን ዝማሬ ተከትሎ ወደ አዛባው ተጠጋ ፡፡ ከአዛባው መሃልም አውጥቶ በላት፡፡ ትምህርት 1----- ክፉ የሚያደርግብህ ሁሉ ጠላት ...

                                               

የመማፀኛ ከተማ ቤተ ክርስቲያን

በቀድሞ አጠራር ዮጎ ሲቲ ቤ/ያን ሲባል አድራሻ፡ ከቦሌ ድልድይ በብራስ ሆስፒታል በኩል ወደ ቦሌ መድሃኔያለም በሚወስደው መንገድ ቦሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል ፊትለፊት የቤተ ክርስቲያኒቷ ራዕይ ፡ ዮጎ ሲቲ ቤ/ያን የእግዚአብሔርን ንፁህና የማይለዋወጥ ፍቅር እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በቤተክርስቲያን ውስጥ፣ በህብረተሰብ ውስጥ፣ ብሎም በአለም ሁሉ የሚያዩና የሚሰብኩ የተነቃቁ አባላት እንዲሁም ሌሎች ወደ ቤተክርስቲያኗ በመምጣት ትምህርትን የሚከታተሉ ሰዎች ህብረት የሚያደረጉበት ስፍራ ነው፡፡ ቤተክስቲያኒቷ በተራራ ላይ እንዳለችው ልትሰወር እንደማትችለው ከተማ እንድትሆን ማንኛውንም ዋጋ እንከፍላለን፡፡መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚናረገው በእምነት ብቻ ስለሚገኝ ፅድቅ እና በአማኙ አጠቃላይ ህይወት ውስጥ ቅድስና መኖር እንዳለበት እናምናለን፡፡ ስለቤተክርስቲያንዋ አጀማመር በ1991 ዓ.ም አጋማሽ አከባቢ በአሁኑ ሰዓት በዮጎ ሲቲ ቸርች ዋና መጋቢ የሁኑትን መጋቢ ሞላልኝ አዱኛን እግዚአብሄር በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ ቤተከርስቲያንን እንዲያ ...

                                               

ተስፋዬ ገብረአብ

ተስፈዬ ገብረአብ የበርካታ መፅሀፍት ደራሲ ነው።ሆኖም ግን ከብዙሀኑ የአማርኛ አንባቢ ጋር በስፋት ያስተዋወቀው ማስታወሻዎቹ ናቸው፤ እነሱም የጋዜጠኛው፣ የደራሲው እና የስደተኛው ማስታወሻ የተሰኙ ትረካዎቹ ናቸው። ያልተመለሰው ባቡር እና የቢሾፍቱ ቆሪጦች እነዚህ ሁለት መፅሃፍትን እራሱ ተስፋዬ ገብረአብ፣ ችሎታዬን ያገየሁባቸው የሚላቸው ስራዎቹ ናቸው። ምንም እንኳ በአንዳንድ ሃያሲያን ለመተቸት ቢበቃም። የቡርቃ ዝምታ የቡርቃ ዝምታ በ1992 ዓም የታተመ መፅሀፍ ነው። መፅሀፉን ብዙዎች ጠብ አጫሪ ነው ብለው ቢተቹትም በቅን ልቦና ከተነበበ ግን አስተማሪና ታላቅ እውቀት አስጨባጭ እነደሆነ ይነገርለታል። ማስታወሻዎች ማስታወሻ በሚል ርዐስ ያሳተማቸው 3 መፅሀፍት ሲሆኑ፤ እነሱም የጋዜጠኛው ማስታወሻ 2000 ፣ የደራሲው ማስታወሻ 2000 እና የስደተኛው ማስታወሻ 2006 ናቸው። በነዚህ 3 መፅሀፍት የተበታተኑ ፅሁፎችና መረጃዎችን አንድ ወጥ በሆነ የጋራ ጉዳይ ዙሪያ ማስተሳሰር ችሏል። ፅሁፊቹ አብዛኛው ትኩረታቸው በጊዜው ፓለቲካ ቢሆንም ፣ የፃ ...

