Back

ⓘ ትርጕም
                                               

ደብተራ

ደብተራ ማለት ድንኳን ማለት ነው አንድም ካህንን አገልጋይ መዘመር አንድም በእውቀቱ ከፍ ያለ ሊቅ ማለት ነው። ●የደብተራ ትርጓሜ በመዛግበተ ቃላት ወጥበባት ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላቸው፡- ‹‹ደብተራ – ድንኳን፡፡ ደበተረ – ደብተር ዘረጋ፣ ጻፈ፣ ከተበ ፡፡ ተደበተረ – ተዘረጋ፡፡ ደብተራ – የድንኳን ስም፡፡ ደብተራ – ዜማ. ቅኔ፣ ሳታት ሰዓታት የሚያውቅ፣ በደብተራ በድንኳን ውስጥ የሚመራ፣ የሚቀኝ፣ የሚዘምር፣ መንፈሳዊ አገልጋይ፣ ካህን፣ አወዳሽ ሳታት ቋሚ፡፡ ደብቴ – ከፊለ ስም ወይም ቁልምጫ፣ የደብተራ ወገን፣ የኔ ደብተራ ማለት ነው፡፡›› ይሉናል፡፡ ● #ግእዙም፡- ‹‹ደብተረ› ማለትን በአወራረዱ ሕግ በተንበለ ቤት አስገብቶ ሲያበቃ ‹‹ተከለ›› ሲል ይተረጕምና ለድንኳን ይሰጠዋል፡፡ ግእዝ ድንኳን ለሚለው ቃል ከደብተራ በተጨማሪ ኀይመትና ደበና ማለትን ይጠቀማል፡፡ ደበና የንጉሥ ድንኳን የሚጠራበት ስም ነው፡፡ ደበናንሳ ባለእጅ የሚለው ቃል ከዚህ ስም ጋራ ስለመያያዝ አለመያያዙ አላውቅም! ●የፕ/ር ሥርግው አማርኛ የቤ/ክ ...

                                               

ሚስኪቶ

ሚስኪቶ በማዕከል አሜሪካ የሚኖር ብሔር ነው። መሬታቸው ከካሜሮን ርእሰ ምድር ሆንዱራስ ጀምሮ እስከ ሪዮ ግራንዴ ወንዝ ኒካራጓ ድረስ ይዘረጋል። የራሳቸው ሚስኪቶ ቋንቋ አለ። ነገር ግን የእስፓንኛ እና የሚስኪቶ እንግሊዝኛ ፓቷ ተናጋሪዎች በትልቅ ወገን ይገኛሉ። የሚስኪቶ እንግሊዝኛ ፓቷ የመጣ ከእንግሊዞች ጋራ ብዙ ጊዜ በማገናኘታቸው ነበር። ብዙዎቹ ክርስቲያኖች ናቸው። በጊዜ ላይ ያመለጡ ባርዮች ከነሱ ጋር ስደት ስላገኙ ዘራቸው ተደባልቆ ክልስ ሆነ። መሬታቸውን ለመድረስ አስቸጋሪ በመሆኑ እስፓንያውያን ሰፊ አገሩን ሲወረሩ ለሚስኪቶዎቹ ብዙ ውጤት አልነበረም። የሚስኪቶ ባሕላዊ ኅብረተሠብ በጣም የተደራጀ ነውና የተወሰነ ፖለቲካዊ ሥራዓት አለው። ንጉስ ቢኖሯቸውም ሙሉ ሥልጣን ግን አልነበራቸውም። ከነገስታታቸው ብዙዎች የሚታወቁ ከአፈታሪክ ስለሆነ የነሱ ታሪካዊ መረጃ ሁልጊዜ ግልጽ አይደለም። መንግሥታቸው ከ1617 ዓ.ም. በፊት ጀምሮ በታሪኩ መጀመርያ የተመዘገቡት ንጉሳቸው ኦልድማን ነበሩ። በአባታቸው ዘመን ከእንግሊዞች ተገናኝተው ኦልድማን ...