                                               

ከጥላቸው እራቅ

ህመምህ እንዳያገረሽብህ ኋላ መጥፎ ነው የሰው ጥላ ብለው ሲሉህ ሰምቼ ለወንድምነትህ ሳስቼ ልመክርህ ተነሳሁ በጥብቅ ከጥላቸው እንድትርቅ 2 መጨበጫም የለው መቼም የኔ ጣጣ በሀገሬም አልኖር ካገሬም አልወጣ እዛ ስሆን እዚ ከዚ እዛ እያሰብኩኝ ማደሪያ የሌለው ከንቱ አሞራ ሆንኩኝ 3 ሳስርና ስፈታ ስስብ ስሸመቅቅ ብዙ ዘመን ኖርኩኝ ስዘዋወር ስለቅ ዘንድሮም ደርሶብኝ ይሄው መገላበጥ ልብስ መሃል ቆሜ መስያለሁ ሸቀጥ 4. የየኔሰው ስንብት ከዋካ ምነው ፈጣሪ አምላክ? ምነው የዓለም ቤዛ በድርብ ሰንሰለት፤ እየተገረፍን ስንገዛ ጠላት እንኳን፤ ባልፈጸመው ጭካኔ ሲሸነቁጠን ወያኔ ስቃይ፤ ሞታችንን ለዓለም ነግረን ሰሚ ጠፍቶ ዝም ሲለን ምነው አንተስ ጨከንክብን? ለምን ፊትህን አዞርክብን? እንግዲያውስ ፈጣሪዬ፤ የማሪያም ልጅ ልመናዬ መራር ሆኖ ላንተም ባይበጅ በቃላቸው እንዳልረታ በገንዘባቸው እንዳልገታ አካሌ በችግር ደክሞ ሆዴ በጉርሻ ተስለምልሞ በፍቅረ ነዋይ ልቤ እንዳይደለል መንፈሴ ጽናት አጥቶ እንዳይዋልል ተደናቅፌ እንዳልቀር ሃገሬን እንዳልከ ...

                                               

መላከ ህይዎት ነቃ ጥበብ እሸቱ

መላከ ህይዎት ነቃጥበብ እሸቱ ከአባታቸው ከአቶ አሸቱ ይመር እና ክእናታቸው ከወ/ሮ አየናለም በ ፩፱፳፮ በደቡብ ወሎ ዞን በወልደያ ከተማ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት እስኪደረስ ድረስ ልክ እንደማንኛውም ህጻን ቤተሰቦቻቸውን በተለያዩ ስራዎች ሲረዱ ከቀዩ በኃላ ፯ ዓመት ሲሞላቸው ወደ ደቡብ ጎንደር ምስራቅ እስቴ ወረዳ በመሄድ ከወረዳው ዋና ከተማ ፲ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ቁት አረጋዊ ቤተ ክረሰቲያን የመንፈሳዊ ትምህርታቸውን ጀመሩ። ገና ከህጻንነታቸው ጀምሮ በትምህርት አቀባበላቸው መምህራኖቻቸውን በማስደነቃቸው ከሌሎች ተማሪዎች የተለየ ትምርት እንዲማሩ ይደረግ ነበር። ከላይ ከፍ ሲል ከተገለጸው የማዕረግ ስም በፊት የመጠረያ ስማቸው መኳንንት ነበር። ትምህርታቸውንም በአጭር ጊዜ ከዳዊት ደገማ አስከ ከፍተኛ ንባብ ፣ ከውዳሴ ማርያም እስከ ጸዋትወ ዜማ ትምህርታቸውን በማጠነቀቅ መምህሮቻቸውን አስደመሙ።

                                               

ብሩ ኬርስሞ

አቶ ብሩ ኬርስሞ ከወጣትነታቸው ጀምሮ ትምህርት እንዲስፋፋ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ አባት ነበሩ። የእምድብር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በካቶሊክ ቤተክስቲያን አማካይነት ሲቋቋም አቶ ብሩ ኬርስሞ የትምህርት ቤት የጠቅላላ ጉዳዮች ሁሉ ኃላፊ በመሆን ከአባ ፍራንሷ ማርቆስ ጋር በመሆን የላቀ አስተዋጽዎ አበርክተዋል። ቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ይባል የነበረው የእምድብር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲቋቋም በቤት ቤት በመሄድ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ አድርገዋል። እስከዛሬ ድረስም ትምህርት ቤቱን በማስዋብ ላይ ያሉትን የግራር ዛፎችን የተከሉትን እሳቸው ናቸው። አቶ ብሩ ኬርስሞ ለእምድብር አንደኛ ደረጃ ትምህት ቤት ዘበኛ፣ አትክልተኛ፣ ፓስተኛ፣ እቃ ገዢ እና መፃፍት አዳይ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ሥራዎች ደራርበው ቢሠሩም ሲከፈላቸው የነበረው ግን የአንድ አትክልተኛ ደመወዝ ብቻ ነበር። እምድብር ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲከፈት አቶ ብሩ ኬርስሞ ከአንደኛ ደረጃ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ተዘዋወሩ። የተማሪ ...

                                               

ተማረ ባምላኩ

Banks, J የህብረ ባህላዊ አመለካከትን ማዳበር ስለሚያስገኘው ጠቀሜታ በሚከተለው መልኩ ገልፆታል፡፡ በባህላችን አማካኝነት ያዳበርናቸው እሴቶችና እይታዎች እንዴት /ዓለምን የምንተረጉምበትን መንገድ/ እንደሚመሩና እይታችንም ላይ ድርሻ እንዳላቸው እንድናስተውል የሚረዳ አቅም ይፈጥርልናል፡፡ ጎልቶ የሚታየው ባህል እንዴት በሌሎች ባህሎች አባላት ግምት ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ያሳውቃል፡፡ አገልግሎት ሰጭዎችና ባለሙያዎች ከሌሎች የባህል አባላት ጋር እንዴት ተግባብቶ ማድረግ እንደሚገባቸው ግንዛቤ ይፈጥርልናል፡፡ ለሁሉም ባህሎች፣ ብሔረሰቦችና የእምነት ተከታዮች እኩል የሆነ አዎንታዊ እይታ እንድናዳብር የሚያስችል አቅም ይፈጥርልናል፡፡ ተረስተው እና ትኩረት አጥተነው የነበሩ ህዝቦች በባህላቸው፣ በብሔረሰባቸውና በሚከተሉት እምነት ሳይሸማቀቁ በዜግነታቸው የሚኮሩበትን ስነልቦናዊ አቅም ያዳብርላቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ህብርባህላዊ አመለካከት ማዳበር ራሳችንን የምንገነዘብበትን መንገድ ያጎለብትልናል፡፡

                                               

ሐውሳ ቋንቋ

አማርኛ የፊደል ገበታ ማንኛውንም በስልክ ወይም በቃል የሰሙትን የዓለም ቋንቋ በጽሑፍ በማስቀመጥ የእንግሊዝኛን ጎደሎ ይሸፍናል።የፊደል ገበታ ከሦሥት እስከ አንድ ዓመት ጠንቅቆ ከተጠና በኋላ ማንበብና መጻፍ ለዘላለም ሙሉ አንባቢና ጸሐፊ ያደርጋል።የአራተኛ ክፍል እና የስድስተኛ ተማሪዎቹን ጳውሎስ ኞኞንና ማሞ ውድነህን ለአብነት መጥቀስ ይችላል።

                                               

ዘላለማዊነት

ለመሆኑ "እኔ ማነኝ" ብለው ያውቃሉ? ካለወቁ ግን ጌዜ አለዎትና ራስዎን ይጠይቁ። የስነ-ህዋ ተመራማሪዎች ግን ሰወች የሚያስቡ ዩኒቨርስ ናቸው ይላሉ። አንድ ነገር ይወቁ እየኖርን ያለነው እጅግ ስፍር ቁጥር በሌላቸው ከዋክብቶች፣ ፕላኔቶች፣ ቋጥኞች ውስጥ ነው።

                                               

አማረ ብርመጂ

አማረ ብርመጂ ከአባታቸው ከአቶ ብርመጂ ቱፋ ከእናታቸው ክወ/ሮ ወርቅነሽ ደሳለኝ በ፲፱፻፳፰ በአሩሲ ክፍለሃገር ጎሎልቻ ከተማ ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ፤ታላቅ እህታቸው ወ/ሮ ክብነሽ ብርመጂ ወደሚኖሩበት ሁሩታ ከተማ ተጉዘው ኑሮ ጀመሩ። ባለቤታቸው ወ/ሮ ሽታ ፈለቀ ልጆቻቸው ቻቻ አማረ አሰገድ አማረ አቤል አማረ ብሩክ አማረ ያለምዳር አማረ ሳሙኤል አማረ ሰርካለም አማረ ናቸው ።