                                               

ዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን

"ይህ ገጽ ከእንግሊዝኛው በቀጥታ የተቀዳ ነው። በቀስ ይተረጎማል በማለት ነው።" ዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በቤጂንግ ቻይና በ1909 ዓ.ም. የተመሠረተ ነፃ ቤተ ክርስቲያን ነው። በ6 አህጉር ላይ 1.5 ሚሊዮን የሚያሕሉ ምዕመናን አሉት። ቤተ ክርስቲያኑ በቻይና የወጣ ከጰንጤ እንቅስቃሴ የተነሣ ነው። ይህ ቤተ ክርስቲያን ግን የሥላሴ ጽንሰ ሐሳብ አይቀበልምና "የኢየሱስ ስም ትምሀርት" ተከታዮች ናቸው።

                                               

ይሁዳዊ-ሮማንስ ቋንቋዎች

ይሁዳዊ-ካታላን ወይም ካታላኒክ በሰሜንና በምሥራቅ እስፓንያ እና በባሌሪክ ደሴቶች በ"ተሰወረ አይሁዳዊ ህብረተሠብ" ቅሬታ ሆኖ ይቆያል። ይሁዳዊ-ጣልኛ ወይም ኢታልኪያን ቀበሌኞች በደንብ የሚናገሩ ዛሬ ከ200 በታች ናቸው። ቀድሞ ግን በጣልያና በግሪክ አገሮች በሰፊ ይናገር ነበር፡፡ ይሁዳዊ-አራጎንኛ በሰሜን እስፓንያ ቀድሞ ከ750 ዓ.ም. ጀምሮ ይናገር ነበር፡፡ በ1484 ዓ.ም. አይሁዶች ሁሉ ከእስፓንያ ከተባረሩ በኋላ ግን መናገሩ ቆመ፡፡ ይሁዳዊ-ሮማይስጥ ወይም ላዓዝ በድሮው ሮማ መንግሥት የተናገረው ቀበሌኛ ነበር፡፡ ይሁዳዊ-ፖርቱጊዝ ወይም ሉሲታኒክ በፖርቱጋል "ተሰወረ አይሁዳዊ ህብረተሠብ" ቅሬታ ሆኖ ይቆያል። ላዲኖ የእስፓንያ ዋና ይሁዳዊ ቀበሌኛ እስከ 1484 ድረስ ነበር፡፡ ከመበራረትቸው በኋላ በተበተኑት ህብረተሠብ ጥቅሙ ሳይቋረጥ ዛሬም አንደኛው ይሁዳዊ-ሮማንስ ቋንቋ ሆኖ ይገኛል፡፡ ሿዲት ወይም ይሁዳዊ-ፕሮቨንሳል በደቡብ ፈረንሳይ ከኦሲታኛ የታደገ ቀበሌኛ ነው፡፡ በተለይ ጽኑ የዕብራይስጥ ተጽእኖ ነበረበት፡፡ ዛሬ ግን አይሰማ ...

                                               

ሃሰኩራ ጹነናጋ

ሃሰኩራ ሮኩኤሞን ጹነናጋ 支倉六右衛門常長, 1563–1614 ዓ.ም. ጃፓናዊ ሳሙራይ መኮንን እና የሰንዳይ ዳይምዮ ገዥ የዳተ ማሳሙነ ሎሌ ነበሩ። ከ1605 ዓ.ም. እስከ 1612 ዓ.ም. ድረስ ወደ ሜክሲኮ፣ እስፓንያ፣ ፈረንሳይ እና ጣልያን አገሮች አምባሳደር ሆነው ይፋዊ ጉብኝት አደረጉ። ከማንም በፊት ወደ አሜሪካ አህጉር የተላኩት የጃፓን መንግሥት ልዩ ተወካይ እሳቸው ነበሩ። ከዚያ በላይ የርሳቸው ተልዕኮ በታሪክ መዝገብ የሚታወቀው መጀመርያው ጃፓናዊ-ፈረንሳያዊ ግንኙነት ሆኗል። ስለ ልጅነታቸው ብዙ ባይታወቅም፣ በታይኮ እንደራሴ ሂደዮሺ በኮርያ ላይ በተደረገው ወረራ ጊዜ በ1584 እና በ1589 ዓ.ም. ዘመቻዎች ልምድ ያለው ሳሙራይ ሆነው እንደ ተሳተፉ ይታወቃል። በ16ኛው ምዕተ ዓመት ከተካሄደው አንድሬስ ዴ ኡርዳኔታ ጉዞ ጀምረው እስፓንያውያን በፊሊፒንስ የያዙትን መሬት መሠረት አድርገው በሜክሲኮና በቻይና መካከል ፓሲፊክ ውቅያኖስን ይሻገሩ ነበር። በ1563 ዓ.ም. ማኒላ ለምሥራቅ እስያ ሁሉ መሠረታቸው ሆነላቸውና። የስፓንያ ...

                                     

ⓘ ትርጕም

  • የ1812 መቅድም ለኦፔራ ጓድ በፕዮትር ኢልዪች ቻይኮቭስኪ የተጻፈ ሙዚቃ ነው ፈረንሳዮች በ1804 ዓ.ም. 1812 እ.ኤ.አ. ወደ ሩሲያ በወረሩበት ወቅት የናፖሊዎን ሠራዊት ድል ስለሆነ ሙዚቃው ለጦርነቱ መታሠቢያ እንዲሆን ተጻፈ ሙዚቃው
  • ይህ ገጽ ከእንግሊዝኛው በቀጥታ የተቀዳ ነው ቀስ በቀስ ይተረጎማል በማለት ነው ዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በቤጂንግ ቻይና በ1909 ዓ.ም. የተመሠረተ ነፃ ቤተ ክርስቲያን ነው በ6 አህጉር ላይ 1.5 ሚሊዮን የሚያሕሉ ምዕመናን
  • ይህዳዊ - ሮማንስ ቋንቋዎች ከሮማንስ ቋንቋዎች የወጡት በአይሁዶችም የሚናገሩ ልሳናት ናቸው የራሳቸው ቋንቋዎች ሆነው እስከሚቆጠሩ ድረስ ተለውጠዋል ማለት ነው ይሁዳዊ - ካታላን ወይም ካታላኒክ በሰሜንና በምሥራቅ እስፓንያ እና በባሌሪክ ደሴቶች
  • ሃሰኩራ ሮኩኤሞን ጹነናጋ 支倉六右衛門常長, 1563 1614 ዓ.ም. ጃፓናዊ ሳሙራይ መኮንን እና የሰንዳይ ዳይምዮ ገዥ የዳተ ማሳሙነ ሎሌ ነበሩ ከ1605 ዓ.ም. እስከ 1612 ዓ.ም. ድረስ ወደ ሜክሲኮ እስፓንያ ፈረንሳይ እና ጣልያን
አፋን ኦርማ ማ መዝገበ ቃላት 1850
                                               

አፋን ኦርማ ማ መዝገበ ቃላት 1850

አፋን ኦርማ ማ መዝገበ ቃላት የሜጫ ኦሮምኛን ቋንቋ ሰዋሰው እና ቃላት ትርጕም የሚመመረምር ጽሑፍ ሲሆን፣ የተደረሰው ከ19ኛው ክፍለዘመን አጋማሽ በፊት መሆኑ ነው ። ደራሲው ጎጃም ይኖሩ የነበሩ አቶ ሐብተ ስላሴ የተሰኙ ሰው እንደነበሩ ታሪክ አጥኝው ኮንቲ ሮሲኒ ዘግቦት ይገኛል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ 320 የኦሮምኛ ቃላት፣ ትርጕማቸውና እና አገባባቸው ተዘርዝረው ይገኛሉ። በተጨማሪ፣ ኮንቲ ሮሲኒ ብዙ የኦሮምኛ ቃላትን ወደ ጣሊያንኛ በመተርጎም በ1896 ይህን መጽሐፍ አሳትሞት ከታች ይገኛል። የመጽሐፉን ሙሉ ገጽ ለማንበብ ምስሉን ይጫኑ።

የ1773 ዓ.ም. ታላቅ አውሎ ነፋስ
                                               

የ1773 ዓ.ም. ታላቅ አውሎ ነፋስ

የ1773 ዓ.ም. ታላቅ አውሎ ነፋስ ከሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ ታላቁ አውሎ ንፋስ ነበር። ከጥቅምት 2 ቀን 1773 ዓ.ም. 10 October 1780 እ.ኤ.አ. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 8 October 16 ድረስ፣ መውጁ በማርቲኒክና በባርባዶስ ደሴቶች ላይ ሲጎርፍ 22.000 የሚያሕሉ ሰዎች ጠፍተዋል።

የ1812 መቅድም
                                               

"የ1812 መቅድም"

"የ1812 መቅድም" ለኦፔራ ጓድ በፕዮትር ኢልዪች ቻይኮቭስኪ የተጻፈ ሙዚቃ ነው። ፈረንሳዮች በ1804 ዓ.ም. 1812 እ.ኤ.አ. ወደ ሩሲያ በወረሩበት ወቅት የናፖሊዎን ሠራዊት ድል ስለሆነ ሙዚቃው ለጦርነቱ መታሠቢያ እንዲሆን ተጻፈ። ሙዚቃው በተለይ የሚታወቅበት የመድፍ ትኩስ ቅድም ተከተል በውስጡ ሊሰማ ስለሚችል ነው። አንዳንዴም የሙዚቃ ጓድ ሲያጫውተው በዕውነተኛ መድፍ ነው የሚደረገው። ምንም እንኳን በ1804 1812 በአሜሪካ እና በእንግሊዝ መካከል ስለ ተዋገው ጦርነት ሙዚቃው አንዳችም ግንኙነት ባይኖረውም፣ በዩናይትድ ስቴት ውስጥ ብዙ ጊዜ እንደ አርበኞች ሙዚቃ ተቆጥሮ ይሰማል።

Users also searched:

...
...
...